Wednesday, May 27, 2015

Joshua Tehadso: በንቃት መጽሐፍቅዱስን ማንበብና ማጥናት Actively Read and Stu...

Joshua Tehadso: በንቃት መጽሐፍቅዱስን ማንበብና ማጥናት Actively Read and Stu...: በንቃት መጽሐፍቅዱስን ማንበብና ማጥናት Actively Read and Study the Bible ክፍል አንድ የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተ...

በንቃት መጽሐፍቅዱስን ማንበብና ማጥናት Actively Read and Study the Bible ክፍል አንድ

በንቃት መጽሐፍቅዱስን ማንበብና ማጥናት


Actively Read and Study the Bible


ክፍል አንድ


የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ  2 ጢሞቴዎስ 2 15 እንደገናም በኤፌሶን 1 13 ላይ እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ ይለናል በመሆኑም መጽሐፍቅዱሳችንን በንቃት ከምንጊዜውም በተለየ ሁኔታ የምናጠናበት ምክንያት ቃሉ የእውነት ቃልና የመዳን ቃል ስለሆነ ነው ታድያ ይህ የእውነት ቃልም ሆነ የመዳን ቃል አምነን ስንከተለው እንድንሆንለት የሚፈልገው ነገርና የሚያደርገንም ነገር አለ እንድንሆንለት የሚፈልገው ነገር ቃሉን በቅንነት የምንናገርና የማናሳፍር ሠራተኛ ሆነን የተፈተነውን ራሳችንን ለእግዚአብሔር ልናቀርብ መትጋት የሚያደርገን  ነገር ደግሞ ይህንን የእውነትን ቃልና የመዳንን ወንጌል ሰምቶ መቅረት ብቻ ሳይሆን ሰምቶ በክርስቶስ በማመን በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ መታተም ነው  ታድያ ይህ  ሊሆን የሚችለው ግን  በንቃት መጽሐፍቅዱስን ማንበብና ማጥናት ስንችል ነው ከዚህም ሌላ ይሄ የእውነት ቃል ለፍጥረቱ የበኲራት ዓይነት እንድንሆን መንፈሳዊ ልደትን የሚሰጠን  ነው ለዚህም ነው በያዕቆብ 1 18 ላይ ለፍጥረቱ የበኵራት ዓይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን የሚለን በመሆኑም በቆላስያስ 1 15 ላይ እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል ስለዚህ ይሄ ጌታ ለፍጥረቱ የበኵራት ዓይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ የወለደን ብቻ ሳይሆን በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋል ስለሚለን  ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥረዋል ስለሆነም መጽሐፍቅዱሳችንን በንቃት ስናነብና ስናጠና እንግዲህ ይህ የእውነት ቃል የሥነፍጥረት ፈጣሪና መገኛ መሆኑን የበኲራት ዓይነት የሆንበትን መንፈሳዊ ልደት አስገኚ መሆኑንም ጭምር እናይበታለን ለዚህም ነው ጊዜያችንን በእቅድና በመደበኛነት አስተካክለን በንቃት መጽሐፍቅዱሳችንን ለማንበብና ለማጥናት የተዘጋጀን እንድንሆን የሚያስፈልገን እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ ቀኖች ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ ስለዚህ የጌታ ፈቃድ ምን እንደሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ ሲል ሐዋርያው የጻፈልን ኤፌሶን 5 15 _ 17 በጊዜና በእቅድ ውስጥ ሆኖ በመደበኛነት መጽሐፍቅዱሱን በንቃት ለማንበብና ለማጥናት የሚተጋ ሰው ጥበበኛና እንዴት እንዲመላለስ የተጠበቀ የቀኖችን ክፋት የሚያውቅ የጌታን ፈቃድ ያስተዋለ ነው ይህ ሰው እንዲህ ሲሆን ታድያ ዘመኑን ሳይቀር እየዋጀ በውጪ ባሉት ዘንድ በጥበብ ጭምር የሚመላለስ ነው ቆላስያስ 4 5 መጽሐፍቅዱሳችን አሁንም በኤፌሶን 5 10 ላይ እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ እያለን በተደጋጋሚ የሚናገረን ለዚህ ነው ጌታ በምናነበው ቃል ይባርከን ተባረኩልኝ


ለተጨማሪ እነዚህን ሃሳቦች በእንግሊዝኛም ጭምር በጥቂቱ  አብራራቸዋለሁ እና ተከታተሉ
1-          Actively Read and study the Bible
2-       Plan time for regular study

It`s easy to let everyday concerns interfere so schedule study time and try to maintain it. Over time you will look forward to this daily experience.

Servant of Lord Priest and Preacher Yonas Getaneh


Friday, May 22, 2015

Joshua Tehadso: የእግዚአብሔርን ቃል እንዴት እንረዳለን ? ክፍል ሦስት በትሕ...

Joshua Tehadso: የእግዚአብሔርን ቃል እንዴት እንረዳለን ? ክፍል ሦስት በትሕ...: የእግዚአብሔርን ቃል እንዴት እንረዳለን   ? ክፍል ሦስት በትሕትና የእግዚአብሔርን መመርያና እርማት በመፈለግ አቤቱ፥ የሰው ...

የእግዚአብሔርን ቃል እንዴት እንረዳለን ? ክፍል ሦስት በትሕትና የእግዚአብሔርን መመርያና እርማት በመፈለግ

የእግዚአብሔርን ቃል እንዴት እንረዳለን ?




ክፍል ሦስት


በትሕትና የእግዚአብሔርን መመርያና እርማት በመፈለግ


አቤቱ፥ የሰው መንገድ ከራሱ እንዳይደለ አውቃለሁ፥ አካሄዱንም ለማቅናት ከሚራመድ ሰው አይደለም
አቤቱ፥ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ በመጠን ይሁን እንጂ በቍጣ አይሁን  ትንቢተ ኤርምያስ 10 23 _ 24




በትሕትና የእግዚአብሔርን እርማት የምንፈልግበት ምክንያት የሰው መንገድ ከራሱ አይደለም እንደገናም አካሄዱንም ለማቅናት ከሚራመድ ሰው አይደለም ስለሚለን ለአንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ለሁል ጊዜ በትሕትና የእግዚአብሔርን መመርያና እርማት ለሕይወታችን እንፈልጋለን መጽሐፍቅዱሳችን በሮሜ 8 6 _ 9  ላይ ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም ተስኖታል በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም እናንተ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ በመንፈስ እንጂ በሥጋ አይደላችሁም የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለም ይለናል በሥጋ ስናስብ ሁልጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር ጠበኞች ነን ለእግዚአብሔርም ሕግ አንገዛም እንገዛ ብንልም እንኳ የሚሳነን ሆነን እንገኛለን እግዚአብሔርንም ማስደሰት አንችልም ለዚህ ነው ኤርምያስ በትንቢቱ አቤቱ፥ የሰው መንገድ ከራሱ እንዳይደለ አውቃለሁ፥ አካሄዱንም ለማቅናት ከሚራመድ ሰው አይደለም በማለት ሳያበቃ በሥጋ የተጓዘባቸው መንገዶች አካሄዱንም ለማቅናት የተራመደበት ጐዳናዎች  ቅጣትን እንዳመጡበት የተገነዘበ በመሆኑ አቤቱ፥ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ በመጠን ይሁን እንጂ በቍጣ አይሁን ሲል አምላኩን የተማጸነው ከዚህ የተነሳ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኛ ዘንድ መኖሩ አስፈላጊነቱ ለዚህ ነው በመንፈስ እንጂ በሥጋ እንድንሆን አያደርገንም እንደገናም የእርሱ የእግዚአብሔር ወገን ለመሆናችን በውስጣችን ያለው የክርስቶስ መንፈስ ያረጋግጥልናል ሌላው በትሕትና የእግዚአብሔርን መመርያና እርማት የምንፈልግበት ምክንያት እግዚአብሔር ፍጹማን ሊያደርገን ስለሚፈልግ ነው በማቴዎስ ወንጌል 5 48 ላይ እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ ይለናል ስለዚህ አባታችን ፍጹም ወደ ሆነበት የፍጽምና ሕይወት ለመምጣት የእግዚአብሔርን መመርያና እርማት በትሕትና መፈለግ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው ለዚህ ነው በትንቢተ ኢሳይያስ 66 2 ላይ እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው ይላል እግዚአብሔር ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ ያለን እንደገናም በዚሁ በትንቢተ ኢሳይያስ 66 5 ላይ በቃሉ የምትንቀጠቀጡ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ የጠሉአችሁ ስለ ስሜም ያባረሩአችሁ ወንድሞቻችሁ  ደስታችሁን እናይ ዘንድ እግዚአብሔር ይክበር ብለዋል ነገር ግን ያፍራሉ ይለናል ስለዚህ በመጥላትና በማሳደድ ሕይወት ውስጥ ሆነን እና  እግዚአብሔርም ሲከብር አይተን ከሚያፍሩት ወገኖች ከምንሆን ይልቅ በትሕትና እና በተሰበረ መንፈስ በቃሉ ወደምንንቀጠቀጥበት ሕይወት መጥተን እግዚአብሔር ቢመለከተን ለእኛ እጅግ የተሻለ ነው መዝሙረኛው ዳዊት በቃሉ ወደሚንቀጠቀጥበት ሕይወት ስለመጣ ራሱን እና ማንነቱን በሙሉ ለተገለጠው ለእግዚአብሔር ቃል አሳልፎ በመስጠት አቤቱ፥ መርምረኝ ልቤንም እወቅ ፍተነኝ መንገዴንም እወቅ በደልንም በእኔ ውስጥ ብታገኝ እይ የዘላለምንም መንገድ ምራኝ  አለ መዝሙር 138 (139) 23 እና 24 ታድያ እኛም እንደ ዳዊት በዘላለም መንገዱ እንድንመራ ለተገለጠው ለእግዚአብሔር ቃል እራሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥና ሕይወታችንንም ለእርሱ እንድናስመረምር በእጅጉ ያስፈልገናል እግዚአብሔር ለዚህ ይርዳን ከዚህ በመቀጠል ጥቂት ሃሳቦችን በእንግሊዝኛ ለተጨማሪ ማብራርያነት ይበልጥ እንዲረዳ መስጠት እፈልጋለሁና ተከታተሉ ጌታ ይባርካችሁ

Keep an open mind

Be willing to admit when you are wrong and change even if it means letting go of a long held belief or tradition. If u can successfully apply this one principle you will be for a head in the search for spiritual truth. Act 17 : 11, Isaiah 8 : 20.


ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ