Wednesday, January 6, 2016

የመልዕክት ርዕስ በተጻፈልን እንኑር


የመልዕክት ርዕስ


በተጻፈልን እንኑር



በዚያን ጊዜ አልሁ፦ እነሆ፥ መጣሁ፤ ስለ እኔ በመጽሐፍ ራስ ተጽፎአል
አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ፥ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው

መዝሙር 40 7



እኔ በስውር በተሠራሁ ጊዜ፥ አካሌም በምድር ታች በተሠራ ጊዜ፥ አጥንቶቼ ከአንተ አልተሰወሩም
ያልተሠራ አካሌን ዓይኖችሕ አዩኝ፤ የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ
አቤቱ፥ አሳቦችህ በእኔ ዘንድ እንደ ምን እጅግ የተከበሩ ናቸው፦ ቍጥራቸውም እንደ ምን በዛ፦
ብቈጥራቸው ከአሸዋ ይልቅ ይበዛሉ፤ ተነሣሁም፥ እኔም ገና ከአንተ ጋር ነኝ


መዝሙር 139 15 _ 18


ዳዊት በተጻፈለት ሊኖር የተናገረው አንድ እውነታ ቢኖር እነሆ መጣሁ ስለ እኔ በመጽሐፍ ራስ ተጽፎአል የሚል ነው ለእኛም በተጻፈልን ልንኖር የሚያስፈልገን አንድ እውነታ ስለ እኛ በመጽሐፍ ራስ ተጽፎአልና ከማንምና ከምንም በፊት በተጻፈልን ቃል ወደ እርሱ መምጣት ነው ዳዊት አሁንም ወደ እርሱ ሊመጣ የሆነበት ጉዳይ  አቤቱ፥ አሳቦችህ በእኔ ዘንድ እንደ ምን እጅግ የተከበሩ ናቸው፦ ቍጥራቸውም እንደ ምን በዛ ብቈጥራቸው ከአሸዋ ይልቅ ይበዛሉ፤ ተነሣሁም፥ እኔም ገና ከአንተ ጋር ነኝ በማለት የእግዚአብሔር ሃሳብ ከማንም ይልቅ በእርሱ ዘንድ የተከበሩ ናቸውና ለእግዚአብሔር ሃሳብ ራሱን በመስጠቱ ነው   በመሆኑም ወደ እርሱ ለመምጣት ለእኛም  የእግዚአብሔር አሳቦቹ በእኛ ዘንድ እጅግ የተከበሩ ሊሆኑ ፣ ከዚህ የተነሳ ወደ እርሱ ለመምጣት የእኛንም መነሳት ከእርሱም ጋራ መሆንን በእጅጉ የሚጠይቁ መሆናቸውን ከወዲሁ  በውል ልናውቅና ልናስተውል ይገባል ከዚያ  በኋላ ነው እንግዲህ የሕጉ በልባችን መቀመጥና ፈቃዱንም ለማድረግ የመውደድ ነገር ውስጣችን የሚገባው ዳዊት በእነዚህ በተጻፉት እውነቶች ሁሉ እግዚአብሔር የረዳው ሰው ስለነበረ እነዚህ ነገሮች ሁሉ በሕይወቱ ሆነዋል  ወደ እግዚአብሔር መምጣት ቃሉን ዕለት ዕለት  ከእኛ ከአገልጋዮች ከሚሰሙና እኛም ሳናሰልስ ከምናሰማቸው ምዕመናን ብቻ የሚጠበቅ አይደለም ወደ እርሱ ወደ እግዚአብሔር መምጣት እና ሃሳቦቹም በእኛ ዘንድ የተከበሩ ሆነው ፈቃዱን ለማድረግ መውደድ መነሳት ከእርሱም ጋር መሆን ለሁላችንም   የተጻፈልን ስለሆነ ከሁላችንም የሚጠበቅ ጉዳይ ነው  ዳዊት ሌላውን ሳይሆን ራሱን በተጻፈለት መጽሐፍ ውስጥ አይቶ ስለ እኔ በመጽሐፍ ራስ ተጽፎአል አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ፥ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው አለ ስለዚህ ወገኖቼ በተጻፈልን መጽሐፍ ሌሎችን ሳይሆን በቅድሚያ ራሳችንን ማየት ይሁንልን ያን ጊዜ ነው እንግዲህ እኛም እንደ ዳዊት ወደ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ልንመጣ ጊዜ የሚሆንልን ወደ እግዚአብሔር ሳንመጣ ግን  ሕጉን እንዲሁ በተለምዶም ሊሆን ይችላል ብቻ ምንም የሚታወቅ ነገር የለም  እንናገረው እናስተምረው እንስበከው እንዘምረው እንጂ የሕጉ በልባችን መቀመጥም ሆነ ፈቃዱን የማድረግ ውዴታ  ግን በፍጹም አይኖረንም የለንምም  እንደገናም  እኛ  ራሳችንን በተጻፈልን መጽሐፍ ከምናይ ይልቅ ሌሎችን ብናይ ለሌሎችና ስለሌሎችም ብንናገር ወደ እግዚአብሔር ሕጉም በልባችሁ ይቀመጥ ፈቃዱንም ለማድረግ ውደዱ ብንልና ደግመን ደጋግመንም ብንወተውት ይቀናናል  ነገር ግን በዚህ ነገር እኛው እራሳችን ወደ እርሱ ወደ ጌታ ያልመጣን በመሆኑ ባዶ ከሆነው ውትወታችን ውጪ በምንናገራቸውና በምንወተውታቸው ሰዎች ውስጥ ጠብ የሚል ነገር የለም እንደገናም ይሄ ቃል እናንተን አይመለከትም ወይ ስንባል ደግሞ  ከጥቂቶች በቀር አብዛኞቻችን ከተጻፈው ቃል ማዶ ያለን በመሆናችን እኛማ ፓስተሮች አስተማሪዎች ሽማግሌዎችና የመሣሠሉትን ነን ስንል መልስ እንሰጣለን እኛን ወደ ጌታ ወደ እግዚአብሔር ያላመጣ ቃል ደግሞ ቀኑን ሙሉ ስንናገርበትና ስንጮኽ ብንውል ሌሎችን አያመጣም በመጀመርያ ሊያመጣ የሚገባው እኛኑ ራሳችንን ነው እኛ ባልተጻፈልን ከቃሉ ማዶ ሆነን እየኖርን እናንተስ እያለ እኛነታችንን የሚጠይቅና የሚፈትሽ ቃል ሲመጣ እኛማ ሐዋርያት  መጋቢዎች ነቢያት አስተማሪዎችና የመሣሠሉትን  ነን ብንል ወደ ማዶ ሳንሻገር እግዚአብሔርም እርሱ ወደሚፈልገው ክብርና የዕድገት ደረጃም ሳያደርሰን  ስማችንን ብቻ ይዘንና ተቆልለን በደጅ በአፍአ ከምንቀር ውጪ የምናተርፈው ነገር የለም ዳዊት ወደ አንተ መጣሁ ሲል ወደ ጌታ ሊመጣ ስሙና ንግሥናው ዘውዱና ዙፋኑ አልያዘውም ከዘውዱ ከክብሩና ከንግሥናው ይልቅ የጌታ ሃሳቦች በእርሱ ዘንድ እጅግ የተከበሩ ነበሩ ስለዚህ ወደ ጌታ ሊመጣ ሕጉም በልቡ ሊቀመጥና ፈቃዱንም ለማድረግ ሊወድ የተከለከለበትና የታገተበት አንዳች ነገር አልነበረም ለእኛም በሥልጣን ላይ ላለንና ትልልቅ የማዕረግ ስሞች አሉን ስንል  ስለማንነታችን ብዙ በማውራት እኔማ እንዲህና እንዲያ ነኝ ለምንል ለእኛ  በቅድሚያ ለዳዊት የሆነው  ሁሉ ለእኛም ይሁንልን  ታድያ እኛ ከቃሉ ማዶ ሆነን ወደ እኛም መጥቶ እኛነታችንን ለፈተሸውና ለኮረኮረው ቃል ምላሻችን እኛማ እንዲህና እንዲያ ነን ከሆነ ብዙዎችን ሳይቀር ከተጻፈላቸው የእግዚአብሔር ቃል ሃሳብ ጋር እንዳይገናኙ ሕጉም በልባቸው ተቀምጦ የጌታን ፈቃድ የመፈጸም ውዴታ እንዳይኖራቸው በብዙ እየከለከልን ነውና በጌታ ዘንድ እንጠየቃለን ሽማግሌው ነቢይ እኔም እንዳንተ ነቢይ ነኝ በማለት የእግዚአብሔርን ፈቃድ የማድረግ ውዴታውን ሊፈጽም በእግዚአብሔር ቃል ከይሁዳ ወደ ቤቴል ተልኮ ለመጣ የእግዚአብሔር ሰው እንቅፋት ሆነ አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔር ሃሳቦች በእኛ ዘንድ እጅግ የተከበሩ መሆናቸው ሲቀር በምትኩም ስማችንን በቤተክርስቲያንም የተሰጠንን የሃላፊነት ቦታ ብቻ ማክበርና ማስከበር  ስንጀምር እንደገናም አሁንም  ተዋረድን ፈልገን እንዲሁ ለእኛነታችንና ለስማችን ብቻ ጥብቅና ስንቆም ይሄ ሁሉ ይሆናል 1ኛ ነገሥት 13 ምዕራፍን በሙሉ ይመልከቱ እግዚአብሔር ከዚህ ይጠብቀን ይልቁንም እኛም የእግዚአብሔርን ፈቃድ የመፈጸሙ ውዴታ ኖሮንና ፈጽመን ሌሎችም እንዲፈጽሙ ማነሣሣት ነው ያለብን ጌታችን ኢየሱስ ያደረገው ነገር ይህንን ነበር ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ ዮሐንስ ግን፦ እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን ? ብሎ ይከለክለው ነበር ኢየሱስም መልሶ፦ አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው ያን ጊዜ ፈቀደለት ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ የማቴዎስ ወንጌል 3 13 _ 13  ከዚህም ሌላ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 13 1 _ 20 የተጻፈውን ቃል ስንመለከት የደቀመዛሙርቱን እግር ሊያጥብ የማበሻ ጨርቅ ይዞ ለተነሳው ኢየሱስ ደቀመዝሙሩ ጴጥሮስ ባነሳው ጥያቄ ትሁት ጌታ የናዝሬቱ ኢየሱስ የሰጠውን መልስ እንመልከት እውነት ብለሃል ጴጥሮስ ጎሽ በእርግጥም  እኔ እኮ መምሕር እና ጌታ ነኝ እና ተገቢ የሆነን ተግባር እየፈጸምኩ አይደለሁም ሲል እግሮችን ከማጠብ ተግባሩ አልተመለሰም ይልቁንም ለየዋሁ ጴጥሮስ ተገቢውን መልስ ሰጥቶ ከጨረሰ በኋላ በቀጥታ የደቀመዛሙርቱን እግር ወደ ማጠብ ተግባሩ ተመልሶ እግሮቻቸውን አጥቦ እንደ ጨረሰ  ያደረግሁላችሁን ታስታውሳላችሁን በማለት እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብኩ እናንተ ደግሞ እርስ በእርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል ነው ያላቸው ስለዚህ ዛሬ የሚያስፈልጉን ሰዎች እንደ ጌታችን ኢየሱስ ከራሳቸው ይልቅ በትሕትናና ሌላውን በማገልገል ምሳሌ የሚሆኑን ሰዎች ናቸው ከዚህ በተጨማሪም የሕዝቡን ብቻ ሳይሆን የእነርሱንም ማንነትና ሕይወት የሚሰራ ቃል ሲመጣ ቶሎ ብለው ከሥልጣናቸው ጋር በመሆን እኔማ እንዲህና እንዲያ ነኝ የሚሉን ወይንም እንደዚያ እንደ ሽማግሌው ነቢይ የመጣውን የእግዚአብሔርን ቃል  ላለመቀበል ስማቸውን ተገን አድርገውና በስማቸው ለመከላከል ፈልገው እኔም እኮ እንዳንተ ነቢይ ነኝ የሚሉን ሳይሆኑ አሁንም እንደ ኢየሱስ  ቅሌን ማቄን ሳይሉና ምክንያተ ብዙ ሳይሆኑ ራሳቸውን ዝቅ አድርገውና ጽድቅን የመፈጸም ተነሳሽነት አግኝተው ጽድቅን በመፈጸም ሌሎችም ጽድቅን እንዲፈጽሙ መንገድ የሚሆኑ ሰዎች ነው የሚያስፈልጉን ጌታ እግዚአብሔር በዚህ እውነት ሁላችንንም ይጎብኘን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
                              

                               


ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ


የ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለራዕይ

No comments:

Post a Comment