Thursday, August 6, 2015

የጌታ እራት ለእኛ ምንድነው ? ለዛሬ ያለው ትርጉም Meaning for today ክፍል ዘጠኝ

የጌታ እራት ለእኛ ምንድነው ?



ለዛሬ ያለው ትርጉም




Meaning for today  




ክፍል ዘጠኝ








ዛሬን ስንጠይቅ ለክርስቲያኑ የጌታ እራት ትርጉሙ እንዴት ነው ? ሦስት የተያያዙ ሃሳቦች ለሃላፊ ጊዜ ለአሁን ጊዜና ለወደፊት ጊዜ ሊጠቅሙ የሚችሉ ሲሆኑ እነርሱም ተያይዘው ያሉና  የተገናኙም ናቸው


1ኛየጌታ እራት የጌታን መታሰቢያ ጊዜ    የምናስታውስበት ነው ጌታም እንዲህ ሲል ትዕዛዝ ሰጥቷል<< Do this in remembrance of me  >> የሉቃስ ወንጌል 22 19 1 ቆሮንቶስ 11 24   _  25 ይህ ለመኖርያችን ዋጋ ለመክፈል በአዕምሮ ወይም በሥጋ የምንጨነቅበት ሳይሆን ግሩምና ድንቅ የሆነውን የጌታን የማዳን ሕይወትና አገልግሎት ለማስታወስ ነው ይህ የጌታ እራት ጥልቅ የሆነውን ምሥጋናና አድናቆት ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ስላደረገልን ለመግለጽ ትልቅ በዓል ወይንም በእንግሊዘኛው Occasion ነው

     በአይሁድ የፋሲካ እራት ጊዜ የዕብራውያን ከግብጽ ባርነት ነጻ መውጣት የታወጀ አንድ ደረጃም ወደፊት የሄደ ነበረ በዘጸአት 12 26 እና 27 ላይ እንዲህ የሚል ቃል ተጽፎ እናገኛለን እንዲህም ይሆናል፤ ልጆቻችሁ፦ ይህ አምልኮ ለእናንተ ምንድር ነው ?  ባሉአችሁ ጊዜ፥ እናንተ፦ በግብፅ አገር በእስራኤል ልጆች ቤቶች ላይ አልፎ ግብፃዊያንን በመታ ጊዜ፥ ቤቶቻችንን ያዳነ የእግዚአብሔር የማለፉ መሥዋዕት ይህች ናት ትሉአቸዋላችሁይለናል  በመሆኑም በዚህ በሐዲስ ኪዳኑ የጌታ እራት ደግሞ ክርስቲያኑ ከኃጢአት ነጻ መውጣቱን ፣ ከሞት ሥቃይ መከራ በአካልና በአዕምሮም  ሳይቀር ፋሲካችን በሆነው ክርስቶስ እንደገናም ነጻ መውጣቱንና መላቀቁንም ጭምር ያውጃል( 1 ቆሮንቶስ 5 7 1 ቆሮንቶስ 11 26 )


2ኛሁለተኛው የጌታ እራት ጊዜ ፦ብርታት የማግኘት ጉልበት የማግኘት የመታደስ ጊዜ የመተሳሰርና የቁርባን ጊዜ  ነው እንደ ተሳትፎአችን መጠን የኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ ትርፉ ሕይወትን መስጠት ነው( ሮሜ 5 10 1 ቆሮንቶስ 10 16 ) ስለዚህ በክርስቶስ ትንሣኤ ባለ መንፈስ ውስጥ ሥልጣንን አግኝተን እንመገባለን እናድጋለን ዮሐንስ ዊስሊ ይህንን ጥንካሬ ያውቃል በአማካኝ በየአራት ወይም አምስት ቀን በረጅም ጊዜና ፍሬያማ ሥራው ወይንም የሕይወት ታሪኩ ቁርባኑን የወስዳል ያለ ጌታ እራት እግዚአብሔር ሥልጣንን አይሰጠንም ነገር ግን ለእኛ የጌታ እራት ተቋም አዘጋጅቷል እንደገናም ለግንኙነት መንገድና ዘዴ ጸሎትንና የእግዚአብሔር ቃል መስማትን ሰይሟል የዮሐንስ ዊስሊ መመርያ ሁልጊዜ ጠንከር ያለ ፣ ማሰብንና ማመዛዘንን የተገባን እንድንሆን አስችሎናል


3ኛ) ሦስተኛውና የመጨረሻው የጌታ እራት ጊዜ ቃልኪዳንን የማደስ እና ተስፋ የማድረግ ጊዜ ነው ነገር ግን ራሳችንን ቃል በቃል ማረጋገጥና የጥራት ሙከራ ወይንም ፈተና ማድረግ አለብን የጌታን እራት ተካፍለን የምንበላበት አኳኋን ዋጋ ያለው ነው( 1 ቆሮንቶስ 11 28 እና 29 ) እንደገናም የእርሱ ሕዝቦች ሙሉ በሆነ የመታደስ ተስፋ ለክርስቶስ የተሰጠንበትን እናድሳለን እርሱ እስኪመጣ ድረስ ( 1 ቆሮንቶስ 11 26 ) ክርስቶስ ከተመለሰ በኋላ በእርሱ መንግሥት ውስጥ በእርሱ አካላዊ መገኘት ከእርሱ ጋር ተካፍለን እንበላለን ( የማቴዎስ ወንጌል 26 29 ) የተወደዳችሁ ወገኖች የጌታን እራት ትምህርታችንን በዚህ የክፍል ዘጠኝ ትምህርት በማጠቃለል እንደመድማለን ጥያቄ ወይንም አስተያየት ካላችሁ በዚሁ በፌስቡክ አድራሻችን በብሎጎቻችንና በጎግል አድራሻችን ልትልኩልን ትችላላችሁ ወገኖቼ ትምህርቱ ከክፍል አንድ እስከ ክፍል ዘጠኝ ድረስ በየተራ የተለቀቀ ስለሆነ ሕይወታችንን የሚመሠርት ነውና በመደጋገም እንድትከታተሉት እንድታጠኑትም ማሳሰብ እወዳለሁ ለሌሎችም ወገኖቻችን ይጠቀሙ ዘንድ ሼር አድርጉት በተረፈ በሚቀጥሉት ሌሎች አዳዲስ ትምህርቶችና የትምህርት አርዕስቶች እስክንገናኝ ሰላም ሁኑ በማለት የምሰናበታችሁ



Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ

ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ ነኝ

God bless all People of God amen and amen.

Tuesday, August 4, 2015

Joshua Tehadso: የጌታ እራት ለእኛ ምንድነው ? መጽሐፍቅዱሳዊ ትምህርቶች Bi...

Joshua Tehadso: የጌታ እራት ለእኛ ምንድነው ? መጽሐፍቅዱሳዊ ትምህርቶች Bi...: የጌታ እራት ለእኛ ምንድነው ?       መጽሐፍቅዱሳዊ ትምህርቶች Biblical  teachings ክፍል ስምንት በ1ኛ ቆሮንቶስ 10 ፥ 16 መሠረት ሐዋርያው...

የጌታ እራት ለእኛ ምንድነው ? መጽሐፍቅዱሳዊ ትምህርቶች Biblical teachings ክፍል ስምንት

የጌታ እራት ለእኛ ምንድነው ?
     

መጽሐፍቅዱሳዊ ትምህርቶች


Biblical  teachings




ክፍል ስምንት


በ1ኛ ቆሮንቶስ 10 16 መሠረት ሐዋርያው ጳውሎስ በጌታ እራት ላይ ጣዖት ማምለክን መሐል ስላስገቡ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖችን ይገስጻል ይህ አመንዝራነት ነውና የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን ? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን ? እያለ ያመሣክራል የግሪኩ ቃል ትርጉም ስለ ቅዱስ ቁርባን  ( Holy Communion  ) እንዲህ ይላል ኅብረት የማድረግ ልምምድና መካፈል እንደሆነ ይናገራል ከክፍሉ ማለትም Context (ከኮንቴክስቱ ) እንደምናየው ጳውሎስ ያለው ክርስቲያን ወይኑና ኅብስቱን  በሚካፈልበት ጊዜ በክርስቶስ ውስጥ ያለውን የሞቱንና የትንሣኤውን ሕይወት ጥቅም እየተካፈለ ነው የዚህ ነገር ዋናው ጥቅሙ ኃጢአታችን ይቅር ለመባሉ ክርስቶስ ደም ውስጥ ሙሉ የሆነ ዋስትናና መጽናናት ስለተሰጠን ነው የክርስቶስ ኃይልና መገኘት ዋስትና የጋራ እና የሁሉ እንደገናም ለሁሉም የሆነችዋ  ቤተክርስቲያን በመያያዝ ከክርስቶስ አካል ጋር አንድ አካል የምንሆንበት ነው( 1 ቆሮንቶስ 10 16 _ 24 ) አንዱ እንጀራ የሚተካው የኢየሱስን የሕይወት እንጀራ ነው ( ዮሐንስ ወንጌል 6 35 ) ሁሉም አማኞች በጌታ እራት ጊዜ የሚበሉት ነው ምሳሌነቱ በክርስቶስ አካል ውስጥ ያለውን የክርስቲያኖች አንድነታቸውንና የጋራ ተሣትፎአቸውን ነው በሕይወት እንጀራ ላይ ትልቁ የኢየሱስ ንግጝር ከዚህ እንደሚከተለው በዚሁ በቃሉ ላይ ተዘግቧል ( ዮሐንስ ወንጌል 6 25 _ 68 )ከዚህም ሌላ ጳውሎስ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች በነበራቸው በምግብ ላይ የነበረ ኩራትና ስስ   ጌታ ቁርባን ላይ እንደሚጫወቱና እንደሚቀልዱ ክፍሉ ይናገራል 1 ቆሮንቶስ 11 17 _ 34  በመቀጠልም
የጌታን እራት ትምህርት ይገልጣል የበለጠ ዋጋ በመስጠትም ክርስቲያኑ በሚካፈልበት ጊዜ ለክርስቲያኑ ጥቅም እንዲሆን ጥሩ የሆነ ግምት ያለው ሁኔታን  ይሰጣል (1 ቆሮንቶስ 11 23 _ 25 ) ከዚህ የተነሣ በእግዚአብሔር የፍርድ ውጤት ጊዜ መልካም ያላደረጉ ደክመው ነበር ታመውና ብዙዎቹም እንኳ አንቀላፍተው ነበር በማለት ቃሉ ይነግረናል ( 1 ቆሮንቶስ 11 27 _ 34 )
የጌታን እራት ሥልጣን ለመጥፎ ነገር ላዋሉ ሰዎች ለምን ጳውሎስ ታድያ ጠንካራ ቃላትን መናገር ወደደ ?  ስንል  የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች በደንብ ወይም እንደሚገባ ለጌታ አካል እውቅና አልሰጡም ወይንም የጌታን አካል አልለዩም  ነበር ሃብታም የቆሮንቶስ ሰዎች ደሃ በሆኑ ክርስቲያን ወንድሞችና እህቶች ስስታም   ሆነው በሚበሉት የምግብ ልምምዶቻቸው አፍረዋል ተሸማቀዋል የክርስቶስ አካል የሆነችውን የእውነተኛዋን ቤተክርስቲያን ተፈጥሮ ካልለየን እንደገናም ማኅበራዊ ክፍሎችን እሽቅድምድሞችን የቀለም ልዩነቶችን ለይተን ካላወጣን ችግር ነው ( ገላትያ 3 28 ) በሌላ መልኩ ኅብስቱንና ወይኑን የሚወስድ ክርስቲያን ጸጋ በጎደለው ጠባይ ወይም አድራጎት በመለየት ውስጥ ቢወድቅ ክርስቲያን በቀጥታ ሊባረክ ሥልጣን አይሰጠውም በሚያስፈራ በዚህ አኳኋን የጌታን ኅብስትና ወይን የወሰደ ነውና ይህ ሊሆንለት አይችልም እንዲህ ዓይነት ሰው ጥፋተኛና በደለኛ ኃጢአተኛ የክርስቶስ አካልና የደሙ ተቃራኒ ነው ( ገላትያ 3 27 ) የክፍል ስምንት ትምህርታችንን እንግዲህ በዚሁ እንቋጫለን በክፍል ዘጠኝ ትምህርቶቻችን እስክንገኛ ሰላም ሁኑ በማለት የምሰናበታችሁ


Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ

ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ ነኝ

ተባረኩልኝ ለዘላለም