Saturday, June 6, 2015

ሁሉንም መጻሕፍት በባለቤትነት እንመልከት Look at all the Scriptures on the Subjects ክፍል አራት

ሁሉንም መጻሕፍት በባለቤትነት እንመልከት

Look at all the Scriptures on the Subjects

ክፍል አራት


በአንድ የእግዚአብሔር ቃል ጥናት ላይ ወደ ውሳኔ ከመምጣታችን በፊት ጊዜ ወስደን ጥሩ የሆነ መረዳት እንዲኖረን ከባለቤቱ ጋር የተገናኙ ጥቅሶችን ማየት ያስፈልገናል በሐዋርያት ሥራ 28 23 ላይ ቀንም ቀጥረውለት ብዙ ሆነው ወደ መኖሪያው ወደ እርሱ መጡ፤ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትም እየመሰከረ ስለ ኢየሱስም ከሙሴ ሕግና ከነቢያት ጠቅሶ እያስረዳቸው፥ ከጥዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ይገልጥላቸው ነበር ይለናል ከሐዋርያው ጳውሎስ  የቃሉ አገልግሎትና መረዳት ተምሣሊትነት እንደምናየው ተገቢ ወደሆነ መረዳት ለመምጣት ከባለቤቱ ጋር የተገናኙ ጽሑፎችን በእርግጠኝነት ወደ ሂሳብ ማምጣቱ ነው ይህ ታድያ መንፈሳዊ ነገሮችን ከመንፈሳዊ ነገር ጋር የማነጻጸር መመርያ ነው በ1ኛ ቆሮንቶስ 2 13 ላይ መንፈሳዊውን ነገር ከመንፈሳዊው ነገር ጋር አስተያይተን መንፈስ በሚያስተምረን ቃል ይህን ደግሞ እንናገራለን እንጂ የሰው ጥበብ በሚያስተምረን ቃል አይደለም ይለናል ጳውሎስ ያደረገው ይህንን ነው መንፈሳዊውን ነገር ከመንፈሳዊው ነገር ጋር አስተያየ ማለት ስለ እግዚአብሔር መንግሥትም እየመሰከረ ስለ ኢየሱስ ሊናገር በወደደ ጊዜ ከሙሴ ሕግና ከነቢያት ጠቅሶ እያስረዳቸው፥ ከጥዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ መግለጡ በእርግጥም መንፈሳዊውን ነገር ከመንፈሳዊው ነገር ጋር ማስተያየቱን ያመላክታል ታድያ ሁሉንም መጻሕፍት በባለቤትነት ስንመለከት እኛም እንደ ጳውሎስ ሌሎችን እንደዚህ በምልአትና በሰፋ መልኩ ማስረዳት እንጀምራለን ሌላው ሁሉንም መጻሕፍት በባለቤትነት የምንመለከትበት ምክንያት ቅዱሳት መጻሕፍት በእግዚአብሔር መንፈስ የተጻፉ ናቸው ከዚህም ሌላ እነዚህ መጻሕፍት በሰው ፈቃድ የመጡ አይደሉም እና እርስ በእርሳቸው የሚጋጩ አይሆኑም ደግሞም አይጋጩም 2 ጴጥሮስ 1 20 እና 21 የናዝሬቱ ኢየሱስም ጳውሎስ የተጠቀመበትን መንገድ ተጠቅሞ ስለነበር ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጎመላቸው ይለናል የሉቃስ ወንጌል 24 27 ጌታችን ታድያ ይህን ማድረጉ ሁሉንም መጻሕፍት በባለቤትነት መመልከቱን የሚያሳየን ነው እንደገናም በዚሁ በሉቃስ ወንጌል 24 44 _ 48 ላይ እርሱም፦ ከእናንተ ጋር ሳለሁ በሙሴ ሕግና በነቢያት በመዝሙራትም ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይገባል ብዬ የነገርኋችሁ ቃሌ ይህ ነው አላቸው በዚያን ጊዜም መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው እንዲህም አላቸው፦ ክርስቶስ መከራ ይቀበላል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሣል በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል ተብሎ እንዲሁ ተጽፎአል እናንተም ለዚህ ምስክሮች ናችሁ ይላቸዋል ይልቁንም ካኖናይዝድ ሆነው ማለት ቅዱሳት መጻሕፍት ተብለውና በአንድ ላይ ተቆጥረው በአንድ ጥራዝ ውስጥ የገቡ ቢሆኑም እንኳ የተጻፉበት ክፍለ ዘመን ግን ልዩ ልዩ ነው ነገር ግን እጅግ የሚደንቀው ነገር በእግዚአብሔር መንፈስ የተጻፉ ናቸውና እርስ በእርሳቸው ካለመጋጨታቸው የተነሳ አንዱ ለሌላው የማመሳከርያ መንገድና ማቆራኛ ሆነው የቀረቡ ናቸው ለዚህ ነው እንግዲህ ጌታችን ኢየሱስም ሆነ ጳውሎስ ሁሉንም መጻሕፍት በባለቤትነት የተመለከቷቸው በመሆኑም  ለተነሱበት ሃሳብ እንደ ተጨማሪ ማብራርያ ሊጠቀሙባቸው መጻሕፍቱን ሲያጣቅሱና ሲተረጉሙዋቸው የምንመለከተው  ከዚህ የተነሳ ነው ታድያ እነዚህ መጻሕፍት በመንፈስቅዱስ አማካኝነት እንዲጻፉና እንዲደረሱ ላደረገ ለእግዚአብሔር መንፈስቅዱስ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን ከምንል በቀር የምንለው የለም ለአንድ መሠረታዊ ትምህርት አስረጂ እንዲሆኑ ሁሉም መጻሕፍት በባለቤትነት ቀርበው በሚጠቀሱ ጊዜ ሰዎች ዛሬም እንደከበረው ቴዎፍሎስ እርግጡን ያውቃሉ የሉቃስ ወንጌል 1 1 _ 4 ጢሞቴዎስ እንደ ተባለም ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡአቸው የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን ሁሉ ያውቃሉ ከማን እንደተማሩም አውቀው ደግሞ በተማሩበትና በተረዱበት ነገርም ጸንተው ይኖራሉ እንግዲህ ሁሉንም መጻሕፍት በባለቤትነት መመልከት ለተነሳንበትም መሠረታዊ የእግዚአብሔር ቃል ሃሳብ እነዚህኑ መጻሕፍት በአስረጂነት ማቅረብ ጥቅሙ ያለው እዚህ ላይ ነው እና ቅዱሳን የእግዚአብሔር ወገኖች ይህንን የእግዚአብሔር ቃል እውነት እንወቅ አውቀንም ደግሞ እንጠቀምበት እላችኋለሁ ከዚህም ሌላ የመጽሐፍቅዱስ መንፈሳዊ ሥነፍጥረት ወይንም መንፈሳዊ ተፈጥሮ የተገለጸው በኤፌሶን ፲፯ ላይ ነው ቃሉም እንዲህ ይለናል የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው
The Spiritual nature of the bible is described in Ephesians 6 : 17 as << The sword of Spirit, which is the word of God >>

Thank u God bless u all People of God


The servant of God Yonas Asfaw 

No comments:

Post a Comment