Wednesday, January 13, 2016

Joshua Tehadso: New Book from Yonas Getaneh Asfaw

Joshua Tehadso: New Book from Yonas Getaneh Asfaw: ሰላም ቅዱሳን ወገኖች የጌታ ሰላምና ጸጋ ይብዛላችሁ ከዚህ በመቀጠል ቤተክርስቲያንና አገልጋዮችዋ በሚል ርእስ በጌታ እርዳታ የሁላችሁ ታናሽ በሆንኩት በእኔ በባርያው ተዘጋጅቶ እና ተጽፎ የቀረበ ሲሆን ይህንን መጽሐፍ ለመግ...

New Book from Yonas Getaneh Asfaw

Yonas Asfaw's photo.ሰላም ቅዱሳን ወገኖች የጌታ ሰላምና ጸጋ ይብዛላችሁ ከዚህ በመቀጠል ቤተክርስቲያንና አገልጋዮችዋ በሚል ርእስ በጌታ እርዳታ የሁላችሁ ታናሽ በሆንኩት በእኔ በባርያው ተዘጋጅቶ እና ተጽፎ የቀረበ ሲሆን ይህንን መጽሐፍ ለመግዛትና ለመጠቀም ለምትፈልጉ ሁሉ መጽሐፉ ታትሞ የተሰራጨው በአዲስ አበባና በመላው ኢትዮጵያ በመሆኑ መጽሐፉንም የምታገኙት እዛው ኢትዮጵያ ነው በመሆኑም በሀገር ቤት በሀገራችን በኢትዮጵያና በመላው ዓለም የምትገኙ ቅዱሳን ሁሉ ይህንን መጽሐፍ ለማግኘት ኢትዮጵያ እስቴድዮም በሚገኘው የመሠረተ ክርስቶስ የመጻሕፍት መሸጫ መደብርና በሌላም ቦታዎች የሚገኝ በመሆኑ ገዝታችሁ እንድታነቡና እንድትጠቀሙ ለሌሎችም መግዛት እና መጠቀም ለሚፈልጉ ሁሉእንድታሰሙ በ Joshua Renewal Teaching and Preaching Ministry ስምና በራሴም ስም ላሳስባችሁ እወዳለሁ
አገልጋያችሁ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

Wednesday, January 6, 2016

Joshua Tehadso: የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ወይም የገና መልዕክት ወይቤሎሙ...

Joshua Tehadso: የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ወይም የገና መልዕክት 







ወይቤሎሙ...
: የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ወይም የገና መልዕክት   ወይቤሎሙ መልአክ   ኢትፍርሁ እስመ ናሁ እዜንወክሙ ዐቢየ ዜና ፍሥሐ ዘይከውን ለክሙ ወለኲሉ ...

M2U00105 የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ወይም የገና መልዕክት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ወይም የገና መልዕክት ወይቤሎሙ መልአክ ኢትፍርሁ እስመ ናሁ እዜንወክሙ ዐቢየ ዜና ፍሥሐ ዘይከውን ለክሙ ወለኲሉ ዓለም እስመ ናሁ ተወልደ ለክሙ ዮም መድኅን ዘውእቱ ክርስቶስ እግዚእ ቡሩክ በሀገረ ዳዊት ወንጌል ዘሉቃስ ምዕራፍ ፪ ቊጥር ፲ ትርጉም ፦ መልአኩም እንዲህ አላቸው፦ እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 2 ቊጥር 10 ይህ በ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry ሥር ተዘጋጅቶ የቀረበላችሁ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት መልዕክት ነው የተወደዳችሁ ብፁአን አባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ፣ አበው ሊቃውንት መምሕራን ፣ የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎች እንዲሁም አዕይንተ እግዚአብሔር ካህናት እና ዲያቆናት የሰንበት ትምህርት መምርያ ሃላፊዎች እና የሰንበት ተማሪዎች ፣ አስተማሪዎች ሕዝበ እግዚአብሔር ምዕመናን በሙሉ በቅድሚያ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ የከበረና ልባዊ ሰላምታዬን ሳቀርብ ይህ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ለሁላችንም የጤና ፣ የበረከት ፣ የደስታና የሰላም በዓል በያለንበት እንዲሆንልን እመኛለሁ በመቀጠልም ይህንን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት አስመልክቶ የተዘጋጀ ስብከተ ወንጌል ስላለኝ እርሱን ላቀርብላችሁ እወዳለሁ ከላይ በመግቢያዬ ላይ እንደገለጽኩት መልአኩም ይህንን የምሥራች መንጋቸውን በሌሊት በሜዳ ሲጠብቁ ላደሩ እረኞች ሲያበስራቸው ኢትፍርሁ እስመ ናሁ እዜንወክሙ ዐቢየ ዜና ፍሥሐ ዘይከውን ለክሙ ወለኲሉ ዓለም እስመ ናሁ ተወልደ ለክሙ ዮም መድኅን ዘውእቱ ክርስቶስ እግዚእ ቡሩክ በሀገረ ዳዊት ወደ አማርኛው ስተረጉመው እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና አላቸው ወገኖቼ የሚፈሩ ሰዎች በሰዎች ሳይሆን ከሰማይ በመጡ የመላዕክቱ አንደበት አትፍሩ ሲባሉ በእርግጥም ይህ ታላቅ ደስታና የምሥራች ነው ታድያ ይህ ፍርሃት በእረኞች ዙርያ የታየና እየታየም ያለ ፍርሃት ብቻ ሳይሆን የሕዝብ ሁሉ ፍርሃት ነው ይህ ፍርሃት ደግሞ የተፈጥሮ ፍርሃት ወይንም በተፈጥሮ የመጣ ማንኛውም ዓይነት ፍርሀት ብቻ ሳይሆን ኢየሱስ እስኪወለድ ፣ ተወልዶም ለሰው ልጆች ኃጢአት እስኪሞትና የሰው ልጆችንም ስለማጽደቅ ከሞት እስኪነሳ ድረስ ያለ የባርነትና የሞት ፍርሃት ነው መጽሐፍቅዱስ ሲናገር በመጀመርያ በግዕዙ ቃል እንዲህ ይላል ወካዕበ ይቤ አንሰ እትዌከል ቦቱ እስመ ደቂቅ ተሳተፉ በሥጋ ወደም ውእቱኒ ተሳተፈ በዝንቱ ወከመ ቢጾሙ ኮነ ሎሙ ከመ በሞቱ ይስዐሮ ለመልአከ ሞት ዘውእቱ ሰይጣን ወያዕርፎሙ ለኲሎሙ እለ በፍርሀተ ሞት ተኰነኑ በኲሉ መዋዕለ ሕይወቶሙ ወተቀ ንዩ ለግብርናት ወደ አማርኛው ስተረጉመው እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ በማለት ይናገራል ዕብራውያን 2 ፥ 14 እና 15 ታድያ ይህ የሞት ፍርሃት በኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ የተወገደው ነው ይህ ኢየሱስ ለሰው ልጆች ኃጢአት ሊሞት ፣ ሰዎችንም ስለማጽደቅ ከሞት ሊነሣ ፣ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን ዲያብሎስንም በሞት እንዲሽር ስለሞት ፍርሃትም በባርነት የታሰርነውን እኛን ነጻ ሊያወጣ በሥጋና በደም እንዲሁ የተካፈለ ነው እንግዲህ በሥጋና በደም የመካፈሉ አንደኛውና ዋነኛው ጉዳይ በበረት መወለዱ ፣ በመጠቅለያም መጠቅለሉና በግርግም ተኝቶ መገኘቱ ነው መጽሐፉም ሲነግረን ወወለደት ወልደ ዘበኲራ ወአሰረቶ መንኮብያቲሁ ወአስከበቶ ውስተ ጎል ወጠብለለቶ በአፅርቅት እስመ አልቦሙ መካን ውስተ ማኅደሮሙ ወደ አማርኛው ስተረጉመው የበኵር ልጅዋንም ወለደች፥ በመጠቅለያም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው ማለትን የሚያመለክት ነው የሉቃስ ወንጌል 2 ፥ 7 ለዚህም ነው ካህናቱ በቅኔ ማህሌታቸው የሰንበት ተማሪዎችና መዘምራኑም በአውደ ምሕረታቸው በጐል ሰከበ በአፅርቅት ተጠብለለ ቤዛ ኲሉ ዓለም ዮም ተወልደ እያሉ በያሬዳዊ ጣዕመ ዜማ ማቀንቀናቸው ትርጉሙም በበረት ተኛ በጨርቅም ተጠቀለለ የዓለም መድኃኒት ዛሬ ተወለደ የሚለውን ትርጉም የሚሰጠን ነው ኢየሱስ በእንግዶች ማደርያ ሥፍራ አጥቶ በግርግም የተወለደውና በመጠቅለያም የተጠቀለለው በእርግጥም ሥፍራ አጥቶ አይደለም እርሱ ጌታና መድኃኒት ሆኖ በሥጋ ከማርያም የተወለደ ቢሆንም ከአብ ጋር በቅድምና የነበረ ፣ ሰማይ ዙፋኑ ምድር የእግሩ መረገጫ የሆነ ፣ በኪሩቤል ሠረገላ ላይ የተቀመጠ ፣ ዓለማትን የአብ ባሕርያዊ ቃል ሆኖ የፈጠረ፣ የክብሩም መንጸባረቅና የባሕርዩም ምሣሌ ሆኖ ሁሉን በሥልጣኑ ቃል የደገፈ ፣ ኃጢአታችንንም በራሱ ያነጻና የሚያነጻም ነው ዕብራውያን 1 ፥ 1 _ 3 መጻሕፍት የሚመሰክሩለት ይህንን እውነት ነው የእንግዶች ማደርያ አጥቶ በግርግም መጠቅለሉ ግን እኛ ከእግዚአብሔር ጋር በኃጢአት ምክንያት በመጣብን የልዩነት ዕዳ ማደርያ አጥተን ፣ ተጥለን የነበርነውን ከወደቅንበት ለማንሳትና ወደቀደመ ቦታችንም ለመመለስ ኢየሱስ ለእንግዶች የሚሆን ማደርያ አጥቶ በግርግም ተኛ ወገኖቼ ምሥጢሩ እንግዲህ ይህ ነው ኢየሱስ መጥቶ እስኪወለድልን ድረስ በሞት ፍርሀት ውስጥ በባርነት ተይዘንና ማደርያ አጥተን በእንዲህ ሁኔታ በዚሁ የሞት ፍርሃት ታስረን የተጣልን ነበርን ተወልዶ ያልቀረው ኢየሱስ ግን ጊዜው ደርሶ ስለእኛ ኃጢአት በመሞት በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን ዲያብሎስንም በሞት በመሻር በሞት ፍርሃት የታሠርነውን እኛን ነጻ አወጣን ስለዚህ ዛሬ ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ኢየሱስ በእኛ ውስጥ ስላለ በሞት ላይ ሥልጣን የነበረው ዲያብሎስ ሥልጣኑን አጥቶአል እንግዲህ ምስጢሩ ምንድነው ወገኖቼ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን ዲያብሎስን ሥልጣኑን ሲሽረው ለእኔና ለእናንተ ትንሣኤና ሕይወት ሆኖን ነው በመሆኑም ይህን ትንሣኤና ሕይወት የሆነውን ጌታ በእርግጠኝነት በሕይወተ ሥጋ ሳለን አሁኑኑ ወደ ውስጣችን ፈቅደን እንዲህ ስንል ማስገባት አለብን ጌታዬ ሆይ አንተ ለእኔ ትንሣኤዬና ሕይወቴ ነህ ብሞት እንኳ አንተን በማመኔ ምክንያት ሕያው እንደምሆን አምናለሁና አንተን አዳኜን ኢየሱስን ወደ ሕይወቴ ወደ ውስጠኛው ክፍል አስገባሃለሁ አንተኑ የሕይወቴ ጌታም አድርጌ እቀበልሃለሁ ብለን ፈቅደን ስንወስንና ኢየሱስን ወደ ውስጣችን ስናስገባ ኢየሱስ ለእኛ ትንሣኤና ሕይወት ይሆንልናል በዚያው ቅጽበትም የሞት ፍርሃት እስራት ከእኛ ይበጠሳል ሥልጣኑ የተሻረው ዲያብሎስም ከእግራችን ሥር ይወድቃል ይህ ይሆን ዘንድ ግን አሁኑኑ እያንዳንዳችን ለራሳችን ወስነን ይህንን ልናደርግ ይገባል ወገኖቼ ኢየሱስን ያመነ ሰው ዛሬ የማደርያም ሆነ የመኖርያ ሥፍራ የሚያጣ አይሆንም በግርግምም አይጣልም የኢየሱስ የሆነ ሰውና ኢየሱስንም የሕይወቱ ጌታና ንጉሥ ያደረገ ሰው ሁሉ ሀገሩ በሰማይ ነው የሚጠብቀውም ከላይ የሚመጣውን መድኃኒት ነው ፊልጵስዩስ 3 ፥ 20 እና 21 ይመልከቱ ለዚህ ነው እንግዲህ የእኛ ጌታ የናዝሬቱ ኢየሱስ ከተጣልንበት ከታችኛው ሥፍራ አንስቶ ሀገራችንን በሰማይ ያደረገው የእግዚአብሔር ልጅ የናዝሬቱ ኢየሱስ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ ሲል የተናገረንና ይህንን አስደናቂ የሆነን የተስፋም ቃል የሰጠን ዮሐንስ ወንጌል 14 ፥ 3 መላዕክቱ መንጐቻቸውን ሲጠብቁ በሜዳ ላደሩ እረኞች እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና ሲሉ የማብሠራቸው ሌላው ምስጢሩ ደግሞ መደኃኒት ሊሆን የተወለደው ኢየሱስ ብቸኛ የኃጢአት መድኃኒት ስለሆነ ነው ሞትንም ስናስብ ለሞትም እንዲሁ ብቸኛ የሞት መድኃኒት እርሱ ኢየሱስ ብቻ ነው ከእርሱ ውጪ ከኃጢአትም ሆነ ከሞት የሚያድን ሌላ መድኃኒት የለም ለዚህም ነው በዚያን ዘመን ሊወለድ ላለው ኢየሱስ ወትወልድ ወልደ ወትሰምዮ ስሞ ኢየሱስሃ እስመ ውእቱ ያድኅኖሙ ለሕዝቡ እምኃጢአቶሙ የተባለለት ወደ አማርኛው ስተረጉመው ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ ማለትን የሚያመለክት ነው የማቴዎስ ወንጌል 1 ፥ 21 ሞትንም በተመለከተ ብቸኛ የሞት መድኃኒት መሆኑን የምናይበት እውነት በግዕዙ ቃል አነ ውእቱ ትንሣኤ ወሕይወት ዘየአምን ብየ እመኒ ሞተ የሐዩ ወኲሉ ዘሕያው ወየአምን ብየ ኢይመውት ለዓለም ተአምኑኒ ዘንተ ወደ አማርኛው ስተረጉመው ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል ሕያው የሆነም የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘላለም አይሞትም፤ ይህን ታምኚያለሽን ? የሚል ቃል የተጻፈልን በመሆኑ ነው ዮሐንስ ወንጌል 11 ፥ 25 _ 27 ስለዚህ ኢየሱስ ብቸኛው የሞት መድኃኒት ስለሆነ በእርሱ ሕያዋን ሊሆኑ ለሚያምኑበት ሁሉ ብቸኛው ትንሣኤና ሕይወት እርሱ ነው የተወደዳችሁ ወገኖች የሰማነውን ይህንኑ ቃል ፣ ልናነብ የተዘጋጀነውንም ሁሉ ጌታ እግዚአብሔር በቃሉ ልባችንን ይጎብኘው ፣ ይለውጠው አባቶቼና ወንድሞቼ ወገኖቼ ምዕመናን በሙሉ አሁንም ይህ የልደት በዓል ለሁላችንም የበረከት ፣ የጤናና የሰላም ፣ የደስታ በዓል ይሁንልን በማለት የምሰናበታችሁ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ነኝ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን

Joshua Tehadso: የመልዕክት ርዕስ በተጻፈልን እንኑር

Joshua Tehadso: የመልዕክት ርዕስ በተጻፈልን እንኑር: የመልዕክት ርዕስ በተጻፈልን እንኑር በዚያን ጊዜ አልሁ፦ እነሆ፥ መጣሁ፤ ስለ እኔ በመጽሐፍ ራስ ተጽፎአል አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ፥ ሕግህም በልቤ ...

የመልዕክት ርዕስ በተጻፈልን እንኑር


የመልዕክት ርዕስ


በተጻፈልን እንኑር



በዚያን ጊዜ አልሁ፦ እነሆ፥ መጣሁ፤ ስለ እኔ በመጽሐፍ ራስ ተጽፎአል
አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ፥ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው

መዝሙር 40 7



እኔ በስውር በተሠራሁ ጊዜ፥ አካሌም በምድር ታች በተሠራ ጊዜ፥ አጥንቶቼ ከአንተ አልተሰወሩም
ያልተሠራ አካሌን ዓይኖችሕ አዩኝ፤ የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ
አቤቱ፥ አሳቦችህ በእኔ ዘንድ እንደ ምን እጅግ የተከበሩ ናቸው፦ ቍጥራቸውም እንደ ምን በዛ፦
ብቈጥራቸው ከአሸዋ ይልቅ ይበዛሉ፤ ተነሣሁም፥ እኔም ገና ከአንተ ጋር ነኝ


መዝሙር 139 15 _ 18


ዳዊት በተጻፈለት ሊኖር የተናገረው አንድ እውነታ ቢኖር እነሆ መጣሁ ስለ እኔ በመጽሐፍ ራስ ተጽፎአል የሚል ነው ለእኛም በተጻፈልን ልንኖር የሚያስፈልገን አንድ እውነታ ስለ እኛ በመጽሐፍ ራስ ተጽፎአልና ከማንምና ከምንም በፊት በተጻፈልን ቃል ወደ እርሱ መምጣት ነው ዳዊት አሁንም ወደ እርሱ ሊመጣ የሆነበት ጉዳይ  አቤቱ፥ አሳቦችህ በእኔ ዘንድ እንደ ምን እጅግ የተከበሩ ናቸው፦ ቍጥራቸውም እንደ ምን በዛ ብቈጥራቸው ከአሸዋ ይልቅ ይበዛሉ፤ ተነሣሁም፥ እኔም ገና ከአንተ ጋር ነኝ በማለት የእግዚአብሔር ሃሳብ ከማንም ይልቅ በእርሱ ዘንድ የተከበሩ ናቸውና ለእግዚአብሔር ሃሳብ ራሱን በመስጠቱ ነው   በመሆኑም ወደ እርሱ ለመምጣት ለእኛም  የእግዚአብሔር አሳቦቹ በእኛ ዘንድ እጅግ የተከበሩ ሊሆኑ ፣ ከዚህ የተነሳ ወደ እርሱ ለመምጣት የእኛንም መነሳት ከእርሱም ጋራ መሆንን በእጅጉ የሚጠይቁ መሆናቸውን ከወዲሁ  በውል ልናውቅና ልናስተውል ይገባል ከዚያ  በኋላ ነው እንግዲህ የሕጉ በልባችን መቀመጥና ፈቃዱንም ለማድረግ የመውደድ ነገር ውስጣችን የሚገባው ዳዊት በእነዚህ በተጻፉት እውነቶች ሁሉ እግዚአብሔር የረዳው ሰው ስለነበረ እነዚህ ነገሮች ሁሉ በሕይወቱ ሆነዋል  ወደ እግዚአብሔር መምጣት ቃሉን ዕለት ዕለት  ከእኛ ከአገልጋዮች ከሚሰሙና እኛም ሳናሰልስ ከምናሰማቸው ምዕመናን ብቻ የሚጠበቅ አይደለም ወደ እርሱ ወደ እግዚአብሔር መምጣት እና ሃሳቦቹም በእኛ ዘንድ የተከበሩ ሆነው ፈቃዱን ለማድረግ መውደድ መነሳት ከእርሱም ጋር መሆን ለሁላችንም   የተጻፈልን ስለሆነ ከሁላችንም የሚጠበቅ ጉዳይ ነው  ዳዊት ሌላውን ሳይሆን ራሱን በተጻፈለት መጽሐፍ ውስጥ አይቶ ስለ እኔ በመጽሐፍ ራስ ተጽፎአል አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ፥ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው አለ ስለዚህ ወገኖቼ በተጻፈልን መጽሐፍ ሌሎችን ሳይሆን በቅድሚያ ራሳችንን ማየት ይሁንልን ያን ጊዜ ነው እንግዲህ እኛም እንደ ዳዊት ወደ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ልንመጣ ጊዜ የሚሆንልን ወደ እግዚአብሔር ሳንመጣ ግን  ሕጉን እንዲሁ በተለምዶም ሊሆን ይችላል ብቻ ምንም የሚታወቅ ነገር የለም  እንናገረው እናስተምረው እንስበከው እንዘምረው እንጂ የሕጉ በልባችን መቀመጥም ሆነ ፈቃዱን የማድረግ ውዴታ  ግን በፍጹም አይኖረንም የለንምም  እንደገናም  እኛ  ራሳችንን በተጻፈልን መጽሐፍ ከምናይ ይልቅ ሌሎችን ብናይ ለሌሎችና ስለሌሎችም ብንናገር ወደ እግዚአብሔር ሕጉም በልባችሁ ይቀመጥ ፈቃዱንም ለማድረግ ውደዱ ብንልና ደግመን ደጋግመንም ብንወተውት ይቀናናል  ነገር ግን በዚህ ነገር እኛው እራሳችን ወደ እርሱ ወደ ጌታ ያልመጣን በመሆኑ ባዶ ከሆነው ውትወታችን ውጪ በምንናገራቸውና በምንወተውታቸው ሰዎች ውስጥ ጠብ የሚል ነገር የለም እንደገናም ይሄ ቃል እናንተን አይመለከትም ወይ ስንባል ደግሞ  ከጥቂቶች በቀር አብዛኞቻችን ከተጻፈው ቃል ማዶ ያለን በመሆናችን እኛማ ፓስተሮች አስተማሪዎች ሽማግሌዎችና የመሣሠሉትን ነን ስንል መልስ እንሰጣለን እኛን ወደ ጌታ ወደ እግዚአብሔር ያላመጣ ቃል ደግሞ ቀኑን ሙሉ ስንናገርበትና ስንጮኽ ብንውል ሌሎችን አያመጣም በመጀመርያ ሊያመጣ የሚገባው እኛኑ ራሳችንን ነው እኛ ባልተጻፈልን ከቃሉ ማዶ ሆነን እየኖርን እናንተስ እያለ እኛነታችንን የሚጠይቅና የሚፈትሽ ቃል ሲመጣ እኛማ ሐዋርያት  መጋቢዎች ነቢያት አስተማሪዎችና የመሣሠሉትን  ነን ብንል ወደ ማዶ ሳንሻገር እግዚአብሔርም እርሱ ወደሚፈልገው ክብርና የዕድገት ደረጃም ሳያደርሰን  ስማችንን ብቻ ይዘንና ተቆልለን በደጅ በአፍአ ከምንቀር ውጪ የምናተርፈው ነገር የለም ዳዊት ወደ አንተ መጣሁ ሲል ወደ ጌታ ሊመጣ ስሙና ንግሥናው ዘውዱና ዙፋኑ አልያዘውም ከዘውዱ ከክብሩና ከንግሥናው ይልቅ የጌታ ሃሳቦች በእርሱ ዘንድ እጅግ የተከበሩ ነበሩ ስለዚህ ወደ ጌታ ሊመጣ ሕጉም በልቡ ሊቀመጥና ፈቃዱንም ለማድረግ ሊወድ የተከለከለበትና የታገተበት አንዳች ነገር አልነበረም ለእኛም በሥልጣን ላይ ላለንና ትልልቅ የማዕረግ ስሞች አሉን ስንል  ስለማንነታችን ብዙ በማውራት እኔማ እንዲህና እንዲያ ነኝ ለምንል ለእኛ  በቅድሚያ ለዳዊት የሆነው  ሁሉ ለእኛም ይሁንልን  ታድያ እኛ ከቃሉ ማዶ ሆነን ወደ እኛም መጥቶ እኛነታችንን ለፈተሸውና ለኮረኮረው ቃል ምላሻችን እኛማ እንዲህና እንዲያ ነን ከሆነ ብዙዎችን ሳይቀር ከተጻፈላቸው የእግዚአብሔር ቃል ሃሳብ ጋር እንዳይገናኙ ሕጉም በልባቸው ተቀምጦ የጌታን ፈቃድ የመፈጸም ውዴታ እንዳይኖራቸው በብዙ እየከለከልን ነውና በጌታ ዘንድ እንጠየቃለን ሽማግሌው ነቢይ እኔም እንዳንተ ነቢይ ነኝ በማለት የእግዚአብሔርን ፈቃድ የማድረግ ውዴታውን ሊፈጽም በእግዚአብሔር ቃል ከይሁዳ ወደ ቤቴል ተልኮ ለመጣ የእግዚአብሔር ሰው እንቅፋት ሆነ አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔር ሃሳቦች በእኛ ዘንድ እጅግ የተከበሩ መሆናቸው ሲቀር በምትኩም ስማችንን በቤተክርስቲያንም የተሰጠንን የሃላፊነት ቦታ ብቻ ማክበርና ማስከበር  ስንጀምር እንደገናም አሁንም  ተዋረድን ፈልገን እንዲሁ ለእኛነታችንና ለስማችን ብቻ ጥብቅና ስንቆም ይሄ ሁሉ ይሆናል 1ኛ ነገሥት 13 ምዕራፍን በሙሉ ይመልከቱ እግዚአብሔር ከዚህ ይጠብቀን ይልቁንም እኛም የእግዚአብሔርን ፈቃድ የመፈጸሙ ውዴታ ኖሮንና ፈጽመን ሌሎችም እንዲፈጽሙ ማነሣሣት ነው ያለብን ጌታችን ኢየሱስ ያደረገው ነገር ይህንን ነበር ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ ዮሐንስ ግን፦ እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን ? ብሎ ይከለክለው ነበር ኢየሱስም መልሶ፦ አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው ያን ጊዜ ፈቀደለት ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ የማቴዎስ ወንጌል 3 13 _ 13  ከዚህም ሌላ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 13 1 _ 20 የተጻፈውን ቃል ስንመለከት የደቀመዛሙርቱን እግር ሊያጥብ የማበሻ ጨርቅ ይዞ ለተነሳው ኢየሱስ ደቀመዝሙሩ ጴጥሮስ ባነሳው ጥያቄ ትሁት ጌታ የናዝሬቱ ኢየሱስ የሰጠውን መልስ እንመልከት እውነት ብለሃል ጴጥሮስ ጎሽ በእርግጥም  እኔ እኮ መምሕር እና ጌታ ነኝ እና ተገቢ የሆነን ተግባር እየፈጸምኩ አይደለሁም ሲል እግሮችን ከማጠብ ተግባሩ አልተመለሰም ይልቁንም ለየዋሁ ጴጥሮስ ተገቢውን መልስ ሰጥቶ ከጨረሰ በኋላ በቀጥታ የደቀመዛሙርቱን እግር ወደ ማጠብ ተግባሩ ተመልሶ እግሮቻቸውን አጥቦ እንደ ጨረሰ  ያደረግሁላችሁን ታስታውሳላችሁን በማለት እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብኩ እናንተ ደግሞ እርስ በእርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል ነው ያላቸው ስለዚህ ዛሬ የሚያስፈልጉን ሰዎች እንደ ጌታችን ኢየሱስ ከራሳቸው ይልቅ በትሕትናና ሌላውን በማገልገል ምሳሌ የሚሆኑን ሰዎች ናቸው ከዚህ በተጨማሪም የሕዝቡን ብቻ ሳይሆን የእነርሱንም ማንነትና ሕይወት የሚሰራ ቃል ሲመጣ ቶሎ ብለው ከሥልጣናቸው ጋር በመሆን እኔማ እንዲህና እንዲያ ነኝ የሚሉን ወይንም እንደዚያ እንደ ሽማግሌው ነቢይ የመጣውን የእግዚአብሔርን ቃል  ላለመቀበል ስማቸውን ተገን አድርገውና በስማቸው ለመከላከል ፈልገው እኔም እኮ እንዳንተ ነቢይ ነኝ የሚሉን ሳይሆኑ አሁንም እንደ ኢየሱስ  ቅሌን ማቄን ሳይሉና ምክንያተ ብዙ ሳይሆኑ ራሳቸውን ዝቅ አድርገውና ጽድቅን የመፈጸም ተነሳሽነት አግኝተው ጽድቅን በመፈጸም ሌሎችም ጽድቅን እንዲፈጽሙ መንገድ የሚሆኑ ሰዎች ነው የሚያስፈልጉን ጌታ እግዚአብሔር በዚህ እውነት ሁላችንንም ይጎብኘን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
                              

                               


ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ


የ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለራዕይ