Tuesday, August 4, 2015

የጌታ እራት ለእኛ ምንድነው ? መጽሐፍቅዱሳዊ ትምህርቶች Biblical teachings ክፍል ስምንት

የጌታ እራት ለእኛ ምንድነው ?
     

መጽሐፍቅዱሳዊ ትምህርቶች


Biblical  teachings




ክፍል ስምንት


በ1ኛ ቆሮንቶስ 10 16 መሠረት ሐዋርያው ጳውሎስ በጌታ እራት ላይ ጣዖት ማምለክን መሐል ስላስገቡ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖችን ይገስጻል ይህ አመንዝራነት ነውና የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን ? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን ? እያለ ያመሣክራል የግሪኩ ቃል ትርጉም ስለ ቅዱስ ቁርባን  ( Holy Communion  ) እንዲህ ይላል ኅብረት የማድረግ ልምምድና መካፈል እንደሆነ ይናገራል ከክፍሉ ማለትም Context (ከኮንቴክስቱ ) እንደምናየው ጳውሎስ ያለው ክርስቲያን ወይኑና ኅብስቱን  በሚካፈልበት ጊዜ በክርስቶስ ውስጥ ያለውን የሞቱንና የትንሣኤውን ሕይወት ጥቅም እየተካፈለ ነው የዚህ ነገር ዋናው ጥቅሙ ኃጢአታችን ይቅር ለመባሉ ክርስቶስ ደም ውስጥ ሙሉ የሆነ ዋስትናና መጽናናት ስለተሰጠን ነው የክርስቶስ ኃይልና መገኘት ዋስትና የጋራ እና የሁሉ እንደገናም ለሁሉም የሆነችዋ  ቤተክርስቲያን በመያያዝ ከክርስቶስ አካል ጋር አንድ አካል የምንሆንበት ነው( 1 ቆሮንቶስ 10 16 _ 24 ) አንዱ እንጀራ የሚተካው የኢየሱስን የሕይወት እንጀራ ነው ( ዮሐንስ ወንጌል 6 35 ) ሁሉም አማኞች በጌታ እራት ጊዜ የሚበሉት ነው ምሳሌነቱ በክርስቶስ አካል ውስጥ ያለውን የክርስቲያኖች አንድነታቸውንና የጋራ ተሣትፎአቸውን ነው በሕይወት እንጀራ ላይ ትልቁ የኢየሱስ ንግጝር ከዚህ እንደሚከተለው በዚሁ በቃሉ ላይ ተዘግቧል ( ዮሐንስ ወንጌል 6 25 _ 68 )ከዚህም ሌላ ጳውሎስ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች በነበራቸው በምግብ ላይ የነበረ ኩራትና ስስ   ጌታ ቁርባን ላይ እንደሚጫወቱና እንደሚቀልዱ ክፍሉ ይናገራል 1 ቆሮንቶስ 11 17 _ 34  በመቀጠልም
የጌታን እራት ትምህርት ይገልጣል የበለጠ ዋጋ በመስጠትም ክርስቲያኑ በሚካፈልበት ጊዜ ለክርስቲያኑ ጥቅም እንዲሆን ጥሩ የሆነ ግምት ያለው ሁኔታን  ይሰጣል (1 ቆሮንቶስ 11 23 _ 25 ) ከዚህ የተነሣ በእግዚአብሔር የፍርድ ውጤት ጊዜ መልካም ያላደረጉ ደክመው ነበር ታመውና ብዙዎቹም እንኳ አንቀላፍተው ነበር በማለት ቃሉ ይነግረናል ( 1 ቆሮንቶስ 11 27 _ 34 )
የጌታን እራት ሥልጣን ለመጥፎ ነገር ላዋሉ ሰዎች ለምን ጳውሎስ ታድያ ጠንካራ ቃላትን መናገር ወደደ ?  ስንል  የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች በደንብ ወይም እንደሚገባ ለጌታ አካል እውቅና አልሰጡም ወይንም የጌታን አካል አልለዩም  ነበር ሃብታም የቆሮንቶስ ሰዎች ደሃ በሆኑ ክርስቲያን ወንድሞችና እህቶች ስስታም   ሆነው በሚበሉት የምግብ ልምምዶቻቸው አፍረዋል ተሸማቀዋል የክርስቶስ አካል የሆነችውን የእውነተኛዋን ቤተክርስቲያን ተፈጥሮ ካልለየን እንደገናም ማኅበራዊ ክፍሎችን እሽቅድምድሞችን የቀለም ልዩነቶችን ለይተን ካላወጣን ችግር ነው ( ገላትያ 3 28 ) በሌላ መልኩ ኅብስቱንና ወይኑን የሚወስድ ክርስቲያን ጸጋ በጎደለው ጠባይ ወይም አድራጎት በመለየት ውስጥ ቢወድቅ ክርስቲያን በቀጥታ ሊባረክ ሥልጣን አይሰጠውም በሚያስፈራ በዚህ አኳኋን የጌታን ኅብስትና ወይን የወሰደ ነውና ይህ ሊሆንለት አይችልም እንዲህ ዓይነት ሰው ጥፋተኛና በደለኛ ኃጢአተኛ የክርስቶስ አካልና የደሙ ተቃራኒ ነው ( ገላትያ 3 27 ) የክፍል ስምንት ትምህርታችንን እንግዲህ በዚሁ እንቋጫለን በክፍል ዘጠኝ ትምህርቶቻችን እስክንገኛ ሰላም ሁኑ በማለት የምሰናበታችሁ


Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ

ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ ነኝ

ተባረኩልኝ ለዘላለም


No comments:

Post a Comment