Monday, June 29, 2015

የጌታ እራት ክፍል ሁለት

የጌታ እራት


ክፍል ሁለት




የተወደዳችሁ ወገኖች ይህ ዛሬ ይዘንላችሁ የቀረብነው ትምህርት የክፍል ሁለት ትምህርት ነው በክፍል አንድ ትምህርታችን ላይ የጌታን እራት መውሰድ አስመልክቶ ቅዱሳን የእግዚአብሔር ሕዝቦች የጌታን እራት መውሰድ ሲለማመዱ 1 ቆሮንቶስ 10 16 ላይ የተጻፈውን ቃል መነሻ በማድረግ ሊሆን እንደሚገባ ከማብራርያ ጋር ጠቅለል ያለ ሃሳብ ወስደን በሰፊው ተማምረናል የዛሬው የክፍል ሁለት ትምህርት ከዚሁ የቀጠለ ነው በዚህ ክፍለ ትምህርት የጌታን እራት የምንጠቀመው በ1ኛ ቆሮንቶስ 11 20 መሠረት ነው የመልዕክቱ ክፍል እንዲህ ይላል እንግዲህ አብራችሁ ስትሰበሰቡ የምትበሉት የጌታ እራት አይደለም በመብላት ጊዜ እያንዳንዱ የራሱን እራት ይበላልና አንዱም ይራባል አንዱም ይሰክራል ይለናል ከዚህ ሃሳብ እንደምንረዳው እንግዲህ ሰው የጌታን እራት ለመውሰድ ይሰበሰባል ነገር ግን የተሰበሰበ ሁሉ ስለተሰበሰበ ብቻ የጌታን እራት መውሰድ የለበትም ይህንን ያልኩበት ትልቅ ምክንያት ስላለኝ ነው ብዙ መንፈሳውያን ነን የሚሉ ሰዎች በምን ጉዳይ ይሁን በምን አይታወቅም ስለተሰበሰቡና ስብሰባቸውም ስለተቃናላቸው ብቻ እንዲያው በሞቅታ ተነስተው የጌታን እራት በቤተክርስቲያን በቅዱሳን ኅብረት መካከል ሳይሆን በያሉበት መንደርና ቀዬ ሁሉ እንውሰድ ይላሉ በትክክልም ይወስዳሉ ማለትም  ተነስተው እነርሱ የጌታ እራት ነው ብለው ያሰቡትንና  የሰየሙትን  ለእነርሱም የጌታ እራት የሆነላቸውን መልካም ያደረጉ እየመሰላቸው ይሁን አይታወቅም አሜን ሃሌሉያ በማለት እየተሳሳቁ ይወስዳሉ ታድያ የጌታ እራት ነው ያሉት የጌታ እራት የሆነው የጌታም እራት የተባለው ለእነርሱ ብቻ እንጂ ለክርስቲያኑ ሁሉ አይደለም ይህ እራት ክርስቲያኑን ሁሉ ይወክላል ብዬ እኔ በበኩሌ አላምንም መጽሐፍቅዱሳችንም በዚህ ነገር ላይ የሚያስተምረን ነገር የለም  እንደገናም ይህንን እራት ክርስቲያኑ ሁሉ ባይወስደውም ትክክለኛ  ነው ብሎ ያጸደቀውና የተቀበለው የጌታ እራት አይደለም  ይህ እራት የጌታ እራት ተብሎ ይጠራ እንጂ ጌታም አያውቀውም ስለዚህ ይህ እራት ሰዎች ሆን ብለው በጌታ ስም ለዓመፃቸው ማስፋፍያ ያዘጋጁት በማናለብኝነትና በድፍረትም የጌታ እራት ሲሉ የሰየሙት እንጂ ትክክለኛና እውነተኛ የጌታ እራት አይደለም ወገኖቼ ሃሳባችን ስለሰመረልን ብቻ እንዲያው በሞቅታ ለሃሳባችን ስኬት ከሌሎች ጋር በተስማማንበት ጉዳይ ሁሉ የምንወስደው የጌታ እራት የለም የጌታ እራት ከክርስቶስ ጋር አንድ አካል መሆናችንን የምንገልጽበት እንደገናም ከዚሁ ጌታ የተነሳ እኛ ቅዱሳን እርስ በእርሳችን ያለንን አንድነት የምናሳይበት  ቅዱስ እራት ወይንም በእንግሊዘኛው ሆሊኮሙኒየን እንጂ በየሠፈሩ በተስማማንበት ተራ የመንደር ወሬዎቻችንና የስምምነት ቃላቶቻችንን ልናጸድቅ የምንመገበው  በምጣዳችን ላይ የተጣደ  የኩሽናችን እንጀራና የቤታችን ቂጣ አይደለም ይህን የምናደርግ ሰዎች ከዚህ የከፋ ድርጊታችንና ትዕቢታዊ ድፍረታችን ፈጥነን እንመለስ አለበለዚያ በእግዚአብሔር እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነውና በደጃችን ያለው የእግዚአብሔር ፍርድ ዛሬውኑ  ያገኘናል የምንወያይባቸው የከበሩ የቤተክርስቲያን አጀንዳዎችና ለቤተክርስቲያንም የሚጠቅሙ መንፈሳዊ ነገሮች ቢሆኑም እንኳ ከእነርሱ መልስ ስምምነት ላይ የደረስንባቸውን ሃሳቦች ለማጽናት ስንል የጌታ እራት ብለንና ሰይመን የምንወስደው ቅዱስ እራት የለም ለስምምነታችን ማጽኛና ለአንድነታችንም መግለጫ መብላት ካለብን መብላት ያለብን የቤታችንን እራት ወይንም ምሳችንን በየግል ቤቶቻችን  ካልሆነም ሌላ ቦታ ሄደን በመገባበዝ ሊሆን ይገባል ይህ ግብዣ ካለ እንግዲህ ይህ ግብዣ የተቀደሰ ሃሳብ ያለበት ግብዣ ስለሆነ እኛም ይልመድ ይቀጥል ስንል ልናበረታታ እንወዳለን  ከዚያ ውጪ ያለውን የመንደር ውስልትና ግን በጌታ ስም እንቃወመዋለን ይሁን እንጂ  መጽሐፍቅዱሳችን አሁንም የፍቅር ግብዣ እንዳለ ይናገራል ታድያ  ይህንንም ግብዣ እንኳ ቢሆን በፍቅርና ከእውነተኛ ልብ ሆነን እንድናደርገው መጽሐፉ የሚናገር ነው  2 ጴጥሮስ 2 13 የይሁዳ መልእክት 1 12 ከዚህም ሌላ ቤተክርስቲያን ይህንን እውነት ተረድታ በቤተክርስቲያን ካሉ መርሃ ግብሮችዋ ወይም ፕሮግራሞችዋ ባሻገር በየመንደሩ ያቋቋመቻቸውን የመጽሐፍቅዱስ ጥናቶች ፣ ልዩ ልዩ የጸሎት ኅብረቶችዋን ያላቸው እንቅስቃሴና አሠራር ከወዲሁ ምን እንደሚመስል እንደሚገባ ተከታትላ ልታውቅ ፣ ልታጤን ይገባል ምክንያቱም የስሕተት አሠራሮች ሾልከው ሲገቡ ፊት ለፊት በበር አይመጡም የሚጀምሩት ከመንደር ድብቅ ሆነው ነው ይህ እንግዲህ አባልን ሳይሆን አካልን የማነጽ ሥራ በመሆኑና እኔንም ይህ ጉዳይ የሚመለከተኝ ስለሆነ ለማሳሰብ ያክል ይህን ተናግሬያለሁ ሌላው ሳልናገር የማላልፈው የጌታ እራት መወሰድ ያለበት በቤተክርስቲያን በቅዱሳን ኅብረት መካከል የቤተክርስቲያን መሪዎችና አገልጋዮች ባሉበት ሊሆን ይገባል ለዚህ ነው መጽሐፍቅዱሳችን መጠባበቅን ቅድሚያችን አድርገን በመውሰድ እንግዲህ አብራችሁ ስትሰበሰቡ የምትበሉት የጌታ እራት አይደለም ማንም የራበው ቢኖር ለፍርድ እንዳትሰበሰቡ በቤቱ ይብላ የቀረውንም ነገር በመጣሁ ጊዜ እደነግጋለሁ የሚለን 1 ቆሮንቶስ 11 20 _ 22 1 ቆሮንቶስ 11 34 የጌታ እራት ከክርስቶስ ጋር ባለንም ሆነ የእርስ በእርስ ኅብረት በጌታ እራት ምክንያት አንድ አካል መሆናችንን የምንገልጽበት መንገድ እንጂ  የረሃብተኞች ማስታገሻ ፣ yeየእሽቅድምድም ሥፍራና  የጥሎ ማለፍ ውዽድር አይደለም 1 ቆሮንቶስ 10 16 _ 18 ይህ የጌታ እራት የፍቅር እራትና አንድ አካል መሆናችንን የምንገልጽበት እራት ስለሆነ በውስጡ ምህረትና ይቅርታ እንደገናም ስለዚህ ወንድሞች ሆይ ለመብላት በተሰበሰባችሁ ጊዜ እርስ በእርሳችሁ ተጠባበቁ የሚል ቃል ስላለበት 1 ቆሮንቶስ 11 33  ራስን የመመርመር ሕይወት በተጨማሪም የአባልነት  ሳይሆን የአካልነት ስሜት ግድ ብሎን ለወንድሞችና ለእህቶች በመራራት ሌላውን ወንድምና እህትም የመጠባበቅ ሕይወት አለበት  በዚሁ በ1ኛ ቆሮንቶስ 11 20_ 22 መሠረት የቆሮንቶስ ሰዎች ግን የተሰበሰቡት የጌታን እራት ለመብላት ቢሆንም በሆዳምነታቸውና በአድልዎኝነታቸው ይህንን የጌታ እራት አረከሱት ታድያ ይህ ዓይነት ባሕርይ ዛሬም ላይ ባለችዋ ቤተክርስቲያን ይንጸባረቃል በጌታ እራት ላይ መስገብገብም ሆነ አድሎኝነት  አለ ሰዎች ለራሳቸው እንዳመቻቸው አድርገው የጌታን እራት አዘጋጅተው ይሰጣሉ ይህ እንግዲህ ዋናውና ትልቁ አድሎኝነት ስግብግብነት እና ሆዳምነት ነው የጌታን እራት  መስጠት ያለብን ለራሳችን ባመቸን መንገድ አዘጋጅተንና ሆን ብለን ወይንም ሌላው ከእኛ ጋር መሆኑንና አለመሆኑን ለማረጋገጥና ለመፈተን ብለን ሳይሆን ሁሉም ሰው በዚህ እራት እንዲሳተፍ የጉባኤውን መንፈስ ጠብቀን ሊሆን ይገባል እኛ ክርስቲያኖች እንዲሁም አገልጋዮች እኛው ለራሳችን እራሳችንን እየመረመርን የጌታን እራት የምንወስድ እንጂ  ለራሳችን ስንል ይህንኑ እራት ለመውሰድ የምናዘጋጀው አንድም መንገድ የለም በዚህ ጉዳይ ላይ ደግሞ ራሳችሁን መርምሩ ተባልን እንጂ ሌላው ከእኛ ጋር መሆኑንና አለመሆኑን እንድናውቅ መርማሪና ፈታኝ አድርጎ ያስቀመጠን አንድም የአካል ክፍል የለም እንደገናም ሌላውን እንመረምራለን ስንል እራሳችን ተመርምረን እንዳንወድቅ ለራሳችን ከወዲሁ ልናስብበትና ልንጸልይ ይገባል  ይህ በእርግጠኝነት በሕይወታችን በሚሆንበት ጊዜ እንግዲህ በአካል መካከል ልዩነት አይኖርም  እና  ቃሉም እንደሚነግረን አንዱ አይራብም ሌላው ደግሞ አይሰክርም አንዳች የሌለው የሚመስለውም አያፍርም  ፣ የእግዚአብሔር ማኅበርም አይናቅም ወገኖቼ የምናነበውን አስተውለን እንድንጠቀምበት ጌታ በኃይሉ ችሎት ይርዳን ተባረኩልኝ

Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry

አገልጋይና ባለ ራዕይ      


ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ