Wednesday, May 20, 2015

የእግዚአብሔርን ቃል እንዴት እንረዳለን ? ክፍል ሁለት በትክክለኛ አመለካከት እግዚአብሔር እንዲረዳን መጠየቅ ?

የእግዚአብሔርን ቃል እንዴት እንረዳለን ?


ክፍል ሁለት


በትክክለኛ አመለካከት እግዚአብሔር እንዲረዳን መጠየቅ ?








እናንተ ትሹኛላችሁ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላች

ኤርምያስ 29 13


ለምን ይህ አስተሳሰብ በጣም ጠቃሚ ሊሆን ቻለ ?


ጳውሎስ ይህንን እንዲህ ሲል ይመልሳል ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ እግዚአብሔርም የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ ነገር የተናቀውንም ነገር ያልሆነውንም ነገር መረጠ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እንዳይመካ ይለናል 1 ቆሮንቶስ 1 27 በእግዚአብሔር መንፈሳዊ እውነት መረዳት ማንም ሰው መጎረርና መፎከር አይችልም ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቃል እውነት የራሱ የእግዚአብሔር ማስተዋል ነው የራሱ ጥረትና ሥልጠና ነው በሌላ መንገድ አንድ ሰው በትሕትና እግዚአብሔር እንዲረዳው ከጠየቀ እና የተማረውን ሊታዘዝ ከታመነ ለመረዳት እርሱ በትክክለኛ መንገድ ላይ ነው በማቴዎስ ወንጌል 18 3 _ 4 ላይ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይላል እንዲህም አለ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ካልተመለሳችሁ እንደ ሕፃናትም ካልሆናችሁ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም እንግዲህ እንደዚህ ሕፃን ራሱን የሚያዋርድ ሁሉ፥ በመንግሥተ ሰማያት የሚበልጥ እርሱ ነው አለን No matter how intelligent we may be , If we don’t humble our selves and become teachable like a small child , God will not help us to grasp his word  መልካምን ጥበብ ለማግኘት ትሑት መሆን እንደሚያስፈልግ በትሕትና ጥበብን ካገኘ ሰው ጋር እግዚአብሔር ይሠራል ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል ይለናል ያዕቆብ 1 5 መልካም ጥበብን ለማግኘት ትሕትናን የጠየቁ እና ሽልማት ካገኙ ሰዎች መካከል ዳዊት ሰለሞን ዳንኤል አስቴርና  እንዲሁም የመጀመርያ ደቀመዛሙርት ናቸው በሌላ መንገድ በራሳቸው ችሎታ የተመኩትን አዳምና ሔዋን ቃዬልን በመውጣት ጊዜ የግብጹ ፈርኦን የእሥራኤል ንጉሥ ሳኦል ንጉሥ ናቡከደነፆር የሃይማኖት አስተማሪዎችና ንጉሥ አግሪጳ የሐዲስ ኪዳንን ቤተክርስቲያን የተቃወመው ናቸው ተገቢ ትሕትናንና ጥሩ አስተሳሰብን ካሳዩት ሰዎች መካከል የቤርያ ሰዎችን መጥቀስ እንችላለን ወዲያውም ወንድሞች ጳውሎስንና ሲላስን በሌሊት ወደ ቤርያ ሰደዱአቸው፥ በደረሱም ጊዜ ወደ አይሁድ ምኵራብ ገቡ እነዚህም በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ልበ ሰፊዎች ነበሩና ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን፧ ብለው ዕለት ዕለት መጻሕፍትን እየመረመሩ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ ይለናል የሐዋርያት ሥራ 17 10 _ 12 እንደገናም በያዕቆብ መጽሐፍ ላይ ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ ቃሉን የሚሰማ የማያደርገውም ቢኖር የተፈጥሮ ፊቱን በመስተዋት የሚያይን ሰው ይመስላል ራሱን አይቶ ይሄዳልና፥ ወዲያውም እንደ ምን እንደ ሆነ ይረሳል ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ሕግ ተመልክቶ የሚጸናበት፥ ሥራንም የሚሠራ እንጂ ሰምቶ የሚረሳ ያልሆነው፥ በሥራው የተባረከ ይሆናል ይለናል ያዕቆብ 1 22 _ 25 አለን እግዚአብሔር የምናነበውን ቃል ይባርክልን



ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment