Thursday, October 29, 2015

ወቅታዊ ትኩስ ዜና ለእግዚአብሔር ሕዝቦች በሙሉ የተላለፈ መልዕክት አሁን ላይ ባለው ዘመናችን ከሊቃውንቱ መንደር ሳይታሰብ ብቅ ያሉልን የወንጌል አርበኛው መጋቤ ጥበባት መምህር አስራትና የመወድሱ ቅኔያቸው

ወቅታዊ ትኩስ ዜና


ለእግዚአብሔር ሕዝቦች በሙሉ የተላለፈ መልዕክት



አሁን ላይ ባለው  ዘመናችን  ከሊቃውንቱ መንደር ሳይታሰብ ብቅ ያሉልን የወንጌል አርበኛው መጋቤ
ጥበባት መምህር አስራትና የመወድሱ ቅኔያቸው



መወድስ

ማርያም ኢክህለት ለአድኅኖ ኵሉ ዓለም
ውሉደ አዳም ወሔዋን ዘተወልዱ እም አዳም
ፍትሐ ኵነኔ ወሞት ወፍትሐ ቀዳሚ መርገም
ደሞ ከመ ይክዓው
ወልደ አብ እም ኢተሠገወ በሥጋ ድኩም
ጳውሎስ ከመ ይቤ
አምጣነ አልቦ ስርየት ዘእንበለ ይትከዓው ደም
ወዝ ኵሉ ለእመ ኮነ ከመ ቃለ መጽሐፍ ኅቱም
እፎኑመ ይትከሃል ለአድኅኖ ኵሉ ዓለም
ወእፎ ይብልዋ ቤዛዊተ ኵሉ ዓለም
ዲበ ዕፀ መስቀል ዘቀራንዮ እስመ ኢተሰቅለት ማርያም፡፡

ትርጉም፦

ከአዳም እና ከሔዋን የተወለዱ የአዳም ልጆችን ሁሉ
ከሞትና ከኵነኔ ፍርድ እንዲሁም ከመጀመሪያው መርገም ፍርድ ማርያም ማዳን ብትችል ኖሮ
ደሙን ያፈስ ዘንድ ወልደ አብ በደካማ ሥጋ ሰው ባልሆነም ነበር
ጳውሎስ እንዳለው ደም ሳይፈስ ስርየት የለምና
ይህ ሁሉ እንደ መጽሐፍ ቃል የተዘጋ ቢሆን ኖሮ፣

ዓለምን ከገሃነም ማዳን እንዴት ይቻላል?

እንዴትስ ማርያምን የዓለም ሁሉ ቤዛ ይሏታል?
በቀራንዮ የዕንጨት መስቀል ላይ ማርያም አልተሰቀለችምና




የተወደዳችሁ ወገኖች ቅዱሳን የእግዚአብሔር ሕዝቦች በሙሉ ምሕረቱን ያገነነልን ጌታ እግዚአብሔር ለዚህ ለተባረከ ቀን ያደረሰን አምላክ ነውና ክብር ምስጋና ይግባው ከዚህ በመቀጠል የምናቀርብላችሁ ከላይ በመግቢያ አርዕስታችን ላይ ያቀረብናቸውን የመጋቤ ጥበባት መምህር አስራትን በቤተክርስቲያኒቱ ቅኔ ማህሌት ላይ ተራ ተሰጥቶአቸው ያሰሙትን ወንጌል ተኮር የመወድስ ቅኔያቸውንና ስለ ተቀኙት የመወድስ ቅኔ ከተቃራኒው ክፍል የደረሰባቸውን እንግልት ተቃውሞና መገፋት ለእናንተ ለአንባቢዎች በማቅረብ ይሆናል መምህር አሥራት የቅኔና የቅዱሳት መጻሕፍት ሊቅና በርካታ ደቀመዛሙርት ያፈሩ መምህር ሲሆኑ በእስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን በመምህርነት ሲያገለግሉ የነበሩ ለመሆናቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ በእኚህ ሊቅ አገልግሎት ያልተደሰተውና መናፍቅ ናቸው ሲል በፈረጃቸው ማኅበረ ቅዱሳን የንስሐ ልጃቸው ሆና በቀረበች አንዲት ሴት ተሰልለው በመቅረጸ ድምፅ እንዲቀረጹ ይደረጋል እኚህ ሊቅ ዓይነ ስውር መሆናቸውን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ከቀረጸቻቸው በኋላ ተልእኮውን በሰጣትና በደብሩ ውስጥ ባለው የማኅበረ ቅዱሳን ክንፍ አማካይነት ወደሊቃውንት ጉባኤ ቀርቦ ሊቁ ተከሰሱ ከሥራቸውና ከደመወዝ ታገዱ ታድያ ከንስሐ አባቷ ይልቅቤተክርስቲያኗለሆነው ለማኅበረ ቅዱሳን የታመነችው ያች ሴት መምህሩ የሚከሰሱበትን ነጥብ ለመፈለግ ጥረት ያደረገች ሲሆን፣ በኤርምያስ 17 ፥ 5እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በሰው የሚታመን ሥጋ ለባሹንም ክንዱ የሚያደርግ ልቡንም ከእግዚአብሔር የሚመለስ ሰው ርጉም ነው።በሚለው ክፍል ላይ መምህር አስራት በሰጧት ማብራሪያ ክርስቲያን መታመን ያለበት በእግዚአብሔር ብቻ እንጂ በፍጡራን አለመሆኑን አስረድተዋታል ይህ እውነት ነው መታመን ያለብን እርሱ ብቻ አምላክ በሆነው በአንድነትና በሦስትነት ሲመለክና ሲወደስ በሚኖረው በእግዘአብሔር ብቻ ነው በሌላ ማለትም በቅዱሳን መላእክትና ሰዎች ጭምር እንዳንታመን ግን ታዘናልኢትተአመኑ በመላእክት ወኢ በእጓለ እመሕያው እለ ኢይክሉ አድኅኖእንዲል (መዝ ( 146 ) ፥ 3) በእውነት የሚፈርድ ስለጠፋ ግን በፍጡር የሚታመኑ አሳጋጅና አጋጅ ሲሆኑ፣ የታገዱት ደግሞ የቀናውን ትምህርት ያስተማሩትና መታመን ያለብን በእግዚአብሔር ብቻ ነው ያሉት መምህር አስራት ሆኑ በመሆኑም ይህ ሁኔታ መምህር አስራት ላይ የኑሮ መፈናቀልና ከሥራ የመታገድ ቀውስን ያመጣባቸው ቢሆንም የእግዚአብሔር ወንጌል ግን በዛ ቦታ እንደሚገባ ተነግሮአልና ጌታ ከምንጊዜውም በላይ ሥራውን እየሰራ ያለበት ጊዜ በመሆኑ በተቃዋሚዎች አንደነግጥም በዚህ አጋጣሚም መጋቤ ጥበባት መምህር አስራትን እንደ ወንድም ላሳስባቸው የምፈልገው ነገር ቢኖር በአንድም ነገር እንኳ በተቃዋሚዎች አትደንግጡ ይህም ለእነርሱ የጥፋት ለእናንተ ግን የመዳን ምልክት ነው ይህም ከእግዚአብሔር ነው ይህም ስለክርስቶስ ተሰጥቶአችኋልና እያለ ይናገራል ፊልጵስዩስ 1 28 _ 30 እንደገናም በዮሐንስ ወንጌል 16 1 _ 4 ላይ እንዳትሰናከሉ ይህን ተናግሬአችኋለሁ ከምኲራባቸው ያወጡአችኋል ከዚህ በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል ይህንም የሚያደርጉባችሁ አብንና እኔን ስላላወቁ ነው ይላል ስለዚህ በሆነው ነገር ብናዝንም አባቴና ወንድሜ ስለክርስቶስ ነውና መከራ እየተቀበሉ ያሉት ጌታ በሁሉም ነገር ከእርስዎ ጋር ይሆናልና አይዝዎት ልብዎትም ይጽና ልልዎት እወዳለሁ አሁንም ወደ መምህር አስራት ታሪክ ስመለስ መጋቤ ጥበባት መምህር አስራት በዚህችው ሰላይ ሴት መቅረጸ ድምጽ በቴፕ ተቀርጸው እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል ሲባል የተከሰሱ ብቻ ሳይሆን በኦርቶዶክስ ቅኔ ማኅሌት በተስተጋባው የመወድስ ቅኔም ጭምር ተከሰው የቀረቡም ነበር ይህ ቅኔ በእርግጥም ፍጥረታትንና መላዕክትን ወይም ሰዎችን የሚያወድስ ሳይሆን ስለ ጌታ ኢየሱስ ብቸኛ አዳኝነት የሚናገር በመሆኑ ከተለምዶ ቅኔዎችና ከመሣሠሉት ሁሉ በብዙ የተለየ ቢሆንም ከቅኔዎች ሁሉ የተለየና ይበል የሚያሰኝ እግዚአብሔርም ከሰማይ ወርዶ የተስማማበትና ያጸደቀው ቅኔ ነው ብንል ነገሩ እውነት ነው ከሚያስብለን ውጪ ማጋነን አይሆንም ቅኔ ልንደረድርለት ምስጋናም በብዙ ልናቀርብለት የሚገባው ለሰው ልጆች መዳን መሥዋት ሆኖ ለተሰዋው ለታረደው በግ ለናዝሬቱ ኢየሱስ ነው ቅኔን ለፍጡራን ለመላዕክትና ቅዱሳን ናቸው ብለን ለምናስባቸው ሰዎች እንድንሰጥና እነርሱንም እንድናወድስ የእግዚአብሔር መጽሐፍ መጽሐፍቅዱስ አያስተምረንም ዘጸአት 20 1 _ 5 ዮሐንስ ወንጌል 1 3 ሮሜ 11 36 1 ቆሮንቶስ 8 4 - 6 እነዚህ ጥቅሶች ማን ሊመሰገን እንደሚገባውና ምስጋናም  ለማን እንደሆነ ይበልጥ ስለሚያብራሩልን እንደሚገባ እናንብባቸው ፣ እናጥናቸው ይህ ቅኔ ከአዳም እና ከሔዋን የተወለዱ የአዳም ልጆችን ሁሉ ከሞትና ከኵነኔ ፍርድ እንዲሁም ከመጀመሪያው መርገም ፍርድ ማርያም ማዳን ብትችል ኖሮ ደሙን ያፈስ ዘንድ የአብ ልጅ በደካማ ሥጋ ሰው ባልሆነም ነበር ነው የሚለው የአብ ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ የእኛን ደካማ ሥጋ የለበሰውና ሰው የሆነው ደራሲውና ሊቁ በመወድስ ቅኔያቸው ዘርፈው እንደተናገሩት እኛን የሰው ልጆች ለማዳን ነው በመሆኑም በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም ጥርጥር ሳይኖርበት ብቻውን ያደነና የሚያድንም ኢየሱስ ነውና ደራሲው በዚሁ የመወድሱ ቅኔያቸው የማርያም አዳኝነትም ሆነ አማላጅነት ቦታ የለውም ማለታቸው ነው  በመሆኑም መጽሐፍቅዱሳችንም የሚነግረን እውነት ይሄ ስለሆነ እኚህ ሊቅ ትውልድን ጠቀሙ ፣ ሰውን ከአዳኙ ከክርስቶስ ጋር አስተዋወቁ እንጂ ያጠፉት ነገር የለም ይህ ጉዳይም እኚህን አባት እስከ ደሞዝ እገዳና የሥራ መባረር  የሚያደርሳቸው አይደለም ወገኖቼ ኢየሱስ ያልተሰበከ ምን ሊሰበክ ነው ? ሐዋርያው ጳውሎስስ ወንሕነሰ ንሰብክ ክርስቶስሃ ዘተሰቅለ አላለንም ወይ ? ወደ አማርኛ ስንተረጉመው እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን ማለት ነው 1 ቆሮንቶስ 1 23 ይመልከቱ የዘመኑ መጻሕፍትን ያላጠኑ ሞኞችና አላዋቂዎች ግን ያለ ማርያም አማላጅነት ዓለም አይድንም እያሉ በሌለና ባልተጻፈ የፈጠራ ወሬ ተሞልተው ይህንኑ ጥቅሳቸውን በየታክሲዎች እና የከተማ አውቶቡሶች ላይ በመለጠፍ የእኒህ ምሁር ትምህርት መጽሐፍቅዱሳዊ እውነት በመሆኑ የማይጥማቸውና ሊያስኬዳቸውም የማይችል ነው  ስማቸውን በውሸት አጥፍቶ መክሰስ ከሥራ ማስባረር የየዕለት ግባራቸው ሆነ በጊዜው ያለችው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንም ነገሩን በመመርመር ይህንን እውነት ነው እንግዲህ ማስተዋል ያቃታት ከዓመጸኞችና ጊዜያዊ ጥቅምን ከሚፈልጉ ሰዎች ጋር ተባብራ እኚህን የመሰሉ በስንት ድካም ቤተክርስቲያን ያፈራቻቸውን ፣ በእውቀታቸውም ብዙዎችን የሚጠቅሙትን ሊቅ አውጥታ በደጅ ጣለች እናም በዚህ ጉዳይ ላይ እኛም ከልብ በጣም አዝነናል እግዚአብሔር ግን ስለስሙ ከተገፉና ከተባረሩ ከተናቁትም ጋር ነው  እኒህ አባት መጋቤ ጥበባት መምህር አስራት በዚሁ በመወድስ ቅኔያቸው ኢየሱስ ብቸኛ አዳኝ ለመሆኑ ማስረጃ ሲሰጡ ጳውሎስ እንዳለው በማለት ደም ሳይፈስ ሥርየት የለም አሉ ዕብራውያን 9 22 ይህንን ሥርየት አሁንም ታድያ ከኢየሱስ ውጪ ለሰው ልጆች ያመጣ ማንም የለም ይህ ሥርየት ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን ማርያምም ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው የታጨች የሰው ዘር ናትና ለማርያምም ሳይይቀር የመጣ ሥርየት ነው ጥንተ አብሶ ያልነካካው እና ያልተጠናወተው ከሰው ወገን የሆነ ማንም የለም ጥንተ አብሶ በአዳም የመጣ በደል ማለት ስለሆነ የሰው ዘር የሆነውን ሁሉ አግኝቶታል ማርያምንም ጭምር በሮሜ 5 12 _ 21 1 ቆሮንቶስ 15 42 _ 50 እነዚህን ጥቅሶች ልብ ይበሏቸው  ታድያ ኢየሱስ ግን ከዚህ የተለየ ቅዱስ አምላክና ፍጹም ሰው ስለሆነ  ደሙን አፍሶልን ይህንን ሁላችን የሚያስፈልገንን ሥርየት ሰጠን      ኢየሱስ ወዶን ስለኃጢአታችን ቤዛ ሊሆንልን ደሙን ባያፈስልን ኖሮ  ይህንን ሥርየት ከየትም አናገኘውም ነበር ታድያ ሰይጣን ይህንን የሆነልንን እውነት ስለሚያውቅ  ይህንን ሥርየት ሰዎች በትክክል ከኢየሱስ አምነው እንዳይቀበሉ ማርያምንና ሌሎችንም ቅዱሳን ጻድቃን ሰማዕታት  ናቸው እያሉ ሰዎች የሚጠሯቸውን ሁሉ  በመሐል እያስገባ እና በነዚህም በኩል  ሥርየት ይገኛል እያስባለ ሰዎችን ያወናብዳል ወደ ሥርየትም እንዳይቀርቡ አምነውም ለዚሁ ጌታ ብቻ ሕይወታቸውን እንዳይሰጡ ያደርጋል ነገር ግን ሥራው የተነቃበት በመሆኑ በጌታ በኢየሱስ ስም እየገሰጽነው ሰዎችን ለክርስቶስ እንማርካለን ሊቁ መጋቤ ጥበባት መምህር አስራት በመወድሱ ቅኔያቸው አሁንም በቀራንዮ የእንጨት መስቀል ላይ ማርያም  አልተሰቀለችምና እንዴትስ ማርያምን የዓለም ሁሉ ቤዛ ይሏታል ? በማለት ደሙን አፍስሶ ሥርየትንና ይቅርታን የሰጠን ኢየሱስ ብቻ መሆኑን በዚሁ አስደናቂ በሆነው ቅኔያቸው በኦርቶዶክስ የቅኔ ማኅሌት ለካህናቱና ለመምህራኑ ለሊቃውንቱ ሁሉ አብስረዋል ይህ ነው እንግዲህ ወንጌል ማለት ሐዋርያው ጴጥሮስም በበዓለ ሃምሳ ቀን የአይሁድ ሊቃነ ካህናት እና ከልዩ ልዩ ሀገራት ወደ ኢየሩሳሌም የመጣ  የአይሁድ ሕዝብ ሁሉ በተሰበሰበበት ቀን ነበር በተመሳሳይ መልኩ እንደ መጋቤ ጥበባት አስራት የኢየሱስን አዳኝነት በመስበክ የኢየሱስን ቅኔ ለኢየሱስ ብቻ የተቀኘው በዚህም አገልግሎቱ ሦስት ሺህ ነፍስ ለጌታ ማርኳል እኛም ገና ከዚሁ ቤት ይህን እንጠብቃለን ትላንት በጴጥሮስ ዘመን ብቻ ሳይሆን አሁንም ኢየሱስ ከሦስት ሺህ ሕዝብ በላይ ቁጥር ስፍር የሌለውን ነፍስ ሁሉያድናል ለዚህ ነው መጋቤ ጥበባት አስራት ማርያም ኢክህለት ለአድኅኖ ኩሉ ዓለም በማለት ዓለሙን ሁሉ ልታድን ማርያም አትችልም  ሲሉ  የኢየሱስን አዳኝነት ብቻ ሳይሆን ማርያምም ዓለምን ለማዳን ያለመቻልዋን የሚያትት ከመጽሐፍቅዱስ ማስረጃ ጋር ተቀናብሮ የቀረበ የመወድስ ቅኔያቸውን በግልጽና በአደባባይ ያዥጐደጐዱት ታድያ ቅኔው ለእኚህ አባት መከራን ያተረፈላቸው ቢሆንም ለብዙዎች ግን ይህ ቅኔ ቅኔ ሆኖ ባለመቅረት ፍቺን አስገኝቶአል በማስገኘትም ላይ ይገኛል ቅዱሳን ወገኖች እኚህ አባት ዛሬ ይህን የመሰለ ነጻ አውጪ ወንጌል በመወድስ ቅኔ መልክ አቅርበው ይበል ተብለውና ቦታ ተሰጥቷቸው፣ ተመቻችተው አይደለም ያሉት የእኚህን ሊቅ አቤቱታና ይግባኝ ማለት የሚሰማ አካል ጠፍቶ ዛሬ ላይ ባለ ሕይወታቸው  በፍትሕ እጦት እየተራቡና እየተጠሙ ነው ያሉት ስለዚህ ይህ መልዕክት የደረሳችሁና ያነበባችሁ ቅዱሳን ወገኖች የእግዚአብሔር ሕዝቦች በሙሉ ለእኚህ አባት የየበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድታደርጉላቸው አቅማችሁ በፈቀደ ሁሉ እንድትረዱአቸውና እንድትጸልዩላቸው ከጎናቸውም እንድትሆኑ ጥሪ ማድረግና ማሳሰብ እወዳለሁ እኚህ ሰው ዓይነ ስውር በመሆናቸው ተንቀሳቅሰው እንዲህና እንዲያ በማድረግ እራሳቸውን ይረዳሉ ብለን ልናስብ አንችልም ሞያቸውንና በሞያቸው በኩል የሚያገኙትንም ደሞዝ የተነጠቁ ሰው በመሆናቸው  ከሞያቸው ውጪ ምንም ነገር ለማድረግ ዝግጁ የሆኑ ዓይነት ሰው አይደሉም ብዬ አስባለሁ ስለዚህ የእናንተ የቅዱሳን እርዳታ በብዙ ያስፈልጋቸዋል ስለዚህ እኚህ ሰው ሀገር ቤት ነውና ያሉት ያሉበትን ቦታ አፈላልጋችሁ በማግኘት የምትችሉትን ሁሉ እንድታደርጉላቸው በጌታ ፍቅር አሁንም ለእናንተ ለወገኖቼ ማሳሰብ እወዳለሁ ወገኖቼ ትምህርቴንም ሆነ ያለኝን መልዕክት በዚህ እጠቀልላለሁ በትዕግስት ሆናችሁ ትምህርቱንም ሆነ መልዕክቱን ማሳሰቢያዎችንና ያለውን ነገር ሁሉ ልታነቡ ልትከታተሉና ልትተባበሩም ፈቃደኛ በመሆናችሁ ጌታ እግዚአብሔር ይባርካችሁ እያልኩ  ከዚህ በመቀጠል  የዘማሪት ዘርፌ ከበደን ምሕረት የሚገባት ካላችሁማ እኔ ነኝ ሰዎች ሩሃማ የሚለውን ዝማሪ እጋብዛችኋለሁ ጌታ እግዚአብሔር ሁላችሁንም ይባርክ ሰላም ሁኑልኝ


ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን


የ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry

አገልጋይና ባለራዕይ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment