Wednesday, July 29, 2015

Joshua Tehadso: የጌታ እራት ዛሬ ለእኛ ምንድነው ? ክፍል ሰባት 3ኛ) ምልክታዊ ት...

Joshua Tehadso: የጌታ እራት ዛሬ ለእኛ ምንድነው ? ክፍል ሰባት 3ኛ) ምልክታዊ ት...: የጌታ እራት ዛሬ ለእኛ ምንድነው ? ክፍል ሰባት 3ኛ ) ምልክታዊ ትዕይንቶች እና እንቅስቃሴን    የሚፈጥር ኃይል ያለው ትዕይንት Symbolic View and ...

የጌታ እራት ዛሬ ለእኛ ምንድነው ? ክፍል ሰባት 3ኛ) ምልክታዊ ትዕይንቶች እና እንቅስቃሴን የሚፈጥር ኃይል ያለው ትዕይንት Symbolic View and The Dynamic View

የጌታ እራት ዛሬ ለእኛ ምንድነው ?


ክፍል ሰባት



3ኛ) ምልክታዊ ትዕይንቶች እና እንቅስቃሴን   የሚፈጥር ኃይል ያለው ትዕይንት


Symbolic View and The Dynamic View


በዚህ በክፍል ሰባት ትምህርታችን ላይ የምንመለከተው ምልክታዊ ትዕይንቶችን እና እንቅስቃሴን የሚፈጥር ኃይል ያለው ትዕይንትን ነው በእንግሊዘኛው  Symbolic View and The Dynamic View ይባላል ምልክታዊ ትዕይንቶች ( Symbolic View ) ኅብስቱና ወይኑ ክርስቶስ በሰውነቱ ለከፈለው እና ደሙን ላፈሰሰው ምልክት የሆነ ብቻ ነው እርሱ እንደተናገረው የጌታ እራት በመጀመርያ ክርስቶስ ለፈጸመው ሥራ ማስታወሻ ነው ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝቦች አንድነታቸውን በሚጠብቁበት ጊዜ ማለት እርስ በእርሳቸው ያላቸውን አንድነት ሲጠብቁ ከአንዱ ከክርስቶስ ጋር ናቸው ይህ ደግሞ በተጠመቀችና ነጻነት በወጣች ቤተክርስቲያን ያለና የተያዘ ትዕይንታዊ ነጥብ ነው ለዚህ ሃሳብና ድምጽ ደግሞ የበለጠ ቦታና ዋጋ በመስጠት በጌታ እራት ጊዜ ጌታ ያደረገውን ክርስቲያን የሚያደርገውና ቃል የሚገባበት ነው እንቅስቃሴን የሚፈጥርና ኃይል ያለው ትዕይንት
በእንግሊዘኛው The Dynamic View  የተባለው ደግሞ የመጨረሻው ጆን ካልቪን ለፕሪስፒቴርያን ቤተክርስቲያን ማሻሻያ የሰጠ የእርሱን ትምህርት The Dynamic View  የሚከተሉ ናቸው ይህ ዕይታ የመጨረሻ የሆነ የእርሱ ዕይታ ነው እርሱ በሉተርና በዝዊንግሊ መካከል አካባቢ የተነሳ ነው ካልቪን ከዝዊንግሊ ጋር የተስማማ ነው እርሱ እንደተረዳው ኅብስቱና ወይኑ ክርስቶስ በአካል ለመገኘቱ በጥንተ ነገሩ ሆኖ ምሳሌ የሆነ ነው ምክንያቱም አካሉ በሰማይ ተነስቶ ከብሮአል ( ዕብራውያን ፲፪ እና ፲፫ ) እስካሁን ድረስም እርሱ እንቅስቃሴን ኃይልን የሚፈጥር በእንግሊዘኛው The Dynamic View  ሲሆን በጌታ እራት ጊዜም በመንፈስቅዱስ አማካኝነት መንፈሳዊ መገኘት የሚያደርግ ነው ይለናል በአምልኮ አገልግሎትና የእግዚአብሔር ቃል በሚታወጅበት ጊዜ የጌታን እራት እንወስዳለን የከበረው ጌታ መንፈሳዊ መግቦቱን ከከበረው ሰውነቱ እርሱን ለተቀበሉ ይሰጣል በኅብስቱ መግቦቱ በሚታይ ሰውነቱ ክርስቶስ በሰውነቱ የከበረ ነውና ለነፍሳችን ሙሉ የሆነ ብሩህ ደስታንና ንቃትን ጉብዝናን ይሰጠናል ከክርስቶስ ጋር በሰውነት ወይም በአካል መካከል ካለ የሕይወትና የአንድነት ግንኙነት ምክንያት ራስ ሆኖ ለተነሳው ክርስቶስ በቤተክርስቲያን የእርሱ አካልና አባላት ነን ( ኤፌሶን 1 18 _ 23 ኤፌሶን 4 15 እና 16 ኤፌሶን 5 23 )ይህንን መግቦት ወደ ክርስቲያኖች የሚያዘዋውረው በእኛ በሚኖረው በመንፈስቅዱስ ነው ( ሮሜ 8 9 _ 11 )ይህ ካልቪን ያመነው የመንፈስቅዱስ መንገድ ደግሞ ምሥጢራዊ የሆነና መሳሳት የሌለበት መንገድ ነው የካልቪን ዕይታ በእነዚህ መጻሕፍት በትክክል የተጻፈ የእግዚአብሔር መግቦትና ሥልጣን በሕዝቡ ላይ የሚሠራ ነው (ኤፌሶን 3 14 _ 21 ቆላስያስ 2 6 _ 10 19 ) ምንጭ  New Alustrated Bible Dictionary  እና ከመሳሰሉት ተጠናክሮ የተወሰደ እግዚአብሔር  የምናነበውን ቃል ይባርክልን 

Joshua Breakthrough Renewal    Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ

ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ
                                                      


   

Monday, July 27, 2015

Joshua Tehadso: የጌታ እራት ዛሬ ለእኛ ምንድነው ? ክፍል ስድስት 2ኛ ) The C...

Joshua Tehadso: የጌታ እራት ዛሬ ለእኛ ምንድነው ? ክፍል ስድስት 2ኛ ) The C...: የጌታ እራት ዛሬ ለእኛ ምንድነው ? ክፍል ስድስት 2ኛ ) The Consubstantiation View ሁለተኛው የዕይታ ነጥብ የተገለጸው በማርቲን ሉተር ነው   ይህም ...

የጌታ እራት ዛሬ ለእኛ ምንድነው ? ክፍል ስድስት 2ኛ ) The Consubstantiation View

የጌታ እራት ዛሬ ለእኛ ምንድነው ?


ክፍል ስድስት


2ኛ ) The Consubstantiation View



ሁለተኛው የዕይታ ነጥብ የተገለጸው በማርቲን ሉተር ነው  ይህም የጌታ ሥጋና ደም በእውነት በእኛና በእኛ ውስጥ ማለት ባዘጋጀነው ዳቦና ወይን ውስጥ ይገኛል ጥንተ ነገሩ በእውነተኛነት ወደ ክርስቶስ ሥጋና ደም የሚለወጥ አይደለም ነገር ግን በአንድ ዓይነት መንገድ ሙቀቱ በጥንተ ነገር ውስጥ ይገኛል ስለዚህ በሉተራን ሁናቴ ይህ ጉዳይ ሁልጊዜ የሚጠራው Consubstantiation በመባል ነው ሁኔታው ክርስቶስ በእውነተኛነት በእራት ውስጥ ስላለ ይህንን በመገንዘብ ቅዱስ ቁርባኑን ለመቀበል ሊያበረታታ የሚችል ነው ነገር ግን የጌታን ቃል ቅርጽና መልክ መጠቀም ለማግኘት ያልቻለ ነው ከራሱ ከክርስቶስ ይልቅ በዳቦውና በወይኑ ላይ ሥዕሉን በማድረግ አትኩሮት የሰጠና ያዘነበለ ነው ይሁን እንጂ መጽሐፍቅዱሳችን የሚለን ይህንን ነው የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና ይለናል ሮሜ 14 17 እንደገናም መብል ግን ወደ እግዚአብሔር አያቀርበንም፤ ባንበላም ምንም አይጎድለንም ብንበላም ምንም አይተርፈንም ይለናል 1 ቆሮንቶስ 8 8 ከዚህም ሌላ እንግዲህ በመብል ወይም በመጠጥ ወይም ስለ በዓል ወይም ስለ ወር መባቻ ወይም ስለ ሰንበት ማንም አይፍረድባችሁ እነዚህ ሊመጡ ያሉት ነገሮች ጥላ ናቸውና፥ አካሉ ግን የክርስቶስ ነው በማለትም ይናገራል ቆላስያስ 2 16 እና 17 መጽሐፍቅዱሳችን እንደሚያስተምረን የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን ? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን ? አንድ እንጀራ ስለ ሆነ፥ እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን፤ ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና  በሥጋ የሆነውን እስራኤል ተመልከቱ፤ መሥዋዕቱን የሚበሉ የመሠዊያው ማኅበረተኞች አይደሉምን ? ይለናልና የምንቆርሰው እንጀራም ሆነ የምንወስደው የበረከት ጽዋ ይህንን ቃሉን ለተረዳን ለእኛ ትልቅ ትርጉም አለው ከጌታ ጋር ባለን ነገርና የእርስ በእርስ ግንኙነታችን አንድነታችንን የምናረጋግጥበት ነው ስለዚህ እንዲሁ የምንወስደው እንጀራም ሆነ የበረከት ጽዋ የለም እንደገናም የእግዚአብሔር ቃል የማይመሰክርልንን ቅርጽና መልክም የማይሰጠንና ያላስያዘልንን እራት የጌታ እራትም ሆነ የበረከት ጽዋ ነው ስንል አንወስድም ማንኛውንም ነገር የምናደርገው በዘፈቀደ ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ቃል ስለሆነ የእግዚአብሔርን ቃል ብቻ ተከትለን እናደርጋለን 1 ጴጥሮስ 4 11  2 ጴጥሮስ 1 19 የምንቆርሰው እንጀራም ሆነ የምንወስደው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ጋር ኅብረት ኖሮት ለእኛም ኅብረትን  የማይሰጠን ከሆነ እንደገናም የእርስ በእርስ ኅብረታችንንም ጭምር የማያጸናልን ከሆነ ያው የተለመደው በተፈጥሮ የምናውቀው  ዳቦና ወይን ነው ከዚህ የተለየ ትርጉምም ልንሰጠው አንችልም መጽሐፍቅዱሳችን ግን የምንቆርሰው እንጀራም ሆነ የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ጋር ኅብረት ያለው ስለሆነ ይህንን እንጀራም ሆነ የበረከት ጽዋ ስንካፈል በጥንቃቄ መሆን እንዳለበት ቃሉ ይነግረናል ለዚህም ነው ማንም የራበው ቢኖር ለፍርድ እንዳትሰበሰቡ በቤቱ ይብላ የቀረውንም በመጣሁ ጊዜ እደነግጋለሁ የሚለን 1 ቆሮንቶስ 11 27 _ 34 ከክርስቶስ ጋር ያልተገናኘን ኅብስትና ወይን እኛ አማኞች እንደ ቃሉ እንጂ በሉተራን ዓይን ተመልክተን ውሳኔ የምንሰጥበት አይሆንም ከክርስቶስ ጋር ያልተገናኘ ኅብስትና ወይን ክርስቶስ በእውነተኛነት በእራት ውስጥ ስላለ በአንድ ዓይነት መንገድ ሙቀቱ በጥንተ ነገር ውስጥ ይገኛል ብለን አናስብም የጌታን ቃል ቅርጽና መልክ መጠቀም ለማግኘት ያልቻለ እንደገናም ከራሱ ከክርስቶስ ይልቅ በዳቦውና በወይኑ ላይ ሥዕሉን በማድረግ አትኩሮት የሰጠና ያዘነበለ በመሆኑ ተራ ዳቦና ወይን ነው ከምንለው ውጪ ሌላ ትርጉም አንሰጠውም ወገኖቼ በዚህ ቃል ተባረኩ እያልኩኝ ይህንን ትምህርት እንድታነቡ እጋብዛለሁ በክፍል ሰባት ትምህርት እስክንገናኝ የጌታ ጸጋና ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን በማለት እሰናበታለሁ ተባረኩልኝ ለዘላለም



Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ

ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ