Sunday, May 22, 2016

Lesson 3 :- በጥምቀት ዙርያ የቤተክርስቲያኒቱ ጠንካራ ያልሆኑ ጎንዎቿና በአሁኑ ዘመን ያለው የትምህርት ይዞታ...

Lesson 3 :- በጥምቀት ዙርያ የቤተክርስቲያኒቱ ጠንካራ ያልሆኑ ጎንዎቿና በአሁኑ ዘመን ያለው የትምህርት ይዞታ..Part 5 በጥምቀት ዙርያ የቤተክርስቲያኒቱ ጠንካራ ያልሆኑ ጎንዎቿና በአሁኑ ዘመን ያለው የትምህርት ይዞታዋ ወነአምን በአሐቲ ጥምቀት ለሥርየተ ኃጢአት ኃጢአት በሚሠረይባት በአንዲት ጥምቀት እናምናለን የተወደዳችሁ ወገኖች የዛሬው ትምህርታችን የሚያጠነጥነው ኃጢአት በሚሠረይባት በአንዲት ጥምቀት እናምናለን በሚለው ሃሳብ ዙርያ ነው ይህ ሃሳብ የተገኘው አስቀድሞ በኒቅያ ጉባኤ ሦስት መቶ አስራ ስምንት ሊቃውንት በግዕዙ ቃል አነጋገር ሠለስቱ ምዕት የተባሉት ወልድ ፍጡር ነው በማለት የተገለጠውን አርዮስን መክረውና ዘክረው አልመለስ ባለ ጊዜ ፈጥነው የለዩበትና ተስማምተውም ይህንኑ የእምነት መግለጫ ያረቀቁ ያወጡም በመሆናቸው ቤተክርስቲያኒቱ ማለትም ጥንታዊትና ሐዋርያዊት ኦርቶዶክሳዊት የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ይህንን የእምነት መግለጫ አምናና ተስማምታ ከእነርሱ በመቀበል የእምነት መግለጫዋ አድርጋዋለች በመሆኑም ወነአምን በአሐቲ ጥምቀት ለሥርየተ ኃጢአት ወደ አማርኛ ስተረጉመው ኃጢአት በሚሠረይባት በአንዲት ጥምቀት እናምናለን የሚል ትርጉም የሚሰጠን ነውና ይህንኑ ሃሳብ በስፋት እና መጽሐፍቅዱሱ በሚሰጠን ሃሳብ መሠረት እንመለከተዋለን 1ኛ) መጽሐፍቅዱሳችን በኤፌሶን 4 ፥ 4 ላይ በመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደ ተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ ይለናልና 2ኛ ) በትምህርታችን አሁንም ያቺ አንዲት ጥምቀት የተባለችው እንደ መጽሐፍቅዱሳችን ቃል ማንና ምን እንደሆነች ምን እንደምትመስል በሰፊው የምናይበት ጉዳይ ይሆናል 3ኛ ) በጥምቀት ዙርያ ይህቺው ጥንታዊትና ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን እንደ እግዚአብሔር ቃል የሆነ ጠንካራ ጎንዋና መረዳትዋ እንዲሁም የቀድሞ ትምህርትዋ ምን እንደሚመስል እንመለከታለን 4ኛ) በጥምቀት ዙርያ አሁንም የቤተክርስቲያኒቱ ጠንካራ እና መጽሐፍቅዱሳዊ ያልሆኑ ብሎም ሊታደሱ ሊስተካከሉና ሊለወጡ የሚገባቸው ጎንዎችዋ እንደገናም በአሁኑ ዘመን ሳይቀር ያለው የትምህርት ይዞታዋ ምን እንደሚመስል ሰፋ አድርገን የምንቃኝበት የትምህርት ክፍለ ጊዜ ነው ይህ ትምህርት በቪድዮ ተዘጋጅቶ በየተራ የሚለቀቅ ስለሆነ የሚለቀቀው ትምህርት ሳያመልጣችሁ ሁሉንም እንድትከታተሉ በጌታ ፍቅር ለመጋበዝ እወዳለሁ አነሳስቶ ላስጀመረን አስጀምሮም ላስፈጸመን ለልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን የትምህርቱ አዘጋጅ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ የ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ .