Simon
Pharisee said If this man were a prophet he would have known who and what sort
of woman this is who is touching him for she is a sinner ( Luke 7: 39 )
የትምህርት ርዕስ ፦
የምንሳለመውም ሆነ የምናሳልመው መስቀል ለእኛ የለንም ( ምንጭ ትምህርተ ኅቡአት )
ይህ መስቀል የሚታሰብ እንጂ የሚታይ አይደለም
( ምንጭ ትምህርተ ኅቡአት )
ክፍል ሁለት
የተወደዳችሁ ወገኖች ዛሬ ደግሞ የምንመለከተው በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 7 ፥ 36 _ 50 በተጻፈው ሃሳብ መሠረት በአንዲት ኃጢአተኛ ሴት እውነተኛ ንስሐ መግባት እና ከጌታዋም ጋር መስማማት ቅር የተሰኘ ፣ ያልተዋጠለትና ያልተስማማ ስሞኦን ፈሪሳዊ እፍረት ሳይዘው በገዛ ቤቱ ያስተጋባውን ተቃውሞና የማጉተምተም ድምጽ እንመለከታለን ታሪኩን ከሞላ ጎደል አብዛኞቻችን የምናውቀው ስለሆነ ተራ በተራ መተረክ አያስፈልገኝም ይህቺ ሴት ከኢየሱስ ጋር ልትስማማ እውነተኛ እና ያልተደበቀ ማንነቷን በእርግጥም ለስምኦን ፈሪሳዊ ሳይሆን ለኢየሱስ ነው ያሳየችው ከዚህም ባሻገር ትክክለኛ እርሷነቷንና ድካምዋን በሙሉ አምጥታ በኢየሱስ እግር ስር ጣለች እንዲህ ማለቷ ከዚህ በኋላ የትም መሄድ የማልችል ፣ የተሸነፈ እና የወደቀ ሕይወት ነው ያለኝ አንተ ካላነሳኸኝ ማንም ሊያነሳኝ አይችልም ዓይነት ጩኸትና ልቅሶ እራስን ዝቅ በማድረግና በማዋረድም የሆነ የአቤቱታ ጥሪ ያሰማች በመሆኑ ሉቃስ ወንጌላዊው እነሆም በዚያች ከተማ ኃጢአተኛ የነበረች አንዲት ሴት፤ በፈሪሳዊው ቤት በማዕድ እንደ ተቀመጠ ባወቀች ጊዜ፥ ሽቱ የሞላበት የአልባስጥሮስ ቢልቃጥ አመጣች በስተ ኋላውም በእግሩ አጠገብ ቆማ እያለቀሰች በእንባዋ እግሩን ታርስ ጀመረች፥ በራስ ጠጕርዋም ታብሰው እግሩንም ትስመው ሽቱም ትቀባው ነበረች
እያለ ይዘግብልናል በነገሩ ያልተደሰተና ሁኔታውም ያልጣመው ስምኦን
ፈሪሳዊ ግን ከዚህ በተለየ ሁኔታ ተቃራኒውን መልስ ሲሰጥ እንመለከታለን ስምኦን ፈሪሳዊ ምንም እንኳ በቤቱ ይሄ ሁኔታ የተካሄደ ቢሆንም ለፈሪሳዊው ስምኦን
ግን ይህንን እርሱን የማይመለከተውን መልስ እንዲሰጥ የፈቀደለት ማንም ሰው አልነበረም ስምኦን ፈሪሳዊ ይህን ብቻ አይደለም ያደረገው ከዚህ ባለፈ ሁኔታ ፍርድ ውስጥ ገብቶ መፍረድ ፣ መበየን ፣ መፈትፈት ልበለው አላውቅም ብቻ የሲቲቱንና የኢየሱስን ነገር አንድ በአንድ እየዘረዘረ እያወጣና እያወረደ ማንሳትና መጣል ጀመረ ታድያ ስምኦን ፈሪሳዊ እነዚህ ሁሉ ነገሮች
ውስጥ ገብቶ መዘባረቅን ሲያደርግ ኢየሱስ ግን አንዳች የመለሰለት መልስ አልነበረም ይህ ስምኦን ፈሪሳዊ
የሚገባውን ሁሉ ብሎ እንደመሰለውም ዘባርቆና የታቹን ወደላይ የላዩንም ወደታች አድርጎ ንግጝሩን ከጨረሰ በኋላ ኢየሱስ በጥያቄ መልክ ወደ ስምኦን ቀርቦ ለሌሎች የመናገርን ዕድል መስጠት ላለመደውና ሁልጊዜም
ቢሰሙ ይስሙ ባይሰሙ የራሳቸው ፈንታ በሚል ዓይነትና በማናለብኝነት ለሌሎች የተናገረ ይምሰለው እንጂ ራሱና ለራሱ ብቻ ተናግሮ ለሚጨርሰው ስምኦን ስምኦን ሆይ የምነግርህ ነገር አለኝ በማለት ኢየሱስ ንግጝሩን ቀጠለ ታድያ ኢየሱስ በስምኦን ፈሪሳዊ በነገሩ መሐል ገብቶ
ባያቋርጠውና ስምኦን ሆይ የምነግርህ ነገር አለኝ ባይለው የስምኦን መጨረሻ ምን ሊሆን እንደሚችል ሁላችንም መገመት አያዳግተንም ኢየሱስም ጥያቄውን ለስምኦን ፈሪሳዊ በትክክለኛ ሁኔታ አቅርቦ ከስምኦን ተገቢውን መልስ ካገኘ በኋላ ወደ ሴቲቱም ዘወር ብሎ ስምኦን ይህቺን ሴት ታያለህን ?
በማለት ስምኦን ያልተዋጠለትንና በማይመለከተው ነገር ውስጥም ገብቶ የፈተፈተበትን የፈረደበትንም ትክክለኛ ያልሆነውን የስምኦንን ነገር ለዚሁ ለስምኦን ፈሪሳዊ በማሳየት የዚህችን ሴት ትክክለኛ
እና እውነተኛ አድራጎት ፣ በኢየሱስም ፊት ለምሕረት የቀረበችበትን መንገድ እንዲሁም ከራሱ ከኢየሱስ ያገኘችውን ይቅርታና ሥርየት ነገረው አያይዞም የእርሱን ነገር ከሴቲቱ ጋር እንዲያስተያይና
እውነተኛውንም ነገር እንዲረዳ እንዲህ ሲል እውነታውን ገለጸለት ይህቺ ሴትም ምሕረትን ለማግኘት ካደረገችው ነገር አንዱን እንኳ ይኼው ስምኦን ፈሪሳዊ በገዛ ቤቱ ተቀምጦ ያላደረገ
መሆኑንም በመጠቆም ሴቲቱን
አንቺ ሴት እምነትሽ አድኖሻል በሰላም ሂጂ በማለት እንዳሰናበታት የክፍሉ ሃሳብ በግልጽ ይነግረናል የተወደዳችሁ ወገኖች ሰዎች ምሕረትን ይቅርታንና ሥርየትን እንዲሁም የእግዚአብሔር ልጅነትን አግኝተው ከጌታ ጋር በሰላም ሊኖሩ የሽቶ ብልቃጣቸውንም በእግሩ ሥር ይስበሩ ወይም እንስራቸውንም ጥለው ይምጡ እና በፊቱም ያልቅሱ ይንከባለሉ ይጩኹ
በሆነው ነገር ሁሉ እነርሱና ጌታ ይተዋወቃሉ ለጮኹበት ስቅስቅ ብለውም ላለቀሱበት
በእግሩም ሥር ተደፍተውና ዝቅ ብለውም ለተንከባለሉበት ነገር ያገኙትን ምሕረት
እነርሱና ምሕረትን
እንዲሁ በነጻ የሰጣቸው ጌታ ነው የሚያውቁት ታድያ እኛ አገልጋዮችና እንደ ስምኦንም ቤተኞች ነን አልፈን ተርፈንም የሕዝብ አለቆች ፓስተሮችና መሪዎች ነን እያልን ሰዎች ከጌታ ጋር በጨረሱትና እየጨረሱም ባለ ነገር ውስጥ ጣልቃ ገብተን ያቺ ሴት በስምኦን ቤት እንዳደረገችው ከዚህም ሌላ
ሳምራዊቷም ሴት በሰማርያ መሲሁን ልትገልጥ እንስራዋን እንደጣለችው ዓይነት በዘመናችንም ይህን የመሰሉ በጌታ የተነኩ
የተለያዩ ሰዎች አሉና
እነርሱና ጌታ ካላቸው የግንኙነት ሕይወት የተነሳ እያደረጉት ባለ የቃላት ልውውጥና አደራረግ መሐል ገብተን የምንፈተፍት ስንችል የምንከለክል ሳንችል ደግሞ ፊታችንን ወደሌሎች መልሰን የምንፈርድ ፣
ሰዎችንም የፍርደ ገምድልነታችንና ፣ የብያኔያችንም ተካፋይ እንዲሆኑ ያለልክ የምናሳምጽ ፣ ለዚሁም የተሳሳተ ብያኔያችን
ሰዎችን የምናነሳሳ ብዙዎች ነን ታድያ ይህንን አስነዋሪ ድርጊት እንፈጽም ዘንድ የተነሣሣን እኛ ማነን ? ሰዎች እንስራቸውንም ይጣሉ የሽቱ ብልቃጣቸውንም ሰብረው ይምጡ ብቻ የሚፈለገው የእኛ ንብረት እንዲሆኑ ሳይሆን በመጡበት መምጣት ለኢየሱስ እንዲሆኑ ነው ከበፊቱም ገና ሲመጡ ደግሞ የእኛ ንብረት ቢሆኑማ ገና ለገና አመጣጣቸውን አይተን አሁን ካለን ከምናሳየውም አልባሌ ድርጊት የተነሳ በተለይም ለአንዳንዶች
ቦታ አይኖረንም ነበር ኢየሱስ ግን ወደኔ የሚመጣውን ወደ ውጪ አላወጣውም የሚል ድምጽ ያለው በመሆኑ ከዚህ በፊትም ወደርሱ የመጡትን ሳያማርጥ ሁሉንም እንደየአመጣጣቸው ተቀብሏል ዛሬም ይቀበላል ስለዚህ የመጡት ሰዎች
ወደፊትም የሚመጡት ወደ እኛ
ሳይሆን የሚመጡት ወደ ኢየሱስ ነውና
ስምኦን ፈሪሳዊ በማይመለከተው ነገር ውስጥ በመግባት ቤቴ ነው ብሎና ቤተኛ ሆኖ በዚያች ሴት እንዲሁም በኢየሱስም ሳይቀር እንደፈረደ በዚህ ነገር ቤተኛ ፓስተር ነኝ መሪ እና ሃላፊ ነኝ ይመለከተኛል የምንል ሰዎች እንደፈሪሳዊው ስምኦን እንዳንሆን አብዝተን ልንጠነቀቅ
ነገራችንንም እንደ እግዚአብሔር ቃል ልናደርግ ይገባል ስምኦንስ በቤቱ የሽቱ ብልቃጥ ይዛ በኢየሱስ እግር ሥር የተንከባለለችውንና ኢየሱስንም ሽቶ የቀባችውን ሴት እንደገናም ኢየሱስንም ጭምር የፈለገውንና ያሻውን ሁሉ ተናግሯቸዋል ፣ ያልተመረጡ ያልተሟሹ የስድብ ቃሎችንም ሁሉ አዝንቦባቸዋል እኛ ግን አሁን ላይ ያለን እራሳችንንም እንደ ስምኦን ቤተኛ ያደረግን ወይንም ቤቴ ነው ፣ መስራችና መሪ ፓስተር ባለራእይም ነኝ ስንል የተቀመጥንና ራሳችንንም ያስቀመጥን መሥራች ባለራእይም እንባል ሌላም ሌላም
እኛ ምናልባትም በቤቱ የአገልግሎት ባላደራዎች ነን እንጂ ከዚህ ውጪ ምንም ልንሆን አንችልም ቤቱ ግን የእኛ ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔርም ቤት ስለሆነ ወደ እግዚአብሔር ቤት አምነው ለመጡ ሁሉ
ቤቱ ቤታቸው ነው በመሆኑም የእግዚአብሔር ቤት የስምኦን ፈሪሳዊውና እርሱን የመሠሉ ሰዎች ቤት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ቤት ነው ከዚህ የተነሣም ቀራጮች ፣ ዓለምና ሰይጣን ኃጢአትም ጭምር የተጫወተባቸው ሰዎች መጥተው ከአዳኛቸው ከኢየሱስ ጋር በመገናኘት የሚፈወሱበት ቤት
ስለሆነ በቤቱ ውስጥ ሆኖ በመፋነን ይህ ቤቴ ነውና እንደገናም መስራችና መሪ ፣ ሃላፊም ነኝና ምን ልሆን እችላለሁ ? በሚል ሰበብ ልኩን አጥቶ አቅሉንም እንደሳተው እንደፈሪሳዊው
ስምኦን እኛም በእግዚአብሔር ቤት እንደፈለግን የምንሆንበት ያሻንንም የምንናገርበት ቤት
አይደለምና ስተን በመገኘት ከመስመር እንዳንወጣ ብርቱ ጥንቃቄ ልናደርግ ያስፈልገናል ሰዎች ከአልባሌም ሥፍራ ይምጡ ከየት ብቻ የሚፈለገው ለኢየሱስ መሆናቸው
ስለሆነ ለኢየሱስ ከሆኑ በቂ ነው እኛ ግን ከተራና ከአልባሌ ሥፍራ መጥተው በትክክል ለኢየሱስ የሆኑበትንና ኢየሱስም ሳያፍርባቸው ልጄ ብሎ የተቀበለበትን ኃጢአታቸውንም በደሙ አጥቦ ይቅርታን የሰጠበትን ፣ የእግዚአብሔርም የቤተሰቡ አባላት ያደረገበትን ሕይወት ከግል ፍላጎታችን አለመሳካትና አለመሟላት ተነስተን የምንፈልገውን ነገር ስላላገኘን ፣ ወደ ጌታም የመጡት ሰዎች እኛ እንደፈለግነው መጠን ስላልሆኑልን እና የፈለግነውንም ስላላሟሉልን ብቻ ይህንኑ ለጌታ የሆኑበትን የማንነት ሕይወታቸውን ስናቃልል ስናንቋሽሽና ስንኮንን እንታያለን
ወገኖቼ ታድያ ይህ የጤና ይመስለናል አይደለም ይህ የጤና ሳይሆን
ስምኦንነት እና ፈሪሳዊነትም ነው የጌታ ሕዝቦች
ክርስቶስ ለሰዎች በነጻ የሰጠውን እነርሱም ከጌታ
ለእኔና የእኔ ሲሉ የተቀበሉት ምሕረት ፣ ሥርየት ፣ ይቅርታ ልጅነት ብቻ አለመሆኑን ተረድተው
አልፎ ሄዶም ጌታን ወደ ማገልገል ሕይወት ሲመጡ እነዚሁ
ሰዎች ጌታን ለማገልገል ሲሉ የተቀበሉትን ጸጋና በረከት ፣ አገልግሎት እንዲሁም የአገልግሎት ጥሪን ሁሉ አሁንም እናቃልላለን ፣ እናንቋሽሻለን
ይህ ታድያ ዛሬም እኔ ብቻ ከሚል ስሜት የመነጨ ተጣብቆም ያለና ያልተቆረጠ የፈሪሳዊው ስምኦን ባሕርይ ነው ስምኦን ያቺ የሽቶ ብልቃት ይዛ የመጣች ሴት ከኢየሱስ ጋር ባላት ግንኙነት ያለመደሰቱ ምናልባትም ያ የለመደው ነገር
ስለቀረበት የተቃወመ አስመስሎበታል ታድያ ይህንን ሁኔታ ከዛሬው ስምኦናዊ የክህነት ማንነት ጋር ስናስተያየው በዛሬው ሕይወታቸውም ያሉ መስቀል ማሳለሙና ነፍስ አባትነቱ የቀረባቸው ካህናት የሚያንቋሽሹትና የሚጠሉት ወደ ኢየሱስ የመጣውንና ኢየሱስንም ጭምር ነው ለምን እንዲህ አምርረውና ተገታትረው ተቆጥተውም
ያንቋሽሻሉ ያሳድዻሉ ይጠላሉ ይቃወማሉም ስንል ሌላ ምንም ተፈልጎ የሚገኝ እነርሱነታቸውንም ብሶተኛ ያደረገ በቂ ምክንያት የላቸውም ትልቁ ምክንያታቸው ነፍስ ልጅ የሚሆን ፣ መስቀል የሚሳለም ዝክርና ተዝካር የሚያወጣ ስለጠፋ ነው ወደ ኢየሱስ የመጣ ሁሉ ከእነዚህ ነገሮች
ነጻ የወጣና የተገላገለ ስለሆነ ይህን እነርሱ የሚፈልጉትን ነገር ሁሉ አያደርግም ይሁን እንጂ ታድያ ሰዎችን ወደዚህ ጌታ በመጥራት ሰዎች ከነዚህና ከመሣሠሉት አሳሳቢ ችግሮች ነጻ ወጥተው የጌታና ለጌታ ብቻ ሆኑ ስንል አሁን ደግሞ ያልጠበቅናቸው የፈሪሳዊው ስምኦን ቀሚስና ቆብ ጥምጣምም ያልታየባቸው ነገር ግን ያማሩ ሱቶችን ለብሰውና ከረባትም አስረው በፈሪሳዊው ስምኦን
የባሕርይ ማንነትና ልክ የሚመላለሱ ትክክለኛና መልካምም ሊመስሉ ሽቶ የተነሰነሱ አንዳንድ ፓስተር ተብዬዎች ከየትኛው ጓሮ ብቅ እንዳሉ ባናውቅም ብቻ ከእንጨት ይሁን ከብረት የማይታወቅ የራሳቸውን መስቀል መሳይ ማሳለምያ ሰርተው መስቀሉን እንኳ ባይሆን እኔን ተሳለሙ ዓይነት ሥራ መጀመራቸው ፣ ወንጌሉም የኢየሱስ መሆኑ ቀርቶ የእነርሱ እንዲሆንና በኢየሱስ መካከለኝነት ፈንታም እነርሱኑ መካከለኛ ያደረገ ፣ የነፍስ አባትነትንም ሥራ ሳያውቁት ውስጥ ለውስጥ ማካሄዳቸው ከሚያሳዩት ተግባራቸው በጥቂቱም ቢሆን ማስተዋል ችለናል ታድያ ይህ ሁሉ ነገር በእኔ ፣ ከእኔ ፣ ለእኔ ፣ እኔ ያላወቅሁት ፣ እኔ ያልተገኘሁበት ፣ እኔ ያልተናገርኩትና እኔ ያልሰበኩት ፣ እኔም ያልባረኩት
፣ እኔ ፣ እኔ ፣ ሥልጣኔ ፣ ሥልጣኔ ከሚል የማንነት አካል የመጣ ስለሆነ እኛንም ጉዞው ወዴት ይሆን ? የሚል አሳሳቢና አወዛጋቢ ጥያቄ ውስጥ ከቶናል ደግሞም በዚህስ ሁኔታ የነዚህ አንዳንድ ፓስተር ተብዬዎች
ባሕርያቸውና ሕይወታቸው ሳይለወጥ በዚሁ ከቀጠለ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል መካከለኛ ሆኖ ሰውና እግዚአብሔርን ያስታረቀው ኢየሱስስ ምን ይስራ ? ይሁን እንጂ አሁንም እኛ ከሰማይ ሳይቀር እሳት
የምናወርድ ፓስተሮችም እንሁን ታላላቅ መሪዎች ሰዎች ስለሆንን
እነዚሁ የተጠሩ ሰዎች ወደ እኛ ሳይሆን ወደ እግዚአብሔር ዘወር እንዲሉ ነው ወንጌል የምንሰብከው ጌታ እግዚአብሔርም ወንጌል ሰባኪዎችና አስተማሪዎች እረኞችም በሉት ነቢያት የፈለጋችሁትን በጸጋ የተገኘውን የአገልግሎት ኦፊስ ብትጠሩ የተጠራነው ወንጌልን ለመስበክና የእግዚአብሔርንም ቃል ለማስተማር ነው የእግዚአብሔርን ቃል የማስተማርም ሆነ መስበክ ደግሞ የውዴታ ግዴታችን ነው ከዚህ ውጪ እኛም ከዚህ በፊት እንደሰበክናቸውና ዛሬም እንደምንሰብካቸው ዓይነት ሰዎች እንዲሁ ሰዎች ነን እንጂ ከዚህ የተለየን አይደለንም የሐዋርያት ሥራ 14 ፥ 8 _ 18 ሰማይን ከእግዚአብሔር ጋር ተስማምቶ የለጎመው ኤልያስም እንኳ እንደ እኛው ሰው ነበር ተብሏል ወገኖቼ ታድያ ሰው መሆናችንን የምናምነውና የሚገባን እንደ ኤልያስ ሰማይን ለጉመን ሳይሆን በሕይወታችን በመጡ አንዳንድ ነገሮችም እኔ ከአባቶቼ አልበልጥምና ግደለኝ ስንል ከክትክታ ስር ወድቀን የልመናም ጸሎት ውስጥ ገብተን ነው ሰው መሆናችን አልገባን ከሆነ ደግሞ እግዚአብሔርም እንዲገባን
ዛሬም ቢሆን የኤልያስን የምሬት ዘመንና ልመናን ከዛም ያለፈ ነገርን ሁሉ ሊያመጣብን ይችላል ስለዚህ ስለማንነታችንና ጌታንም እናከብረው ዘንድ ስለተሰጠን ጸጋ
ስናስብ እነዚህን ሁሉ ነገሮች
ከግምት ውስጥ ማስገባትና ሁኔታዎችንም መለስ ብለን መቃኘት ይኖርብናል ሐዋርያም ሆነ መጋቢ ፣ አስተማሪ ፣ ነቢይና
የመሣሠሉትን መባላችን ከእግዚአብሔር ጸጋ የተነሣ ነው ያውም ሐዋርያው እንደነገረን መጋቢም ይሁን ነቢይ ወይም አስተማሪ ተብለን ልንጠራ የማይገባን ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ
የሆንን ነን እንደገናም አድርጉ የተባልነውን ከጌታ የተነሣ ያደረግንና ወደፊትም የምናደርግ ነን እንጂ እኛው በእኛነታችን ምንም አይደለንም የምናደርገውም አንዳች ነገር የለም ይልቁንም እኛ የማንጠቅም ባርያዎች ነን የሸክላ ዓይነት ሕይወት በያዝነው በእኛነታችንም ውስጥ ጌታችን የከበረን መዝገብ አኖረ ይህንንም ያደረገው የኃይሉ ታላቅነት ከእኛ እንዳይሆን ነው 1ኛ ቆሮንቶስ 15 ፥ 9 _ 11 ፤ የሉቃስ ወንጌል 17 ፥ 10 ፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 4 ፥ 7 _ 11ን እንመልከት ወገኖቼ የመጽሐፍቅዱሱ እውነት የሚያስተምረን እንግዲህ ይህንን ነው ከዚህም ሌላ በ2ኛ ቆሮንቶስ 1 ፥ 24 ለብዙዎች ደስታ ከሌሎች ጋር የምንሰራ ነን እንጂ በሰዎች
በእምነታቸው ላይ የምንገዛ አይደለንም በእምነታቸው ራሳቸውን ችለው የቆሙ ፣ ወደፊትም የሚቆሙ ይኖራሉና ወገኖቼ በመሆኑም እነዚህን ሁሉ እውነቶች በመረዳትና በማስተዋል የጌታን አገልግሎት
ለራሱ ለጌታ ክብር ልናደርግ ይገባል ጌታ በዚህ ሁሉ ማስተዋልን ይስጠን የክፍል ሁለት ትምህርቴን እንግዲህ በዚሁ አጠቃልላለሁ ተባረኩ የክፍል ሦስት ትምህርት ይቀጥላል
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ
ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ
No comments:
Post a Comment