Saturday, September 19, 2015

004 ክፍል አራት እስመ ኢየአምርዋ ለጽድቀ እግዚአብሔር ወፈቀዱ በጽድቀ ርዕሶሙ ይቁሙ ወለጽድቀ እግዚአብሔርሰ ስእኑ ገኒየ ኀበ ሰብአ ሮሜ ምዕራፍ ፲ ቁጥር ፫ የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሳያውቁ የራሳቸውንም ጽድቅ ሊያቆሙ ሲፈልጉ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕራፍ 10 ቁጥር 3 ጥንታዊት ሐዋርያዊትና ዓለም አቀፋዊት የሆነችዋን እናት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናችንን ወደ ጥንተ መሠረት ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነት ለመመለስ የሚያስችሉ እውነቶችን በእግዚአብሔር ቃል እውነት አማካኝነት ከራሷ ከቤተክርስቲያኒቱ የእምነት መግለጫ ያገኘን በመሆናችን ከዚህ በፊት እንዳቀረብነው አሁንም ከክፍል አንድ እስከ ክፍል ሦስት የሚደርሱ ተከታታይና ቀጣይነት ያላቸውን ትምህርቶች ማቅረባችን ይታወሳል የክፍል አራት ትምህርታችን ደግሞ አሁን የሚቀጥል ነው ትምህርቶቹ በቤተክርስቲያኒቱ የእምነት መግለጫ ማለትም በሐዋርያት አመክንዮ በተሰኘው የእምነት መግለጫ ላይ ተጽፈውና ሠፍረው ያሉ በመሆናቸው እንዲህ የሚል ሃሳብ ይዘዋል በግዕዙ ቃል እንዲህ ይላል ኢንትገዘር እንከ ከመ አይሁድ ነአምር ከመ መጽአ ዘይፌጽም ኦሪተ ወነቢያተ ወደ አማርኛው ስንተረጉመው እንዲህ ይላል እንግዲህ እንደ አይሁድ አንገዘር ኦሪትንና ነቢያትን የሚፈጽማቸው እንደመጣ እናውቃለን የሚል ነው በመሆኑም እነዚህን ሃሳቦች መነሻ በማድረግ በክፍል አንድ ትምህርታችን ላይ ቤተክርስቲያኒቱ እንደ አይሁድ አንገዘር ያለችባቸውን ከአንድ እስከ ሦስት የሚደርሱ ተከታታይና ቀጣይ ክፍሎችን አቅርበናል በክፍል ሁለት ትምህርታችን ላይ ደግሞ ኦሪትንና ነቢያትን የሚፈጽማቸው እንደመጣ እናውቃለን በሚል ንዑስ አርስት እንደዚሁ ሦስት ያህል ተከታታይ ሃሳቦችን ማቅረባችን ይታወሳል በክፍል ሦስት ትምህርታችንም ላይ የመዳኛው መንገድ የተገለጠው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው በሚል ንዑስ አርዕስት በተመሣሣይ መልኩ ወደ ሦስት የሚደርሱ ተከታታይ ክፍሎችን ለአድማጮች አድርሰናል ታድያ ትምህርቱ ተያያዥነት ያለው በመሆኑ በቀጥታ የክፍል አራት ትምህርትን በኦድዮና በፓወር ፖይንት በተደገፈ ሥዕላዊ መግለጫ ያቀረብነው በመሆኑ በማስተዋል ሆናችሁ እንድትከታተል በጌታ ፍቅር ማሳሰብ እንወዳለን የክፍል አራት ትምህርት እንደሚያመለክተን የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሳያውቁ የራሳቸውን ጽድቅ ሊያቆሙ ሲፈልጉ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም ማለቱ 1ኛ ) ሰው የራሱን ጽድቅ ሲያቆም በራሱ የሚታመንና ሌላውንም የሚንቅ በመሆኑ ነው የሉቃስ ወንጌል 18 ፥ 9 _ 14 2ኛ ) ሰው የራሱን ጽድቅ ሲያቆም አይቶ ከመናቁም የተነሣ ገለል ብሎ ያልፋል ምሕረት አያደርግም አይረዳም የሉቃስ ወንጌል 10 ፥ 29 _ 37 3ኛ) ሰው የራሱን ጽድቅ ሲያቆም የሚጥመው ነገር የለም የሉቃስ ወንጌል 7 ፥ 24 _ 35 4ኛ) ከሆነለት ደግሞ የያዘ ያጋለጠና ያዋረደም መስሎ ይህቺ ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች በማለት ጌታን ሳይቀር ስለእርሱዋ ምን ትላለህ ? ሲል መጠየቁ እውን ነው ዮሐንስ ወንጌል 8 ፥ 4 _ 11 5ኛ) እንዲህ ዓይነቶቹ ሰዎች ራሳቸውን በሰው ፊት የሚያጸድቁ ናቸውና እግዚአብሔር ግን ልባቸውን ያውቃል የሉቃስ ወንጌል 16 ፥ 14 እና 15 የተወደዳችሁ ወገኖች ትምህርቱ በኦድዮና በፓወር ፖይንት ታጋዥነት ተዘጋጅቶ የቀረበ በመሆኑ በአንዳንድ ቦታዎቹ ድምጹ በጉልህ አይሰማም ስለዚህ እኛም አዘጋጆች ለዚህ ችግር ትልቅ ይቅርታ እየጠየቅን አድማጮቻችን ትምህርቱን ይበልጥ እንድትረዱ በጽሑፍም ጭምር ያቀረብን መሆናችንን ከወዲሁ ልታውቁልን እንወዳለን ጌታ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ አሜን የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment