Friday, August 14, 2015
012 ነአምር ከመ መጽአ ዘይፌጽም ኦሪተ ወነቢያተ ኦሪትንና ነቢያትን የሚፈጽማቸው እንደመጣ እናውቃለንና ክፍል ሁለት የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ቅዱሳን ወገኖች በሙሉ የክፍል ሁለት ትምህርታችን የሚያጠነጥነው ኦሪትንና ነቢያትን የሚፈጽማቸው እንደመጣ እናውቃለንና ተብሎ በአመክንዮ ዘሐዋርያት ላይ ወደ አማርኛው ስንተረጉመው የሐዋርያት አመክንዮ በተሰኘው የእናት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የእምነት መግለጫ ላይ ሠፍሮ የሚገኘውን ሃሳብ መነሻ በማድረግ ነው በክፍል አንድ ትምህርታችን ላይ ይህንኑ የእምነት መግለጫ የክፍል አንድ ትምህርታችን በማድረግ እንግዲህ እንደ አይሁድ አንገዘር በሚል ሃሳብ ዙርያ የጥንቷ ኦርቶዶክሳዊትና ሐዋርያዊት ዓለማቀፋዊት ቤተክርስቲያን ይህንን ያለችበትን ወደ ሦስትና አራት የሚደርሱ ሃሳቦችን አንስተን ባቀረብነው የቪድዮ አገልግሎት ላይ በሰፊው ማብራራታችን ይታወሳል እናንተም አድማጮች በቪድዮ የተላለፈው መልዕክት እንደደረሳችሁና እንደተጠቀማችሁበትም ተስፋ እናደርጋለን የክፍል ሁለት ትምህርትም ከዚሁ የቀጠለ ነው አሁንም ታድያ ደፍረን የዛሬዋን ቤተክርስቲያን ባንልም የጥንቷ ሐዋርያዊትና ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ግን በእምነት መግለጫዋ ላይ አሁንም ኦሪትንና ነቢያትን የሚፈጽማቸው እንደመጣ እናውቃለንና ስትል ወደ ሐዲስ ኪዳን አገልግሎት የመጣችና በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የመጣውን ሙሉ የሆነ የጸጋ መዳን አምና የተቀበለች መሆንዋን የሚያስታውሰን ትምህርት ነው ከዚህም ሌላ ሙሉ የሆነውን የጸጋ መዳንን ላመጣልን ለኢየሱስ እውቅና በመስጠት ነአምር ከመ መጽአ ዘይፌጽም ኦሪተ ወነቢያተ ወደ አማርኛው ስንተረጉመው ኦሪትንና ነቢያትን የሚፈጽማቸው እንደመጣ እናውቃለንና የሚለውን ትርጉም የሚሰጠን ነውና ኦሪትንና ነቢያትን በመፈጸም አምነን ለምንጸድቀው ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ መሆኑን አረጋግጣ የሰበከችና ያስተማረች መሆኑን ከዚሁ ከእምነት መግለጫዋ ለማስተዋል እንችላለን በመሆኑም ኦሪትንና ነቢያትን የሚፈጽማቸው እንደመጣ እናውቃለንና ብላ በእምነት መግለጫዋ ላይ የዘገበችና ያስተማረች ቤተክርስቲያን ጌታችን ኢየሱስ ኦሪትንና ነቢያትን የፈጽማቸው መሆኑን አምና ለዚሁ ጌታ እውቅና የሰጠች በመሆንዋ በክርስቶስ የሆነውን የጸጋ መዳን አምና የተቀበለች እንጂ እንደገና እንደ አይሁድ በጸጋ መዳንን ካስገኘው እምነት ወደኋላ ተመልሳና አፈግፍጋ ካልተገረዛችሁ አትድኑም እንደገናም የዳኑትን አሕዛብ ሳይቀር ከእምነት እንዲያፈገፍጉ እና ወደኋላም እንዲሉ ለማድረግ ትገርዙአቸውና የሙሴን ሕግ እንዲጠብቁ ታዙአቸው ዘንድ ይገባል ስትል የተናገረች አለመሆንዋን ከክፍሉ እንረዳለን የክፍል ሁለት ትምህርታችን እንግዲህ በሰፊው ይህንን እውነት ያብራራል ከዚህ በተጨማሪም ክርስቶስ ወደዚህ ምድር መጥቶ ሕግን የፈጸመልን በመሆኑ አምነው ለጸደቁትም ሆነ ወደፊትም በማመን ለሚጸድቁት ይኸው ጌታ የሕግ ፍጻሜ የሆነ እና ዛሬ ላይም አምነን ለጸደቅነው ለእኛም ሳይቀር ይህንኑ ጌታ በማመናችን ምክንያት ታጥባችኋል ተቀድሳችኋል ጸድቃችኋል ያለን መሆኑን ትምህርቱ በተገቢው መንገድ ይጠቁማል ይህንኑ ላደረገ ለልዑል እግዚአብሔር ጽድቃችንንም ለፈጸመልን እና ላጸደቀን ለጌታ ለኢየሱስ ክርስቶስ ከዘላለም እስከዘላለም ድረስ ክብር ይሁንለት አሜን ወገኖቼ እነዚህ ትምህርቶች እንግዲህ ከጥሩ ማብራርያና የመጽሐፍቅዱስ ማስረጃ ጋር ለእናንተ ለአድማጮችተዘጋጅተው የቀረቡ በመሆናቸው የተለቀቁትን ቪዲዮዎች ተከታትላችሁ እንድታዩአቸው ለሌሎችም ሼር እንድታደርጉት ስንል በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን ጌታ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment