Tuesday, October 27, 2015

Only those drown by God will understand እነዚህ ብቻ በእግዚአብሔር የፈቃድ መረዳት የተሳሉ ናቸው ክፍል ስድስት

Only those drown by God will understand



እነዚህ ብቻ በእግዚአብሔር የፈቃድ መረዳት የተሳሉ ናቸው



ክፍል ስድስት


ለእግዚአብሔር የመጠራትና የመመረጥ ሂደት ከእግዚአብሔር " በተአምር" መለየት የሚጀምር ነው መጽሐፉም  የላከኝ አብ ከሳበው በቀር ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለሁ ይለናል ዮሐንስ ወንጌል 6 44  ከዚህም ሌላ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 6 65 ላይም ከአብ የተሰጠው ካልሆነ ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም አለን ጌታ እግዚአብሔር አስደናቂ የሆነና ያልተለመደ የኃይል ምስክርነት አለው እርሱ ለእኛ ደርሶ እኛን ከሰይጣን እስራት ተጽዕኖ ፣ ከምንኖርበትም ከዓለም ክፋት ፈትቶናል ወደፊትም ገና ብዙዎችን ይፈታል እግዚአብሔር የሚጋብዘን ከእነዚህ ነገሮች ሊያወጣን ነው ልባችንንም የሚለውጠው ወደ ራሱ አቅጣጫ ነው እርሱ አጥብቆ የሚፈልገው ማረጋገጫ እና እውቅናም የሰጠን የሚሰጠንም መንገዱን እንድንማር ፈቃዳችንንም ለእርሱ እንድናስገዛ ነው ነገር ግን ዝንባሌያችን ለእግዚአብሔር ሕግ ሊገዛ አይፈቅድም ሕጉንም መቃወም ይጀምራል በሮሜ 8 7 ላይ እንዲህ የሚል ቃል ተጽፎአል ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና መገዛትም ተስኖታል ይለናል ለእግዚአብሔር ፈቃድ መሸነፍ መማረክ በእውነትም ተአምር ነው መጽሐፍቅዱሳችን አሁንም ስለበጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና ይለናል ፊልጵስዩስ 2 13 ስለ አራቱ የመሬት ዓይነቶች ትርጉማቸው ለእግዚአብሔር ቃል ዘር ሰዎች ያላቸው ኃላፊነት የእግዚአብሔር ቃል እውነት በእነዚህ ነገሮች ውስጥ መሰበኩ ነገር ግን እግዚአብሔር የጠራቸው ብቻ እውነትን መረዳታቸውና መያዛቸው ለዚህ መልዕክት ሰዎች ልዩ ልዩ ምላሽ መስጠታቸው በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 13 ላይ በግልጽ ተጽፎ እናገኘዋለን በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 13 ቊጥር 19 ላይ ደግሞ የመንግሥትን ቃል ሰምቶ በማያስተውል ክፉ ይመጣል በልቡ የተዘራውንም ይነጥቃል በመንገድ ዳር የተዘራው ይህ ነው ይለናል ታድያ እንደነዚህ ዓይነት ሕዝቦች የመልዕክቱን አስፈላጊነት አያስተውሉም  በመሆኑም ይህን መልዕክትና ትምህርት ያነበብን የደረሰንም ሰዎች ያነበብነው ቃል ተራ የሆኑና ሰዎችን ለማሳመንም ሆነ የራስ ለማድረግ ሲባል ተኰልኩለው የተጻፉ ልብ ወለድ የሰዎች የፈጠራ ድርሰቶች  ሳይሆኑ የእግዚአብሔር የመንግሥቱ ቃል ስለሆነ የመልዕክቱን አስፈላጊነት አስተውለን እኛም ለየራሳችን  አወንታዊ ምላሽ ልንሰጥበት ይገባል  ስል ወንድማዊ ምክሬን ላስተላልፍላችሁ እወዳለሁ ጌታ እግዚአብሔር በምናነበው ቃል ዓይኖቻችንን ይክፈትልን አሜን
የ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry  


አገልጋይና ባለራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment