Friday, September 4, 2015

የትምህርት ርዕስ የሕይወት መለወጥ Life transformation ክፍል አንድ

የትምህርት ርዕስ


የሕይወት መለወጥ



Life transformation


ክፍል አንድ


የተወደዳችሁ ወገኖች ዛሬ ወደ እናንተ የቀረብኩት አዲስ እና ተከታታይ የሆነ ትምህርት ይዤ ነው በተለያዩ ንዑሳን አርዕስቶች የሚቀርቡ ተከታታይ የሆኑ ሃሳቦች ያሏቸው ትምህርቶች ናቸው ከዛሬው የትምህርት ክፍለ ጊዜ በመጀመር እንግዲህ እንደሚገባ በማስተዋል እንድትከታተሉአቸውና እንድትጠቀሙባቸው በጌታ ፍቅር ለማሳሰብ እወዳለሁ ወደ  ዛሬው የትምህርት ክፍል ስመለስ በሐዋርያት ሥራ 15 3 ላይ  ቤተክርስቲያኑም በመንገድ እየረዳቸው እነርሱ የአሕዛብን መመለስ እየተረኩ በፊንቄና በሰማርያ አለፉ ወንድሞችንም ሁሉ እጅግ ደስ አሰኙአቸው ይለናል እንደገናም በደረሱም ጊዜ ቤተክርስቲያኑን ሰብስበው እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ያደረገውን ሁሉ ለአሕዛብም የሃይማኖትን ደጅ እንደከፈተላቸው ተናገሩ በማለትም የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል የሐዋርያት ሥራ 14 27 የሕይወት ለውጥ የአንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን የሁል ጊዜ ነው ለዚህም ነው መጽሐፍቅዱሳችን እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስታወት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን የሚለን 2 ቆሮንቶስ 3 18 በመሆኑም የአሕዛብን የጅማሬ ለውጥ ስንመለከት አሕዛብ መለወጥን ያደረጉት ቃሉን ሰምቶ በማመንና በመመለስ ነው ቃሉን ሰምተን ስናምን የእግዚአብሔር ቃል ይመልሰናል በሕይወታችንም ላይ ለውጥ እንድናደርግ ያስችለናል ለዚህም ነው በዚሁ በሐዋርያት ሥራ 14 27 ላይ  በደረሱም ጊዜ ቤተክርስቲያኑን ሰብስበው እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ያደረገውን ሁሉ ለአሕዛብም የሃይማኖትን ደጅ እንደከፈተላቸው ተናገሩ በማለት የተናገረን እንግዲህ የሃይማኖትን ደጅ እንደከፈተላቸው ተናገሩ ሲለን በቃሉ ሊናገረን የወደደው የእምነትን በር እንደከፈተላቸው ተናገሩ በማለት ነው የእምነት በር ማለትም የማመን በር የሚከፈተው ቃሉን ብቻ አምነው ሊድኑና መንገዳቸውንም በቃሉ መሠረት ሊለውጡ ለወደዱ ሰዎች ነው በመሆኑም አሕዛብ ቃሉን አምነው መንገዳቸውንም በቃሉ ሊለውጡ ስለወደዱ ጌታ እግዚአብሔር የእምነትን በር ከፈተላቸው ከዚህ የተነሳ ማመንና መዳን መለወጥም ሆነላቸው ወገኖቼ በዚህ የተከፈተ የማመን በር ነው ወደ እግዚአብሔር መንግሥትም መግባት የሚቻለው ይሄ የማመን በር ደግሞ ከመዳን ባሻገር ለመለወጥ ለማደግና ክርስቶስንም ለመምሰል ጥርጊያ መንገድን የሚከፍት ነው ማመናችን ከጊዜ ወደ ጊዜ በእግዚአብሔር ቃል ከፍ እያለ ሲመጣ መለወጣችንና ማደጋችን ክርስቶስንም መምሰላችን በዚያው ልክ ክፍ እያለና እየጨመረ ይመጣል ታድያ ሰው ሲለወጥ ወይም ሲዛወር ተለወጠ ይባላል ለመለወጥ ግን በቅድሚያ አዕምሮን መክፈት የመጽሐፉንም ቃል ለመነጋገርና ለመስማት ፈቃደኛ መሆንን ይጠይቃል ያን ጊዜ የቃሉን እውነት መረዳት ይጀመራል እግዚአብሔር እንድንለወጥ መጽሐፉንም እንድንረዳ ይጋብዘናል የምንከተለው የመረጥነውን ነው የምናደርገው የሰማነውን ያየነውን ነው መለወጥ ሕይወትን መምረጥ ነው በዘዳግም 30 19 ላይ በፊታችሁ  ሕይወትንና ሞትን በረከትንና መርገምን እንዳስቀመጥኩ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ አስመሰክራለሁ እንግዲህ አንተና ዘርህ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ሕይወትን ምረጥ እያለ ይናገራል በሐዲስ ኪዳንም ጌታ ኢየሱስ ማርያምን ሕይወትን መርጣ ቃሉን ልትሰማ በዚሁ ጌታ እግር ሥር በመቀመጧ መልካም  ዕድልን መርጣለች ከእርሷም አይወሰድባትም ነው ያለው  ማርታን ግን ማርታ ማርታ በብዙ ነገር ትጨነቂያለሽ ትታወኪማለሽ የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው በማለት ተናገራት የሉቃስ ወንጌል 10 38 _ ፍጻሜ ትልቁ መልካም ዕድል ቃሉን ከመስማት የሚገኝ የሕይወት ምርጫ ነው እዚህ ምርጫ ውስጥ ገብተው ሕይወትን ያገኙ ደግሞም ይህን የምርጫቸውን ዕድል ተጠቅመው በዚህ የሕይወት ከፍታና ቃሉንም የመስማት አቅም ወደፊት ለሄዱ፣ ሊሄዱም ለወሰኑና በመሄድም ላይ ላሉ ሰዎች  ሕይወት ለእነርሱ የምርጫ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን እየበዛና እየተትረፈረፈ የሚሄድ  ከእነርሱም  የማይወሰድ ነው እንደገናም ጌታ እግዚአብሔር የሰው ልጆችን ትክክለኛውን ምርጫ እንዲመርጡ ያበረታታል እንጂ ማንንም ፎርስ አያደርግም  He clearly encourages human beings to" choose life " መለወጥም የአንድ ጊዜ ሂደት ብቻ ሳይሆን ፕሮሰስ ነው ጌታ እግዚአብሔር በምናነበው ቃል ወደ እያንዳንዳችን ይምጣና ሕይወታችንንም ይለውጥ ተባረኩልኝ ቅዱሳን

Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ

ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ ነኝ


No comments:

Post a Comment