Sunday, November 29, 2015

መዝገብነ ዘኢይረክቦ ሠራቂ ሌባ የማያገኘው መዝገባችን ክፍል ስድስት


The Rich Man and Lazarus


መዝገብነ ዘኢይረክቦ ሠራቂ


ሌባ የማያገኘው መዝገባችን




ክፍል ስድስት




መዝገብነ ዘኢይረክቦ ሰራቂ ወኢያማስኖ ፃፄ ወቊንቊኔ ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ

ትርጉም ሌባ የማያገኘው ብል  ነቀዝ የማያበላሸው መዝገባችን ይህ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው


( ምንጭ መጽሐፈ ሰዓታት )


በክፍል ስድስት ትምህርታችን ላይ የምንመለከተው ስለ ሕይወት መጽሐፍ ነው በዮሐንስ ራዕይ 20 12 _ 15 ላይ እንዲህ የሚል ቃል ተጽፎልናል ሙታንንም ታናናሾችንና ታላላቆችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፥ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት ተጽፎ እንደ ነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ተከፈሉ ባሕርም በእርሱ ውስጥ ያሉትን ሙታን ሰጠ፥ ሞትና ሲኦልም በእነርሱ ዘንድ ያሉትን ሙታን ሰጡ፥ እያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን ተከፈለ ሞትና ሲኦልም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣሉ ይህም የእሳት ባሕር ሁለተኛው ሞት ነው በሕይወትም መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘው ማንኛውም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣለ ይለናል ታድያ ይህ የሕይወት መጽሐፍ የሚከፈተው በነጩ ዙፋን ፍርድ ነው ምክንያቱም መጽሐፍቅዱሳችን አሁንም ታላቅና ነጭ ዙፋንን በእርሱም ላይ የተቀመጠውን አየሁ፥ ምድርና ሰማይም ከፊቱ ሸሹ ስፍራም አልተገኘላቸውም ይለናል ራዕይ 20 11 ይህ ታላቅና ነጭ ዙፋን ደግሞ የበጉ ዙፋን ነው መጽሐፍ አሁንም በአደባባይዋም መካከል ከእግዚአብሔርና ከበጉ ዙፋን የሚወጣውን እንደ ብርሌ የሚያንጸባርቀውን የሕይወትን ውኃ ወንዝ አሳየኝ ይለናል ራዕይ 22 እንደገናም በራዕይ 22 3 ላይ ከእንግዲህም ወዲህ መርገም ከቶ አይሆንም የእግዚአብሔርና የበጉም ዙፋን በእርስዋ ውስጥ ይሆናል፥ ባሪያዎቹም ያመልኩታል፥ ፊቱንም ያያሉ፥ ይላል በራዕይ 21 5 ላይ ደግሞ በዙፋንም የተቀመጠው፦ እነሆ፥ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ አለ ለእኔም፦ እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸውና ጻፍ አለኝ ይለናል ስለዚህ በበጉ ዙፋን እና በዚሁ የነጩ ዙፋን ፍርድ የመጨረሻ የፍርድ ውሳኔ ይሰጣል መጽሐፍ ይከፈታል  እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት ተጽፎ እንደ ነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ተከፈሉ ባሕርም በእርሱ ውስጥ ያሉትን ሙታን ሰጠ፥ ሞትና ሲኦልም በእነርሱ ዘንድ ያሉትን ሙታን ሰጡ፥ እያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን ተከፈለ ሞትና ሲኦልም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣሉ እያለ ይናገረናል ወገኖቼ እንደ ሥራ የሚከፍል እግዚአብሔር ብቻ ነው ለዚህም ነው በ1ኛ ጴጥሮስ 1 17 ላይ ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ ብትጠሩ በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ ያለን ይህን ማለቱ ግን ጽድቅ በሥራ ይገኛል እና ለጽድቅና ለመዳን መልካምን ሥራ ሥሩ እያለን እንዳልሆነ ለሁላችንም ግልጽ ሊሆን ይገባል መጽሐፉ ሙታንም በመጻሕፍት ተጽፎ እንደ ነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ተከፈሉ ቢለንም አለፍ ብለን ስናነበው በሕይወትም መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘው ማንኛውም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣለ ይለናል ስለዚህ በእሳት ባሕር ውስጥ ተጥለን በሁለተኛው ሞት እንዳንጎዳ በመጀመርያ በሕይወት መጽሐፍ መጻፍ ለሁላችንም የግድ ይሆናል በህይወት መጽሐፍ ለመጻፍ ደግሞ የኢየሱስን ሞትና ትንሣኤ ለጽድቄ አምናለሁ ሲሉ በዚህ ምድር በሕይወት እያሉ አሁኑኑ አምኖ መቀበል ነው በርሜ 4 22 _ 25 ላይ ስለዚህ ደግሞ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት ነገር ግን፦ ተቈጠረለት የሚለው ቃል ስለ እርሱ ብቻ የተጻፈ አይደለም፥ ስለ እኛም ነው እንጂ ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለ ማጽደቅም የተነሣውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው ለምናምን ለእኛ ይቈጠርልን ዘንድ አለው ይለናልና ከዚህ ውጪ ግን ለጽድቃችን እግዚአብሔር የሚቆጥረው እኛም የምናስቆጥረውና የሚቆጠርልን ጽድቅ የለም መጽሐፉ አሁንም ሙታንም በመጻሕፍት ተጽፎ እንደ ነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ተከፈሉ ቢለንም በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ከተገኘው ጽድቅና እግዚአብሔርም የሰዎችን ልጆች ለማጽደቅ ሲል ከቆጠረው ከዚሁ ጽድቅ ጋር አገናኝቶ የተናገረው ቃል አይደለም ሙታን እግዚአብሔር ለጽድቃችን በቆጠረው በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ያላመኑ በመሆናቸው በመጽሐፉ ተጽፎ እንደነበረው እንደ ሥራቸው መጠን ይከፈላሉ ማለትን የሚያመለክት ነው እንጂ ሥራ ያጸድቃል  ሊለን አይደለም በመሆኑም ለመጽድቅ በሕይወት መጽሐፍ  መጻፍ ዋናና የመጀመርያ ነገራችን ሊሆን ይገባል ደግሞም በሕይወት መጽሐፍ መጻፍ እንዳለ ሁሉ ተጽፎ አለመገኘትም አለና ከወዲሁ ዛሬ በሕይወተ ሥጋ እያለን በኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ በማመኔ ምንያት ስሜ በሕይወት መጽሐፍ ተጽፎአል ወይስ አልተጻፈም ሲሉ እራስን መጠየቁ የሁላችንም ድርሻ ሊሆን ይገባል ካልተጻፈ ደግሞ ቶሎ  ይህ ስማችን እንዲጻፍ አሁኑኑ በዚህ ጌታ ሞትና ትንሣኤ ማመን ከእኛ ይጠበቃል እንዴት ነው የምናምነው ሲባል ኢየሱስ ሆይ በእንጨት ላይ መርገሜን ተሸክመህ እና ስለእኔም መርገም ሆነህ የሞትክልኝ ስለበደሌ ነው ከሞት የተነሳህልኝም እኔን ስለማጽደቅ ነው ስለዚህ ዛሬ ፈቅጄ ሕይወቴን ለአንተ እሰጣለሁ እቀበልሃለሁ ብለን  ይህን ጌታ ወደ ሕይወታችን ስናስገባው የእግዚአብሔር ልጆች እንሆናለን የኃጢአትንም ይቅርታ እናገኛለን ስማችንም በሕይወት መጽሐፍ ይጻፋል ገላትያ 3 ፥ 13 እና 14  ዮሐንስ ወንጌል 1 12 1 ዮሐንስ መልዕክት 1 7 _ 9 ከዚያ ውጪ ግን የሚሆን ምንም ነገር ስለሌለ ኢየሱስን ያልተቀበለ ሁሉ ሙታን ነውና ለሙታን የተገባ በመጽሐፍ የተጻፈ ብያኔ ስላለ በተጻፈው መሠረት እንደ ሥራችን ይከፈለናል ስለዚህ ከዚህ ሁሉ ፍርድ ለማምለጥ እንደገናም በዚህ የሕይወት መጽሐፍ ተጽፎ ለመገኘት ዛሬውኑ በኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ ማመን ይሁንልን ይህንኑ ትምህርት አስመልክቶ በክፍል ሁለት ትምህርቴም ላይ ልዩ ልዩ መዛግብት እንደነበሩና ተጽፈው የተቆጠሩ ሰዎች እንደነበሩ በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ዮሴፍ ለመጻፍ ከእጮኛው ከማርያም ጋር እንደሄደ በክፍሉ ሃሳብ ተመልክተን ተማምረንበታል ይሁንና ታድያ በዚያን ዘመን ብቻ ሳይሆን ዛሬም ሰዎች ተገቢ በሆኑ የመቆጣጠርያ መዝገቦችና ሰኖዶች ስማቸውን ከማስመዝገባቸውም ሌላ በልዩ ልዩ ዝናቸው ችሎታቸውና አሸናፊነታቸው በታወቁ ሥፍራዎች ስመ ጥር ሆነው ስማቸውን በከበሩ መዛግብቶችም ላይ ሊያሰፍሩ ይችላሉ ስማቸውንም አስፍረው በትልልቅ ሚዲያዎችና አደባባዮች ይኸው ስማቸው ገኖ የወጣና የሚጠራ እየተጠራም ያለ ብዙዎች ናቸው ነገር ግን ይህ ሁሉ የሚሆነው እነዚህ ሰዎች ግፋ ቢል የሚጠሩት ለተወሰነ ጊዜ አልያም እስኪሞቱ ድረስ ነው ከዚያ ታሪክም ሆነ ሰው ይረሳቸዋል ከዚያ በኋላ ቢነሱም እንኳ ለአንድ ጊዜና ለትውስታ ያክል ነው ከዚያ በኋላ  እንዲህ ዓይነት ሰው ነበረ ወይም ነበረች አይ በቃ ምን ያደርጋል ሞቷል ወይም ሞታለች ተብሎ ታሪክ ሁሉ ይዘጋል በመሆኑም ሽልማቱም ሆነ ዝናውና ስመ ጥር መሆኑ ከዚያ ሰው ጋር ተከትሎ የሚሄድ አይደለምና እዚሁ በምድር ላይ  ቀሪ ነው በኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ ያመነ ግን የተጻፈበት ታዋቂው በምድር ላይ ያለ የሰው መዝገብ ሳይሆን የእግዚአብሔር የሕይወት መጽሐፍ በመሆኑ ታሪኩ ለአንዴም ለዘላለም የማይረሳ ሆኖ ያን ሰው ከእግዚአብሔር ጋር  ለሁልጊዜ ያኖረዋል በመሆኑም በምድር ላይ ስመ ጥር ሆነን በሰው መዝገብ መጻፉ ከሆነና ከተሳካ እሰየው የሚያስብል ቢሆንም የጊዜውና በምድርም ላይ የሚቀር ነው ይህ በእግዚአብሔር የሕይወት መጽሐፍ የመጻፉ ጉዳይ ግን የዘላለምና አስተማማኝ ነው ያኔ እግዚአብሔርም እንዲህ ተጽፈን ሲያገኘን ስማችን በዚሁ የሕይወት መጽሐፍ የተጻፈ ነውና  አላውቃችሁም አይለንም የማቴዎስ ወንጌል 25 31 _ 46 የተጻፈውን ይመልከቱ ጌታ እግዚአብሔር በምናነበውም ሆነ በምንሰማው ቃል ይጠቀመን ይባርከንም

ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን

የ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry

አገልጋይና ባለራዕይ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ




No comments:

Post a Comment