Sunday, December 28, 2014

Joshua Tehadso: የተወደዳችሁ ወገኖቼ ዛሬ ደግሞ የምንማማርበት ሃሳብ Joshua Breakthro...

Joshua Tehadso: የተወደዳችሁ ወገኖቼ ዛሬ ደግሞ የምንማማርበት ሃሳብ Joshua Breakthro...: የተወደዳችሁ ወገኖቼ ዛሬ ደግሞ የምንማማርበት ሃሳብ  Joshua Breakthrough Renewal Teaching and  Preaching Ministry       በሚለው አገልግሎት ዙርያ ለአማኞች...

የተወደዳችሁ ወገኖቼ ዛሬ ደግሞ የምንማማርበት ሃሳብ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry

የተወደዳችሁ ወገኖቼ ዛሬ ደግሞ የምንማማርበት ሃሳብ  Joshua Breakthrough Renewal Teaching and 

Preaching Ministry

 

 

 በሚለው አገልግሎት ዙርያ ለአማኞችና ለአገልጋዮች የሚሆን ትምህርት ማቅረብ ብቻ ሳይሆን ኦርቶዶክስን ወደ ጥንተ መሠረቷ ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነትና ወደ ወንጌል ሃሳብ እንድትመለስ የሚያስችሉ መሠረታዊ የእግዚአብሔር ቃል እውነቶች በተለያዩ መጻሕፍቶችዋ ላይ ሠፍረው ስላሉ እነዛን እውነቶች ከእግዚአብሔር ቃል ጋራ በማገናኘትና በማመሳከር የተለያዩ ትምህርቶችን ማቅረባችን ይታወሳል አሁንም እንደሚከተለው እናቀርባለን ይህንን ትምህርት መከታተል ለምትፈልጉ ሁሉ ይህ አገልግሎት የኔ አገልግሎት ብቻ ሳይሆን ሁላችሁንም የሚመለከት አገልግሎት ስለሆነ የዚህ አገልግሎት ተባባሪና ደጋፊ በመሆን አገልግሎቱ ለብዙዎች እንዲደርስ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ማድረግ የምትችሉ መሆናችሁን ከወዲሁ ላሳስብ እወዳለሁ እግዚአብሔር ይባርካችሁ
 
     ዛሬ የምንመለከተው ሃይማኖተ አበው በተባለው  አንጋፋ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ላይ የሠፈሩ አስደናቂ የሆኑ የእግዚአብሔር ቃል ሃሳቦች ሲሆኑ ከእነርሱም መካከል አንዱን በስፋት ልንማማርበት እንመለከተዋለን ሃሳቡ እንዲህ የሚል ነው

                           ወበከመ ደክመ ከማሁ ነአምር ከመ ውእቱ አዕረፈ
                            ሥሩሐነ ወክቡዳነ ፆር




         ትርጉም    እንደ ደከመ  እንዲሁ የደከሙትን የኃጢአት ሸክም  የከበደባቸውን
                        እንዳሳረፈ እናውቃለን ይላል

                          ሃይማኖተ አበው  ዘሄሬኔዎስ ምዕራፍ 7 ቁጥር 23

                          ከዚሁ ሃሳብ ጋራ በተያያዥነት የማቴዎስ ወንጌል 11 28
                          እና የዮሐንስ ወንጌል 4 6 ጠቅሶአል ክፍሉን መጽሐፉ ያለበት ድረስ በመሄድ ገልጻችሁ ማንበብና መረዳት ትችላላችሁ

           የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ወገኖቼ ዛሬ እንግዲህ ይህ ሃይማኖተ አበው ያሰፈረውን ሃሳብ የትም ሳንሄድ ከዚሁ ከጠቀሳቸው ከእግዚአብሔር ቃሎች ጋራ በማገናዘብ የምናየው ይሆናል ይኸው ሃይማኖተ አበው ኢየሱስ እንደ ደከመ በመግለጽ እንዲሁ የደከሙትን የኃጢአት ሸክምም የከበደባቸውን እንዳሳረፈ እናውቃለን ይለናል ኢየሱስ የደከመበትን ቦታ ከዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 4 ቁጥር 6 ሄደን እንድንመለከት ጋብዞናል እርሱን ክፍል ሄደን በቅድሚያ እንመለከታለን በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 4 ቁጥር 6 ላይ ወሀሎ ህየ ዐዘቅተ ማይ ዘያዕቆብ ወደኪሞ እግዚእ ኢየሱስ በሐዊረ ፍኖት ነበረ ህየ ኀበ ውእቱ አዘቅት ወቀትር ሶቤሃ ጊዜ ስሱ ሰዓት ይለናል ወደ አማርኛው ስንተረጉመው   በዚያም የያዕቆብ ጕድጓድ ነበረ ኢየሱስም መንገድ ከመሄድ ደክሞ በጕድጓድ አጠገብ እንዲህ ተቀመጠ፤ ጊዜውም ስድስት ሰዓት ያህል ነበረ የሚል ነው ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ፍጹም አምላክ ቢሆንም በሥጋ ከዳዊት ዘር የመጣ በመሆኑ ፍጹም ሰው ነው በሥጋ ከዳዊት ዘር ለመምጣቱ የተቆጠረበትን የሥጋ ነገድ ከማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 1 1 ላይ የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ ስለሚል ከእርሱ መረዳት እንችላለን እንደገናም በሥጋ ተገልጦ በምድር በሚመላለስበት ጊዜ ብዙዎች የዳዊት ልጅ ይሉት እንደነበረ ከዚህም ሌላ የዳዊት ልጅ ሆይ ማረን እያሉ ይጠሩት እንደነበር ከክፍሉ ሄደን መመልከት እንችላለን የማቴዎስ ወንጌል 9 27 ማቴ 12 23 ማቴ 15 22 ማቴ 20 30 እና 31 ማቴ 22 41 _ 42 የማርቆስ ወንጌል 10 47 _ 48 ማር 12 35 የሉቃስ ወንጌል 18 38 _ 39 ሉቃ 20 41 ከዚህም ሌላ በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 1 31 _ 33 ላይ ወናሁ ትጸንሲ ወትወልዲ ወልደ ወትሰምይዮ ስሞ ኢየሱስ ውእቱ ዐቢይ ወይሰመይ ወልደ እግዚአብሔር ልዑል ወይሁቦ እግዚአብሔር አምላክ መንበረ ዳዊት አቡሁ ወይነግሥ ለቤተ ያዕቆብ ለዓለም ወአልቦ ማኅለቅት ለመንግሥቱ ትርጉም እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘለላም ይነግሣል፥ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም ይለናልና  የዳዊትን መንግሥት የያዘ በመሆኑ በጌታ ስም የምትመጣ የአባታችን የዳዊት መንግሥት የተባረከች ናት፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ያመሰግኑትም ነበር የማርቆስ ወንጌል 11 10  የዳዊት መክፈቻም ይለዋል በትንቢተ ኢሳይያስ 22 22 ላይ በትንቢታዊ ቃል የዳዊትንም ቤት መክፈቻ በጫንቃው ላይ አኖራለሁ እርሱም ይከፍታል የሚዘጋም የለም እርሱም ይዘጋል የሚከፍትም የለም ይላል በራዕይ 3 7 ላይ ደግሞ በፊልድልፍያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ የዳዊት መክፈቻ ያለው፤ የሚከፍት፥ የሚዘጋም የሌለ፤ የሚዘጋ፥ የሚከፍትም የሌለ፤ ቅዱስና እውነተኛ የሆነው እርሱ እንዲህ ይላል ይለናል የዳዊት ሥር ይለዋል በራዕይ 5 ላይ ከሽማግሌዎቹም አንዱ አታልቅስ፤ እነሆ፥ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል አለኝ እንደገናም  በራዕይ 22 16 ላይ እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፥ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ አለ ታድያ ኢየሱስ የዳዊት ልጅ ብቻ ሳይሆን የአብርሃምም ልጅ በመሆኑ የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም ተባለ የማቴዎስ ወንጌል 1 ዕብራውያን 2 16  በመሆኑም  ይህ የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ ተብሎ ሥጋን የለበሰውና እኛንም ለማዳን የመጣውን ጌታ ነው መንገድ ከመሄድ ደክሞ በጕድጓድ አጠገብ እንዲህ ተቀመጠ፤ ጊዜውም ስድስት ሰዓት ያህል ነበረ በማለት ዮሐንስ የተረከልን ኢየሱስ ፍጹም አምላክ ቢሆንም ፍጹም ሰውም ነውና የደከመ ብቻ ሳይሆን የተራበ የተጠማ ከኃጢአት በስተቀር በሰው ልጅ ሁሉ ላይ የሆነው ነገር ሁሉ የሆነበት ጌታ ነው ስለዚህም የዕብራውያን ጸሐፊ ስለዚህ የሕዝብን ኃጢአት ለማስተስረይ፥ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን፥ በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው እርሱ ራሱ ተፈትኖ መከራን ስለ ተቀበለ የሚፈተኑትን ሊረዳቸው ይችላልና አለን ዕብራውያን 2 17 እና 18 በመሆኑም የሕዝብን ኃጢአት በማስተስረይ ጉዳይ የታመነ ሊቀ ካህናት ሆኖ የሚምር ኃጢአትንም የሚያስተሰርይ ከኢየሱስ በቀር  ማንም የለም ለዚህም ነው የሃይማኖተ አበው ጸሐፊ እንደ ደከመ  እንዲሁ የደከሙትን የኃጢአት ሸክም የከበደባቸውን እንዳሳረፈ እናውቃለን ያለን የኃጢአትን ሸክም የሚያሳርፍ የሚምር ኃጢአትንም የሚያስተሠርይ ኢየሱስ ብቻ ነው በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 9 1 _ 8 የተጻፈውን ሃሳብ ስንመለከት እነሆ በአልጋ የተኛ ሽባን ወደ እርሱ አመጡ ይለናል ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን አንተ ልጅ አይዞህ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ አለው በዚህን ጊዜ ከጻፎች አንዳንዶች በልባቸው ይህስ ይሳደባል ባሉት ጊዜ ነው ኢየሱስ ሁለት ዓይነት እርምጃዎችን ሲወስድ የምንመለከተው (1ኛ) እምነታቸውን አይቶ አንተ ልጅ አይዞህ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ አለ (2ኛ) ነገር ግን በምድር ላይ ኃጢአትን ያስተሠርይ ዘንድ ለሰው ልጅ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ ብሎ ሽባውን ተነሣ አልጋህን ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ አለው ተነስቶም ወደ ቤቱ ሄደ ሕዝቡም አይተው ተደነቁ ለሰውም እንዲህ ያለ ሥልጣን የሰጠ እግዚአብሔርን አከበሩ ይለናል ስለዚህ በምድር ላይ ኃጢአትን ያስተሰርይ ዘንድ ሥልጣን ያለው ኢየሱስ ብቻ ነው ከኢየሱስ ውጪ ይሄን ሊያደርግ የሚችል ማንም ባለ ሥልጣን የለም እንደገናም ይሄ ጌታ በኃጢአት ምክንያት የመጣውን ሽባነትና የአልጋ ቁራኝነት ኃጢአትህ ተሰርዮልሃል በማለትና አልጋ በማሸከም አስወገደ ከዚህ የተነሳ ነው እንግዲህ በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 11 28 _ 30 ላይ ንዑ ኀቤየ ኩልክሙ ስሩሐን ወፅዑራን ወክቡዳነ ፆር ወአነ አዐርፈክሙ ንሥዑ አርዑትየ ላዕሌክሙ ወተመሀሩ እምኔየ እስመ የዋህ አነ ወትሑት ልብየ ወትረክቡ ዕረፍተ ለነፍስክሙ እስመ አርዑትየ ሠናይ ወፆርየኒ ቀሊል ውእቱ የሚለን ወደ አማርኛው ስንተረጉመው እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና የሚል ነው ማለቱ ነው የኃጢአት ሸክማችንን ከላያችን ሊያወርድልን የታመነው ሊቀ ካህናችን ኢየሱስ እያለልን ሸክምን ለማውረድ ወደ ልዩ ልዩ ቦታዎች በመሄድ አንንከራተትም በገደል ውስጥ አንሾልክም ሽቅብ አቀበትና ተራራም ላይ አንወጣም ቁልቁለቱንም ደግሞ እንዲሁ አንወርድም አፈሩንም እፍ ብላችሁ  ባዶ መሬት ላይ ካልቻላችሁ ደግሞ ሠሌን ላይ ተኙም አንባልም  ከዚህም ሌላ የተለያዩ ነፍስ አባቶችንም ነፍስ አባት ሁኑን አናዙን ፍቱን ይቅር በሉን ስንል አናስቸግራቸውም የሚፈታው ጌታ የታመነ ሊቀ ካህን ስለሆነ እርሱ በደሙ ያጥበናል ይቅርም ይለናል ለአንዴና ለዘላለምም ከእስራታችን ይፈታናል  ለመንግሥቱም መጨረሻ የሌለው በመሆኑ እኛን የሚያኖረን በዘላለም መንግሥት ውስጥ ነው የዳዊት መክፈቻ  ያለው የሚከፍት፥ የሚዘጋም የሌለ፤ የሚዘጋ፥ የሚከፍትም የሌለ፤ ቅዱስና እውነተኛ የሆነው እርሱ እንዲህ ይላል ስላለን ቃሉም በራዕይ መጽሐፍ ምዕራፍ 1 17 ላይ ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ ቀኝ እጁንም ጫነብኝ እንዲህም አለኝ፦ አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥ ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ በማለቱ ምክንያት  በዚህ ብቸኛ የደህንነታችን መንገድ በሆነው በኢየሱስ በማመናችን  ከሞትና ከሲኦል አምልጠናል እንግዲህ ጥንታዊት ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊትና ዓለማቀፋዊት የሆናችዋ የመጀመርያይቱ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን የምታስተምረው ትምህርት ይህ ነው ይህ ትምህርት በዚህ የሚያቆም ሳይሆን የሚቀጥል በመሆኑ ቅዱሳን ወገኖች ቃሉን የምታነቡና የምትከታተሉ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች በሙሉ የሚቀጥሉትን ትምህርቶች  ሁሉ  በማስተዋል እንድትከታተሉ በጌታ ፍቅር እጋብዛለሁ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን


ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ