Saturday, July 4, 2015

የጌታ እራት የትምህርት ይዘትና አደረጃጀት ክፍል አራት

የጌታ እራት የትምህርት ይዘትና አደረጃጀት


ክፍል አራት



የተወደዳችሁ ወገኖች ዛሬ በክፍል አራት ትምህርታችን ላይ የምንመለከተው ደግሞ የጌታን እራት የትምህርት ይዘትና አደረጃጀት ምን እንደሚመስል በማስመልከት ነው ከዚህም ሌላ ከመጽሐፍቅዱሳችን ጋር በማመሳከርና  በዝርዝር በማስረጃ በማቅረብ ለሕዝባችን ትክክለኛውን የእግዚአብሔር እውነት ለማስጨበጥ እንወዳለን  ወገኖች ሆይ እዚህ ላይ የጌታ እራት ብቻ ሳይሆን ሌሎችም የጌታን እራት ዓይነት የሚመስሉ ትምህርቶች ሁሉ ይዘትና አደረጃጀት አላቸው ትምህርቶች ሁሉ ይዘት ከሌላቸው ወፍ ዘራሾች ናቸውና አደረጃጀት የሚባለውን ነገር  አያስገኙልንም አደረጃጀት የትምህርት ይዘት ውጤት ነው አንድ በአግባብ የተደራጀን ማንኛውንም  ነገር ስታዩ ከጀርባው ጠንካራ የሆነ የትምህርት ይዘትና ግንባታ አለው በዛ ተመስርቶና ተገንብቶ ነው የሚዋቀረው ብሎም የሚደራጀው ስለዚህ ጌታችን ኢየሱስ ለሰው ልጆች ሁሉ መድኅን ሊሆን የመጣ ጌታ በመሆኑ ይህንን የጌታ እራት በተመለከተ  በእርሱ ዘመንና ከእርሱም ዘመን ባሻገር እስከ ትውልድ ፍጻሜ ድረስ  ላሉና ለሚኖሩ  ሁሉ መመርያ እንዲሆን  ጊዜያትንና ቦታዎችን ተጠቅሞ ለዚሁ ለጌታ እራት የትምህርት ይዘት በመስጠት እንደሚገባ ሲያደራጅና መዋቅርም ሲሰጠው እንመለከታለን  ወገኖች ማንኛውም ትምህርትና አደረጃጀት ሲመጣ እንግዲህ እንዲህ ነው የራሱ የሆነ ይዘትና የራሱም አደረጃጀት አለው ቅድም በመግቢያዬ ላይ በዚህ መልኩ እንደገለጽኩት ትምህርት ሁሉ ይዘት አለው እንደገናም  መዋቅር ወይም አደረጃጀት አለውና ታድያ በዚህ ሁኔታ ውስጥ አሁን ላይ ያለን  አገልጋዮችም ሆንን ክርስቲያን ወገኖች ይህንን ጌታ የተጠቀመበትን መመርያ ተከትለን ማንኛውንም የምናስተምራቸውንም  ሆነ የምንማራቸውን ትምህርቶች ይዘት ልንሰጣቸውና መዋቅር ወይም አደረጃጀት ልናበጅላቸው ይገባል ያኔ ነገራችን ሁሉ ከእኛ አልፎ ወደ ትውልድ  የሚሻገር ይሆናል ዛሬ ግን ከዚዚህ ይልቅ የተዝረከረከ ነገር ነው በቤተክርስቲያን የምናየው እንደገናም ወፍ ዘራሽና አጉራ ዘለል የሆኑ ትምህርቶች ተበራክተው ሕዝባችንን ራዕይ አልባና መረን አድርገውት የሚያንቀዋልሉት ሆነዋል መልክ ያለው መንፈሳዊ ትምህርትና አደረጃጀት ከመጥፋቱም  ሆነ ከመታጣቱ የተነሳ ለብዙ ስሕተቶች ተዳርገናል  እንደገናም ይኼው ሕዝባችን በእግዚአብሔር ቃል  የትምህርት ይዘት ተመስርቶ ካለመደራጀቱ የተነሳ በክርስቶስ ትምህርት ሥር የሰደደ አይደለምና  ያገኘ ሁሉ ይነዳዋል ለዚህ እንግዲህ ተጠያቂው ማን ሊሆን እንደሚችል  እኔ መናገር የሚያስፈልገኝ ባለመሆኑ  ተጠያቂው እኔ ነኝ የሚል ማንኛውም ሰው ሁሉ ራሱን አውቆ ይመርምር ይፈትንም እላለሁ ይሁን እንጂ አሁንም ጊዜው አላለፈምና ራሱን ያወቀና የመረመረ ማንኛውም ሰው  ሁሉ አንድ ብሎ እና መነሻን ይዞ  ቢጀምር  ነገሮችን ከጌታ ጋር በመሆን ማስተካከል ይችላል ጌታም ሥራው የራሱ እንደሆነ ስለሚያውቅ በዚህ ነገር ፈጥኖ ይረዳዋል ሥራውንም ያቃናለታል ጌታችን ኢየሱስ  በጌታ እራት የትምህርት ይዘትና አደረጃጀት ውስጥ የተጠቀመበትን መንገዶችና ያለውን ሁኔታ ሁሉ እነዚህ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶች በግልጥነት ያሳዩናልና እንደሚከተለው ደረጃ በደረጃ እንከታተላቸው እናንብባቸው ደግሞም እናጥናቸው የማርቆስ ወንጌል 14 12 _ 26 የሉቃስ ወንጌል 22 1 _ 23 1 ቆሮንቶስ 11 23 _ 25  ወገኖች እንግዲህ ከነዚህ ጥቅሶች እና የመጽሐፍቅዱስ ክፍሎች መሐል  የማርቆስ ወንጌል 14 12 _ 26 ላይ የተጻፈልንን ሃሳብ ለጥናታችን እንደ መነሻ አድርገን እንወስዳለን ፋሲካን በሚያርዱበት በቂጣ በዓል መጀመርያ ቀን ደቀ መዛሙርቱ ፋሲካን ትበላ ዘንድ ወዴት ሄደን ልናሰናዳ ትወዳለህ ? አሉት ይለናል ይህ በጣም ጥሩ የሆነ ጥያቄ ነው ፋሲካ ሲታሰብ እንግዲህ የሚዘጋጅበት ቦታ እና ጊዜውም ጭምር ከግምት ውስጥ ገብቶ አብሮ የሚታሰብ  በመሆኑ ፋሲካን ብቻ ሳይሆን የፋሲካውን ቦታ እና የጊዜውንም ሁኔታ አብሮ ማሰብ ማዘጋጀት  ትልቁ አደረጃጀት ነው ማርቆስ በወንጌሉ ፋሲካው የሚዘጋጅበትን የጊዜ ሁኔታ ሊጠቁመን በመሸም ጊዜ ከአሥራ ሁለቱ ጋር መጣ ይለናል የማርቆስ ወንጌል 14 17 ስለዚህ የፋሲካው ዝግጅት የተካሄደው ኢየሱስ ከመሞቱ በፊት ባለው ማታ ነው በጋራና በኅብረት የተዘጋጀው ምግብም የጌታ እራት በመባል ይታወቃል አያይዞም ስለ አዘገጃጀቱ ሁኔታ  ማርቆስ በወንጌሉ አሁንም እንዲህ ሲል ይተርክልናል  ከደቀ መዛሙርቱም ሁለት ላከ እንዲህም አላቸው፦ ወደ ከተማ ሂዱ፥ ማድጋ ውኃ የተሸከመ ሰውም ይገናኛችኋል ተከተሉት፥ የሚገባበትንም የቤቱን ጌታ መምህሩ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን የምበላበት የእንግዳ ቤት ወዴት ነው ? ይላል በሉት እርሱም በደርብ ላይ ያለውን የተሰናዳና የተነጠፈ ታላቅ አዳራሽ ያሳያችኋል በዚያም አሰናዱልን ደቀ መዛሙርቱም ወጡ ወደ ከተማም ሄደው እንዳላቸው አገኙ፥ ፋሲካንም አሰናዱ በመሸም ጊዜ ከአሥራ ሁለቱ ጋር መጣ ተቀምጠውም ሲበሉ ኢየሱስ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከእናንተ አንዱ፥ እርሱም ከእኔ ጋር የሚበላው አሳልፎ ይሰጠኛል አለ እንግዲህ ወገኖቼ ከምንባቡ እንደተመለከትነው በመሸም ጊዜ ኢየሱስ ከአሥራ ሁለቱ ጋር ለመምጣቱ  እንደገናም አሁንም ምንባቡ ተቀምጠውም ሲበሉ ይለናልና ተቀምጠውም ለመብላታቸው ምክንያት የሆኑት ከአሥራ ሁለቱ በፊት ይህንን ነገር በቅድሚያ እንዲያሰናዱ የተላኩ ሁለት ደቀመዛሙርት ናቸው እነዚህ ደቀመዛሙርትም ይህንን ሁሉ ሊያደርጉ ተልከው ወደ ከተማ የሄዱ መሆናቸውን ክፍሉ ይጠቁመናል ይሁንና ዛሬም ወዴትም ይሁን ወዴት ብቻ ለወንጌል ሥራ የሚላኩ ሰዎች የሚገኙትና የሚላኩት እንደዚህ በክፍሉ ላይ እንዳየነው እንደ አሁኑ  የተደራጀ ነገር እና አደረጃጀትም ጭምር ሲኖር ነው አለበለዚያ የወንጌሉ ተልዕኮ ግቡን አይመታም አንዱና ዋናው የወንጌል  ተልዕኮ ደግሞ ፋሲካችን የሆነውን ኢየሱስን ሰዎች ፋሲካቸው እንዲያደርጉትና የእንግዳ ቤት የሆነውን ሰገነታቸውንና አዳራሻቸውንም ጭምር አሳልፈው ሲሰጡት ነው የዛሬው የእንግዳ ቤት የሆነው ሰገነትና አዳራሽ ደግሞ ተቆልፈው ያሉና ለማንም ሊከፈቱ የማይችሉ በጌታ ትእዛዝና ፈቃድ ግን የሚከፈቱ የሰው ልቦች ናቸው ጌታ ትእዛዝ ካወጣና ከተናገረ ደግሞ የማይለቀቅ ደርብና የተነጠፈ አዳራሽ የለም ከኢየሱስም በላይ የከበረ እንግዳ  ስለሌለ የማይከፈት የእንግዳ  ቤት አይኖርም የእንግዳ ቤት ተብለውና በክብር የሠረገላ ቁልፍ ተከርችመው የተቆለፉ የሰዎች የልቡና በሮች ሁሉ በራሳቸው በሰዎቹ ፈቃድ ሳይሆን ሞትን ድል በነሣው በይሁዳው አንበሳ  በኢየሱስ ትእዛዝና ፈቃድ ሳይወዱ በግዳቸው የፋሲካው የመስተንግዶ ሥፍራ ብቻ ሳይሆኑ የዚሁ የፋሲካውም ጌታ  መኖርያ ጭምር ሊሆኑ ይከፈታሉ ፋሲካችን የሆነው ክርስቶስ በመስተንግዶው ሥፍራ እና ተነጥፈው ባሉ የልቡና አዳራሾቻችን የፋሲካን በዓል ሊያከብር በዓል አክባሪ ሆኖ የገባ ብቻ ሳይሆን እርሱ እራሱ ከሞት ወደ ሕይወት የተሻገርንበት ወደፊትም በእርሱ ያመኑ ሁሉ የሚሻገሩበት በመሆኑ  እውነተኛው በዓላቸውና  ፋሲካቸው ሆኖ  ፈቅደው ወደከፈቱለት የልባቸው ሰገነት ሁሉ የሚገባ ነው  መዝሙረኛው ዳዊትም ከዚህ የተነሳ ነው ይህች ትውልድ እርሱን የምትፈልግ ናት፥ የያዕቆብን አምላክ ፊት የምትፈልግ እናንት መኳንንቶች፥ በሮችን ክፈቱ፥ የዘላለም ደጆችም ይከፈቱ፥ የክብርም ንጉሥ ይግባ ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? እግዚአብሔር ነው፥ ብርቱና ኃያል፥ እግዚአብሔር ነው፥ በሰልፍ ኃያል እናንተ መኳንንቶች፥ በሮችን ክፈቱ፥ የዘላለም ደጆችም ይከፈቱ፥ የክብርም ንጉሥ ይግባ ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? የጭፍሮች አምላክ እግዚአብሔር፥ እርሱ የክብር ንጉሥ ነው በማለት የተናገረው መዝሙር 24 ፥ 6 _ 10 ስለዚህም  እንግዲህ  ደቀ መዛሙርቱም ወጡ ወደ ከተማም ሄደው እንዳላቸው አገኙ፥ ፋሲካንም አሰናዱ የሚለን ከዚህ የተነሳ ነው  ፋሲካን አሰናዱ የሚለው ሃሳብ እንግዲህ የአደረጃጀትን ነገር የሚያስታውሰን ነው በመሆኑም አሁንም እኛም እንደነዚህ ደቀመዘሙርት በጌታ ተልእኮ ለዚሁ ፋሲካ ሰዎችንም ሆነ ሥፍራዎቻቸውን እናመቻቻለን እናዘጋጃለን ደግሞም ጌታ ብሎአልና ጌታ  እንዳለው የማይገናኘን እኛም የማንከተለው የቤቱ ጌታ የለም ቤት ያለው የቤቱ ጌታ ሁሉ ጌታ ስላለ ይገናኘናል እኛም የሚገባበት ድረስ ተከትለን በመሄድ መምህሩ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን የምበላበት የእንግዳ ቤት ወዴት ነው ? ይላል እንላለን እርሱም እንደተባለው በደርብ ላይ ያለውን የተሰናዳና የተነጠፈ ታላቅ  የልቡን አዳራሽ ያሳየናል እኛም ይህ በደርብ ላይ ያለው የተነጠፈው ለጌታ የተገባው ነውና በዚያ ፋሲካን እናሰናዳለን ጊዜያት የማይወስነው ጌታም በምሽት ይሁን በጠዋት ብቻ በወደደው ጊዜ ፋሲካን ሊበላ ወደዚህ ተነጥፎለት ወደተዘጋጀው ከፍታ ይመጣል  ወገኖቼ ሆይ እኛ ይህን ፋሲካ ልናሰናዳ ልናዘጋጅ በጌታ እንላክ እንጂ ለዚህ ፋሲካ የማይሰናዳ ሰገነቱንም የማይለቅ ማንም የለም በመሆኑም ይህ የፋሲካ መሰናዶ  ትልቅ እና ዋናም ነገር ስለሆነ የጌታ ብቻ ሳይሆን ዛሬም የቤተክርስቲያን የሁልጊዜ ምኞትዋ ሊሆን ይገባል ጌታ በቃሉ በዚህ የፋሲካ እራት አስደናቂ ነገር ተናገረ   ሰዓቱም በደረሰ ጊዜ ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ጋር በማዕድ ተቀመጠ እርሱም፦ ከመከራዬ በፊት ከእናንተ ጋር ይህን ፋሲካ ልበላ እጅግ እመኝ ነበር እላችኋለሁና፥ በእግዚአብሔር መንግሥት እስኪፈጸም ድረስ፥ ወደ ፊት ከዚህ አልበላም አላቸው ይለናል የሉቃስ ወንጌል 22 14 _ 17  የመጽሐፉ ክፍል ፋሲካን በሚያርዱበት በቂጣ በዓል መጀመሪያ ቀን ደቀ መዛሙርቱ ፋሲካን ትበላ ዘንድ ወዴት ሄደን ልናሰናዳ ትወዳለህ ? አሉት ይለናልና ፋሲካ የሚታረድበት የቂጣ በዓል የመጀመርያ ቀን በመጀመርያው የትምህርት አደረጃጀት በእግዚአብሔርና በሙሴ ቀን የተዘጋጀ የአይሁድ ፋሲካ የምግብ ዝግጅት ሲሆን ለዚሁ ጌታ የመጨረሻ የጌታ እራት ቀን ሆኖ የቀረበ ነው ይህ ፋሲካ በሐዲስ ኪዳን ለጌታ እራት የትምህርት ይዘትና አደረጃጀት መሰናዶ ሆኖ የቀረበ ቢሆንም በብሉይ ኪዳንም በእግዚአብሔርና በሙሴ ቀን የተዘጋጀ የአይሁድ ፋሲካ የምግብ ዝግጅት በመሆኑ በዚያን ዘመን ሳይቀር የነበረም የትምህርት ይዘትና አደረጃጀት ነበረው ይህንን ለማጥናት ዘጸአት 12 1 _ 14 ዘኁልቁ 9 1 _ 5 የተጻፉትን ክፍሎች ሄዶ ማንበብ እና ማየት ይቻላል  በመጨረሻም ወደዚህ የጌታ እራት የትምህርት ይዘት ስንገባ ይህ የጌታ እራት የኢየሱስ ድርጊትና ቃል የተፈጸመበት በመሆኑ ኢየሱስ ኅብስቱን ወይም እንጀራውን የመቁረስና የማከፋፈል የፋሲካ ቅዳሴ ወይንም ምስጋና ትእዛዝ ክፍል ነበረው በዚህም ክፍለ ጊዜ ኢየሱስ ኅብስቱን ማለትም እንጀራውን እና በጽዋው ውስጥ ያለውን ወይን አንስቶ ሲያከፋፍል ይህ ሥጋዬ ነው ይሄ ደግሞ ደሜ ነው በማለት ተናግሯል የመጽሐፉ ቃልም እንዲህ በማለት ይገልጸዋል ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቈርሶም ሰጣቸውና እንካችሁ፤ ይህ ሥጋዬ ነው አለ ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው፥ ሁሉም ከእርሱ ጠጡ እርሱም፦ ይህ ስለ ብዙዎች የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው አላቸው ይለናል ወገኖቼ ትምህርታችንን ለዛሬ በዚህ እንቋጫለን በሚቀጥለው የክፍል አምስት ትምህርታችን ላይ ከዚህ የቀጠለውን የጌታ እራት ዛሬ ለእኛ ምንድነው ? በሚል ሃሳብ ዙርያ የምናነሳቸው ነጥቦች ይኖሩናል እናንተም አንባቢዎች ይህንን ጥያቄ ለራሳችሁ በመመለስ እየተዘጋጃችሁ ጠብቁ ጌታ ሁላችንንም በነገር ሁሉ ይባርከን ያስተምረን በማለት የምሰናበታችሁ

Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ

ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ ነኝ

ተባረኩልኝ ለዘላለም



No comments:

Post a Comment