Tuesday, August 18, 2015

005 የትምህርት ርዕስ የመዳኛው መንገድ የተገለጠው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው ይእዜሰኬ አስተርአየት ጽድቀ እግዚአብሔር እንዘ ኢይትገበር ሕገገ ኦሪት ኦሪት ወነቢያት ኮንዎ ሰማዕተ ከመ በአሚን በኢየሱስ ክርስቶስ ይጸድቁ በኀበ እግዚአብሔር ኩሎሙ እለ የአምኑ ቦቱ ኀበ ሰብአ ሮሜ ምዕራፍ 3 ቊጥር 21 እና 22 አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሠከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል እርሱም ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው ወደ ሮሜ ሰዎች የተላከ ምዕራፍ 3 ቊጥር 21 እና 22 ክፍል ሦስት ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና የሕግን ሥራ በመስራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት እንደማይጸድቅ በቃሉ ስለተነገረ ሐዋርያው በሮሜ 3 ፥ 20 ላይ አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሠከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል እርሱም ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው አለን ስለዚህ እኛን ለማጽደቅ የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ባይገለጥልን ኖሮ ሥጋ የለበስን የሰው ልጆች ሁሉ ምን ይውጠን ነበር በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘውን የእግዚአብሔር ጽድቅ በማመን እንድንድን ይህንን የጽድቅን ጥያቄ የመለሰልን ልዑል እግዚአብሔር ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁንለት ታድያ በሕግና በነቢያት የተመሠከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለሕግ መገለጡ ፦ 1ኛ) ሰው የራሱ የሆነ ጽድቅ ስለሌለው ነው ሮሜ 3 ፥ 23 _ 25 ፤ ሮሜ 3 ፥ 11 _ 18 ፤ ትንቢተ ኢሳይያስ 64 ፥ 6 2ኛ ) ይሄ የተገለጠው የእግዚአብሔር ጽድቅ በሕግና በነቢያት የተመሠከረለት ነው ዘፍጥረት 15 ፥ 6 ፤ ትንቢተ ዕንባቆም 2 ፥ 4 ፤ ሮሜ 1 ፥ 17 ፤ ዕብራውያን 10 ፥ 38 _ 39 ፤ የሐዋርያት ሥራ 10 ፥ 43 ፤ ዮሐንስ ወንጌል 3 ፥ 15 እነዚህን ጥቅሶች ከመጽሐፍቅዱሳችሁ በማውጣት አንብቡአቸው 3ኛ ) ኤርምያስ በትንቢቱም እነሆ፥ ለዳዊት ጻድቅ ቍጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እርሱም እንደ ንጉሥ ይነግሣል፥ ይከናወንለታልም፥ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል በዘመኑም ይሁዳ ይድናል እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፥ የሚጠራበትም ስም፦ እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ ነው አለን ትንቢተ ኤርምያስ 23 ፥ 5 _ 6 ስለዚህ ለዳዊት ጻድቅ ቍጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል ሲል በትንቢታዊ መልዕክቱ ጻድቅ ቍጥቋጥ ያለው ኢየሱስን ነውና ተዘልለን የተቀመጥንበትና የዳንበት ጽድቃችን እግዚአብሔር ነው ኢየሱስን በማመን የሚገኘውን ጽድቅ እግዚአብሔር ሰጠን 4ኛ ) የእግዚአብሔር ጽድቅ የምንሆነው በእርሱ በኢየሱስ ስንሆን ነው 2ኛ ቆሮንቶስ 5 ፥ 21 5ኛ ) ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው ተብለናል 1ኛ ቆሮንቶስ 1 ፥ 30 የተወደዳችሁ ወገኖች ትምህርቱ ከክፍል አንድና ከክፍል ሁለት ጋር ተያያዥነት ያለው በመሆኑ ሁሉንም የተለቀቁትን የቪዲዮ ትምህርቶች ተከታትላችሁ እንድትሰሙአቸው በጌታ ፍቀር ሆነን ከታላቅ ትሕትናና አክብሮት ጋር ማሳሰብ እንወዳለን እግዚአብሔር በዚህ ትምህርት ሁላችንንም ይባርከን የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment