Wednesday, June 3, 2015

ዓረፍተ ነገሩ ወይም የየምዕራፉ አንቀጽ የተጻፈበት ሃሳቡን መመርመር Consider the Context ክፍል ሦስት

ዓረፍተ ነገሩ ወይም  የየምዕራፉ አንቀጽ የተጻፈበት ሃሳቡን  መመርመር

Consider the Context

ክፍል ሦስት


የመጽሐፍቅዱሱን ክፍል ዓረፍተ ነገሩ የተጻፈበትን ከላይና ከታች አስተውሎ ማጥናት ተገቢ ነው ለምን ? ስንል ከዓረፍተ ነገሩ ውጪ ማለት ዓረፍተ ነገሩን በጥቂቱ በዙርያው ያለውን ነገር ሳያዩ በመመልከት ወይንም ጥቅስ ቆንጥሮ በማንሳት የተሳሳተ ትርጉም መያዝና ወደከፋ ስሕተት ውስጥም መግባት ስለ አለ ነው በዘፍጥረት 3 4 እና 5 ላይ እባብም ለሴቲቱ አላት ሞትን አትሞቱም ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ አለ ይህንን ውሸት የተናገረው ሰይጣን ነው እርሱም ያለው ሰው አይሞትም ነው ትክክለኛው ትምህርት ግን ከእግዚአብሔር ጋር የተገናኘ በመሆኑ በዘፍጥረት 2 16 እና 17 ላይ እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና ሲለው እንመለከታለን ታድያ በዘፍጥረት መጽሐፍ ምዕራፍ 3 4 ላይ እባብም ለሴቲቱ አላት ሞትን አትሞቱም ተብሎ በተጻፈው ቃል መሠረት  ሰይጣን ሞትን አትሞቱም እያለ ቢናገርም ጌታ እግዚአብሔር በዚሁ በቃሉ  በዘፍጥረት 2 16 እና 17 ላይ ሞትን ትሞታለህ ሲል ተናግሯል ሕያውነታችንንም ለማረጋገጥ እነዚህን ጥቅሶች ይጽፋል 1 ጢሞቴዎስ 6 14 _ 16 ሮሜ 2 7 1 ቆሮንቶስ 15 53 ለዚህ ነው እንግዲህ የተጻፈበትን አውድ ጠብቀን ዓረፍተ ነገሩ የተጻፈበትን ክፍል ከላይና ከታች እንዲሁም ከጠቅላላው የመጽሐፍቅዱስ ቃል ጋር በማገናኘት ተገቢ የሆነውን ትርጉም ሳናገኝ ወይንም ለጊዜው የሚሆነንን ጥቅስ ቆንጥረን በመነሳት ብቻ የተጻፈበትን ሳንመረምር እንዲሁ በተለምዶ ወይንም መስሎን ይህ ማለት እንዲህና እንዲያ ነው ስንል መናገርም ሆነ መተርጎም የማይገባን አንዳንድ ጊዜ ጠቅላላውን ምዕራፍ በማንበብ ባለቤቱን ማግኘት እንችላለን የማቴዎስ ወንጌል 7 18 እና 19 እንመልከት ስለሚበሉና ስለማይበሉ ምግቦች ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል በግልጽ ይናገራል ዘሌዋውያን ምዕራፍ 11 በሙሉ እንደገናም ዘዳግም ምዕራፍ 14 በሙሉ ልንመለከት እንችላለን ነገር ግን በማርቆስ ወንጌል 7 5 ላይ የምንባቡ ሃሳብ የገለጠው ትክክለኛውን ትርጉም ነው መጽሐፉ የሚጠይቀን ደቀመዛሙርቱ ለምን በሽማግሌዎች ወግ አልሄዱም ? ሆኖ  ነገር ግን እጃቸውን ሳይታጠቡ እንጀራ በሉ የሚል ሃሳብ የያዘ ነው በተመሣሣይ ሃሳብ የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 15 በሙሉ እና ከቁጥር 19  እስከ 20 ያሉትን ሃሳቦች በመመልከት የሃሳቡ ሙሉ መልስ ያለው በእነዚህ ቁጥሮች ውስጥ መሆኑን እናስተውላለን ነገር ግን በዚህ አጋጣሚ ለአንባቢዎቼ  ማስተላለፍ  የምፈልገው እነዚህን የጠቀስኳቸውን ምዕራፍና ቊጥሮች መጽሐፍቅዱሳችሁን ከፍታችሁ በተገቢው መልኩ ካላነበባችኋቸውና ካልተመለከታችኋቸው የትምህርቱ ሃሳብ ምን እንደሆነና ሃሳቡም ማንንና ምንን ለመግለጽ እንደተፈለገ ሊገባችሁ አይችልም ስለዚህ በተቻለ መጠን መጽሐፍቅዱሳችሁን አውጥታችሁ በማንበብ እና በመጠቀም ይህንን ትምህርት እንድታጠኑት ይሁን እላለሁ ተባረኩልኝ ከዚህም ሌላ በሮሜ 9 30 _ 32 ላይ እንግዲህ ምን እንላለን ? ጽድቅን ያልተከተሉት አሕዛብ ጽድቅን አገኙ፥ እርሱ ግን ከእምነት የሆነ ጽድቅ ነው እስራኤል ግን የጽድቅን ሕግ እየተከተሉ ወደ ሕግ አልደረሱም ይህስ ስለ ምንድር ነው ? በሥራ እንጂ በእምነት ጽድቅን ስላልተከተሉ ነው፤ እነሆ፥ በጽዮን የእንቅፋት ድንጋይና የማሰናከያ ዓለት አኖራለሁ በእርሱም የሚያምን አያፍርም ተብሎ እንደ ተጻፈ በእንቅፋት ድንጋይ ተሰናከሉ ይለናል ይህንን የቃሉን እውነታ አስተውለን  ስንመለከተው እስራኤል ወደ ሕግ አይድረሱ እንጂ ሕጉ ግን ንጹሕና ቅዱስ ፍጹምም ነው ስለዚህ በሮሜ 7 12 እና 13 ላይ ስለዚህ ሕጉ ቅዱስ ነው ትእዛዚቱም ቅድስትና ጻድቅት በጎም ናት እንግዲህ በጎ የሆነው ነገር ለእኔ ሞት ሆነብኝን ? አይደለም፥ ነገር ግን ኃጢአት ሆነ፤ ኃጢአትም በትእዛዝ ምክንያት ያለ ልክ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ፥ ኃጢአትም እንዲሆን ይገለጥ ዘንድ በጎ በሆነው ነገር ለእኔ ሞትን ይሠራ ነበር ይለናል እግዚአብሔር የምናነበውን ቃል እንድናስተውለውና እንድንጠቀምበት ይርዳን አሜን
 

 ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment