Sunday, August 9, 2015
003ኢንትገዘር እንከ ከመ አይሁድ ነአምር ከመ መጽአ ዘይፌጽም ኦሪተ ወነቢያተ እንግዲህ እንደ አይሁድ አንገዘር ኦሪትንና ነቢያትን የሚፈጽማቸው እንደመጣ እናውቃለን የሐዋርያት አመክንዮ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የእምነት መግለጫ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ክፍል አንድ የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ቅዱሳን ወገኖች እናት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችንን ወደ ጥንተ መሠረት ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነት ለመመለስ ዛሬ በእምነት መግለጫዋ ላይ የተጻፈውን የአመክንዮ ዘሐዋርያት ቃል ላይ የሠፈረውን ቃል ኢንትገዘር እንከ ከመ አይሁድ ነአምር ከመ መጽአ ዘይፌጽም ኦሪተ ወነቢያተ ትርጉም እንግዲህ እንደ አይሁድ አንገዘር ኦሪትንና ነቢያትን የሚፈጽማቸው እንደመጣ እናውቃለን የሚለውን ሃሳብ መነሻ በማድረግ በክፍል አንድ ትምህርታችን ላይ የጥንቷ ሐዋርያዊትና ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን እንግዲህ እንደ አይሁድ አንገዘር ያለችባቸውን ሦስት ያህል ቀጣይነትና ተከታታይነት ያላቸውን ሃሳቦች ከመጽሐፍቅዱሳዊ ማስረጃዎች ጋራ እንደሚከተለው በዚሁ በምንለቃቸው ቪዲዮዎቻችን ላይ አቅርበነዋል ከዚሁ ጋራ ያሬዳዊ የወረብና የሽብሸባ ዝማሬዎች አብረው ቀርበዋል ስለዚህ ወገኖቻችን በዚህ ቃልና የትምህርቱ አገልግሎት እንድትባረኩበት በዝማሬውም ውስጥ አብራችሁ ተሳታፊ በመሆን እንድትዘምሩ ፣ እንድትወርቡ ፣ እንድታሸበሽቡና ከበሮና ጽናጽልም ካለ በከበሮና በጽናጽላችሁ ይህን ዝማሬ እንድታጅቡ ማሳሰብ እንወዳለን ትምህርቱ ያልተቋጨ በመሆኑ በክፍል ሁለት ትምህርት ይቀጥላል የክፍል ሁለት ትምህርታችን ኦሪትና ነቢያትን የሚፈጽማቸው እንደመጣ እናውቃለን የሚል ነው ጌታ እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይባርካችሁ ለማለት እወዳለሁ እነሆ ትምህርቱንም በቪድዮ እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ነኝ God bless all People of God amen and amen.
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment