Saturday, January 3, 2015

የ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry የአገልግሎቱ ተልዕኮና መሠረታዊው ዓላማ

Joshua Breakthrough Renewal Teaching and 
Preaching Ministry
 

የአገልግሎቱ ተልዕኮና መሠረታዊው ዓላማ



የተወደዳችሁ ወገኖች የእግዚአብሔር ቅዱሳን እና ይህንን አገልግሎት ባላችሁበት በማንኛውም ቦታ በማስተዋል ሆናችሁ  የምትከታተሉ ወገኖች በሙሉ ባለፉት ለተከታታይ ሳምንታት የአባ ዘውዱ ኪዳኑን ምስክርነት አስመልክቶ በአጭር በአጭሩ እስከ ክፍል ሦስት የሚደርስ አስደናቂ የሆነ የሕይወት ምስክርነት ማቅረቤ ይታወሳል ዛሬ ግን ከዚሁ ጋር አያይዤ ልገልጽ የምፈልገው ይህ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and 
      Preaching Ministry  እንዲህ ዓይነት ምስክርነት ካላቸው ሰዎች ጋር አገልግሎቱ የተያያዘ ስለሆነ የጆሽዋ ሚኒስትሪን ዓላማ በይበልጥ ለእናንተ ለመግለጽ ነው

1ኛ) Joshua Breakthrough Renewal Teaching and 
      Preaching Ministry
           ጽንሰ ሃሳብ

ይህ ሚኒስትሪ ዛሬ ላይ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and 
      Preaching Ministry
 የሚለውን ስያሜ አግኝቶ በይፋ ይንቀሳቀስ እንጂ ከዛሬ ሃያ ሦስትና ሃያ አራት ዓመት በፊት እኔ ገና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እናት ቤተክርስቲያን ባዘጋጀችው ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጄ ውስጥ በመማር ላይ ሳለሁ ድንገተኛ በሆነ ሁኔታ በበራው የወንጌል ብርሃንና የደኅንነት ቃል ነው እንቅስቃሴው የተጀመረው በቃሉ ላይ ተጽፎ እንደምንመለከተው በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት ብርሃን እንዲሰጥ በልባችን ውስጥ የበራ በጨለማ ብርሃን ይብራ ያለ እግዚአብሔር ነውና ስለሚል እግዚአብሔር ይብራ ሲል የሚከለክለው የለምና በ1980ዎቹ ላይ በተለኮሰው ከሰማይ በሆነው የወንጌል ችቦ ይሄ አገልግሎት ተጀመረ 1 ቆሮንቶስ 4 6 ስለዚህ እኔና መሰሎቼን ለአገልግሎቱ የጠራን ታማኝ አድርጎም የቆጠረን ሰው ሳይሆን እግዚአብሔር ነው እግዚአብሔር ሲጠራን ደግሞ የጠራን በራዕይና በተልዕኮ ነው 1 ወደ ጢሞቴዎስ 1 : 12 ለዚህ ጉዳይ ጥሩ ማስረጃ የሚሆነን ሐዋርያው ጳውሎስ ነው ሐዋርያው ጳውሎስን ሐናንያ እንዲህ ነበር ያለው ጳውሎስም ይህንኑ እንዲህ ሲል ተናገረ እርሱም አለኝ የአባቶቻችን አምላክ ፈቃዱን ታውቅ ዘንድና ጻድቁን ታይ ዘንድ አስቀድሞ መርጦሃል ባየኸውና በሰማኸው በሰው ሁሉ ፊት ምስክር ትሆንለታለህና አሁንስ ለምን ትዘገያለህ ? ተነሣና ስሙን እየጠራህ ተጠመቅ ከኃጢአትህም ታጠብ ስለዚህ ጳውሎስ ለዚህ አገልግሎት አልዘገየም ወዲያው ተነሳ ታድያ ጳውሎስ ለአገልግሎት የመነሳቱ ትልቁ ምስጢር ከኃጢአት መታጠቡ ብቻ ሳይሆን በመንፈስቅዱስም ሳይቀር መጠመቁ ነበር በእኔና በመሰሎቼም ሕይወት የሆነው ይሄ ነው እኛ የሌላ ሠፈር ሰዎች ነበርን በአባ ዘውዱ ምስክርነት ላይ በሰፊው በገለጽኩት መሠረትም  መንገዳችን ሳይቀር ሌላ የነበረ ሰዎች ነን ጌታ ግን ስለወደደን የደኅንነቱ ብርሃን እንዲበራ በሕይወታችን ፈቀደና በደሙ ከኃጢአታችን መታጠብ መንጻት ብቻ ሳይሆን ለአገልግሎቱ ሥራ ሳይቀር ብቁ እንድንሆን በመንፈሱ አጠመቀን ስለዚህ ከራሳቸው ነገር ይልቅ እንደ ሐናንያ የጌታ ሥራ  ግድ  የሚላቸው እስከ ዛሬ ድረስ መልዕክታቸው ተነሣ አሁንስ ለምን ትዘገገያለህ ? የሚል ሲሆን ያልገባቸው ሰዎች ደግሞ  ለምን ተነሣህ ? አትቆይም ? አትዘገይም እንዴ የሚል ነው እኛ ግን ይሄን ሁሉ ድምጽ አልፈን ከተነሣን ዓመታቶች ተቆጥረዋል ስለዚህ ዛሬ
ካየነው ካወቅነውና ከሰማነው ድምጽ የተነሳ ተነሣና አትነሣ በሚለው ነገር ውስጥ አይደለንም  በመሠረቱ ፈጥኖና ተቻኩሎ ከመነሣት ይልቅ አለመነሣት መዘግየትና መቆየት ለብስለት ለዕድገት የተሻለም ነገር ለማምጣት ዓይነተኛ መንገድ ነው ብለን ብናምንም መጽሐፉ ባመዛኙ ሰዎችን ለውጤት ለማብቃት  የሚናገር በመሆኑ እግዚአብሔር በሚሰጠው ጊዜ ከብስለት ከማጣጣምና ከመረዳት ጋር የሆነ መነሣት አለና በመነሣት እናምናለን ሰዎችንም በዚህ እውነት ለወንጌል ሥራ ለቃሉ እውቀትና አስተምሕሮት እንደተሰጣቸው ጸጋ መጠን እንዲነሳሱና እንዲሮጡ እንደግፋለን እናነሳሳለን እናበረታታለን እንደገናም ከሚሮጡ ጋራ ራዕያችንም ገብቶአቸው አብረውን ሊሮጡም ከሚፈልጉ ጋራ  በጋራ መሮጥ እንፈልጋለን አለ አግባብ ግን ሰዎች መስራት በሚገባቸው ጊዜ ሳይሠሩ ቀርተው እና እንዲሁ ተቀምጠው ጊዜ እንዲያጠፉ አትቆይም ? አትዘገይም ነበር ? ቸኮልክ እኮ ? በማለት እንዲሁ በተለምዶ ቃል ብቻ የሰዎችን ወርቃማ የሥራ ጊዜ አናበላሽም ይህ አገልግሎት በ1980ዎቹ ላይ ከተነሳበት ጊዜ ጀምሮ በመከሩ የወንጌል ሥራ ላይ ተሠማርቶ ብዙ ፍሬ አፍርቶአል ብዙ ሰዎችንም ወደ ጌታ አምጥቶአል በጌታ ቃል አስታጥቆ ለአገልግሎትም አብቅቶአል በተለይም ካህናት ዲያቆናት መነኮሳትና የቤተክርስቲያኒቱ መዘምራን መሪጌቶች በዚህ አገልግሎት ውስጥ ተካተው በብዛት ወደ ጌታ መጥተዋል በ1990 ዓመተ ምሕረት የመነኮሳት ህብረት በሚል ለሁለት ቀን የተካሄደው አገልግሎትና ታላቅ ክሩሴድ ለዚሁ ራዕይ ፍንጭ የሚሰጥ የአገልግሎትንም በሮች ያስከፈተና ትልቅ ፈር ቀዳጅ አገልግሎት ነበር በዚህ አገልግሎት ውስጥ የተገለጹ ጥቂት  የማይባሉ ሃሳቦች ከዚህ እንደሚከተሉት ነበሩ [ ከናዝሬት መልካም ነገር ይወጣልን ? አዎን ይወጣል አሮጊቷ ሣራ ወልዳለች የሚሉና ሌሎችንም ስብከቶች ያካተቱ እንዲሁም እንቁላል እንቁላልነቱ የሚታወቀው በአስኳሉ ነው ወንጌል ወንጌልነቱ የሚታወቀው በጌታ ኢየሱስ ነው አስኳሉን ለማግኘት ቅርፊቱን ማስወገድ እንደሚያስፈልግ ሁሉ ኢየሱስን በብቸኛ አዳኝነቱ ለመቀበልና ለማግኘት ብዙ ነገሮችን መጣል መተውም እንዳለ መልዕክቶቹ ያመላክታሉ ]ምስክርነቶችንና ያሬዳዊ የሽብሸባ መዝሙሮችን የያዙም በመሆናቸው እንዲሁም ከወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት የታወቁ ዘማሪዎችን በአምልኮ ያካተተ በመሆኑ በጉባኤው ላይ የመንፈስቅዱስ ሕልውናና የጌታ መገኘት ስለነበረ ፕሮግራሙ ይበልጥ ውበት እንዲኖረውና ብዙዎችንም የሚስብ ሆኖ የቀረበ አድርጐታል መልዕክቱም ሆነ ምስክርነቱ ራዕዩ የተነሣበትንና መሠረታዊ ዓላማውንም ጭምር  በጉልህ የሚያሳይ በመሆኑ ብዙዎችን ያሳተፈ ነበር ማለት ይቻላል  ከዚያም በኋላ ይሄ ሕብረት እንዳይመሠረት እራሱን ችሎም እንዳይቆም የእግዚአብሔርንም ተልዕኮ እንዳያራምድ በብዙ የፈተና ማዕበሎችና እሳት ውስጥ አልፎአል ዝርዝር ሃሳቡን አሁን በእንዲህ ሁኔታ መግለጽ አያስፈልገኝም ነገር ግን ጌታ ብርታት ሆኖን አሁንም ባለንበት ሁኔታ ሁላችንም አለን ራዕዩም ከእኛ ባሻገር ዛሬ ላይ ብዙ መሪጌቶችንና ቀሳውስቶችን ወልዶ በተለያየ መልኩ የወንጌሉ እውነት በዚያው ቤት ውስጥ እየነደደ ይገኛል በገላትያ 4 26 ላይ አንቺ የማትወልጂ መካን ደስ ይበልሽ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ እልል በዪና ጩኺ ባል ካላቱ ይልቅ የብቸኛይቱ ልጆች በዝተዋልና ተብሎ ተጽፎአልና  አሮጊቷ ሣራም ከመካንነት ወጥታ ዛሬ ላይ ባለው ሕይወቷ የብዙ ልጆች እናት ልትሆን በቅታለች  ታድያ አገልግሎታችን ይህቺን እናት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ወደ ጥንተ መሠረቷ ወደ ወንጌል እውነት መመለስና ልጆችዋንም ሣራ እንደወለደችው እንደ ይስሐቅ የተስፋ ልጆች በነጻነት የምትኖር የላይኛይቱ ኢየሩሳሌም ሀገር ዜጐች ማድረግ ሲሆን አገልግሎታችን ከዚያ መልስ በዚች ቤተክርስቲያን ላይ ብቻ ያተኮረ አይደለም ተሻግሮም ወደ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት በመሄድ በእግዚአብሔር ቃልና በእግዚአብሔር ጸጋ በዚያ የሚገኙትን ቅዱሳንን ይጠቅማል  እየጠቀመም ይገኛል ምክንያቱም ጌታ የሚፈልጋት ቤተክርስቲያን አንዲት ቤተክርስቲያንን ነው አሠራር ልዩ ልዩ ቢሆንም  የወንጌልን ሥራ ስንሠራ  ግን  በእግዚአብሔር ዓላማ ውስጥ ገብተን የምንሠራው ለአንዲት ቤተክርስቲያን ነው ከዚህ በመቀጠል በክፍል ሁለት መልዕክቴ የጆሽዋ ሚኒስትሪን ዓላማ እንደሚከተለው አቀርበዋለሁ እስከዚያው የጌታ ሰላም ይብዛላችሁ ሰላም ሁኑ  በማለት የምሰናበታችሁ



ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ነኝ

No comments:

Post a Comment