Monday, June 8, 2015

ብዙ ዓይነትና ተለዋዋጭ የሆኑ ጥቅሶችን በአንድ ባለቤትነት ባለው ነገር ውስጥ ማነጻጸር Comparing Various Verses on the same Subject ክፍል አምስት ንዑስ ክፍል አንድ

ብዙ ዓይነትና ተለዋዋጭ የሆኑ ጥቅሶችን በአንድ ባለቤትነት ባለው ነገር ውስጥ ማነጻጸር


Comparing Various Verses  on the same Subject  


ክፍል አምስት


ንዑስ ክፍል  አንድ



ይህንን ሃሳብ እንደሚገባ ለመግለጽ እንዲያመቸን የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 3 ቊጥር 16 በምሣሌነት ብንወስድ ብዙ ሕዝብ የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 3 ቊጥር 16 መሠረት በማድረግ ያምናል በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና ይለናል የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 3 ቊጥር 16 ኢየሱስን በማመን ሁላችንም በቀላሉ የምንፈልገውና የምናደርገውም የዘላለምን ሕይወት ለመውረስ ነው ነገር ግን ይህ ጠቅላላ ታሪኩ ነው በያዕቆብ 2 19 ላይ ግን እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል ይለናል እግዚአብሔር ከእኛ የሚጠብቀውንና የሚፈልገውን በእርግጠኝነት እንመልከት በሙላትም እንረዳ ጌታ እግዚአብሔር በእርግጥም ከእኛ የሚፈልገውና የሚጠብቀው ሕያው የሆነና የሚንቀሳቀስ እምነት ነው እምነታችን ሕያው ሲሆን ድርጊትን ያስከትላል ይህ ከሌለበት ግን እምነታችን በራሱ የሞተ ነው በእርግጥ ደኅንነት እግዚአብሔር ለእኛ የሰጠው አስደናቂ ስጦታ ነው ይሁን እንጂ ስጦታዎች ሁኔታዎች አሏቸው በብዙ ቦታዎች መጽሐፍቅዱስ የሚያሳየን እግዚአብሔር በእርግጠኝነት ያበጃቸው ሁኔታዎች ደኅንነትን እንድንቀበል ነው አንዳንድ ሁኔታዎች ስጦታን እንድንቀበል አላስቻሉንም አንዳንድ ሁኔታዎች ደግሞ እንድንቀበል የተሟላን አላደረጉንም ኢየሱስ የደኅንነታችን ጀማሪና ፈጻሚ የሃይማኖታችን ሐዋርያና ሊቀህናት ነው በትንቢተ ኢሳይያስ 53 5 ላይ እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን ይለናል በዕብራውያን 3 1 ላይ ደግሞ ስለዚህ፥ ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ፥ የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ፤ ይለናል ነገር ግን በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ የዘላለምን ሕይወት ስናገኝ ምን ማድረግ እንደሚገባን እንመልከት በማቴዎስ ወንጌል 7 21 ላይ በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም ይለናል የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማድረግ ከንስሐ እና ኢየሱስንም በማመን ከመቀበል ይጀምራል ለዚህ ነው መጥምቁ ዮሐንስ አገልግሎቱን ሲጀምር መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ  ግቡ በማለት የተናገረው በተመሣሣይ መልኩ ኢየሱስም የመጀመርያ አገልግሎቱን በጀመረ ጊዜ የተነሳበት ሃሳብ መንግሥተሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ የሚል ነው የማቴዎስ ወንጌል 3 1 እና 2 የማቴዎስ ወንጌል 4 17 ኢየሱስን ስንቀበል በእውነተኛ ንስሐና በእምነትም ጭምር ካልሆነ በቀር ዋጋ የለውም ተቀብለናል ለማለትም አያስደፍረንም በጌታ እግር ሥር የሽቶ ብልቃጥዋን ይዛ የተደፋችው ማርያም ቀራጩ ዘኬዎስ እና የመሣሠሉት ጌታን የሕይወታቸው ጌታና መድኅን አድርገው የኃጢአትን ሥርየት ያገኙት እውነተኛ ንስሐ ገብተውና አምነውም ጭምር ነው የሉቃስ ወንጌል 7 36 _ 50 የሉቃስ ወንጌል 19 1 _ 9 ማመንና እውነተኛ ንስሐም ገብቶ ጌታን መቀበል ትክክለኛ የሆነውን የጌታን ፈቃድ ከማድረግ የሚጀምር ነው በዚህ እውነት ውስጥ ሳንሆን ግን ጌታን አምነን ተቀብለናል በማለት ጌታ ጌታ ብንል ጌታ የሚለን አላውቃችሁም ነው በእውነተኛ እምነትና ንስሐ ጌታን የተቀበሉ ሰዎች እምነታቸው ሕያውና የሚንቀሳቀስ ነው እምነታችን ሕያው በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ ጌታን ተቀብለናልና  በቃ ብለን ብቻ የምናቆም አንሆንም እምነታችን ሕያውነት ያለው ስለሆነ በተግባር የምንገልጠው እንሆናለን ጌታም ሕያው እምነት ላላቸው ደቀመዛሙርቱ ነው በዮሐንስ ወንጌል
13 ፥12 _ 15 ላይ እግራቸውንም አጥቦ ልብሱንም
  
አንሥቶ ዳግመኛ እንዲህም ተቀመጠ፥ አላቸው፦ ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን ?
ናንተመምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ፤ እንዲሁ ኝና መልካም ትላላችሁ እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ፥ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና ያላቸው ሕያው የሆነ እምነት በተግባር የሚገለጥና ምሣሌነት ያለው በመሆኑ ሐዋርያው ጳውሎስ ጢሞቴዎስን ይህን እዘዝና አስተምር በቃልና በኑሮ በፍቅርም በእምነትም በንጽሕናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን እንጂ፥ ማንም ታናሽነትሕን አይናቀው እያለ ሲመክረው እንመለከታለን 1 ጢሞቴዎስ 4 11 እና 12 ይህ ትምህርት እንግዲህ በአጠቃላይ ሙሉ አድርጎ የሚያስተምረን ኢየሱስን ስላመንን ብቻ የምንፈልገውን ለማግኘት ስንል ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ ማለቱ ለእኛ በቂ አለመሆኑንና የእግዚአብሔርን ፈቃድ ወደ ማድረግ ሕይወት መምጣት እንዳለብን የሚጠቁመን ነው ትምህርቱ በዚህ ሊቋጭ የማይችል ስለሆነ የሚቀጥል ነው በቀጣዩ ሃሳብ እስከምንገናኝ ስላም ሁኑ በማለት የምሰናበታችሁ


ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ ነኝ


ጌታ ይባርካችሁ





No comments:

Post a Comment