Wednesday, September 23, 2015

ንስሐ ሁሉም ሰው በእርግጠኝነት መግባት አለበት All must repent ክፍል አምስት (ሀ)

ንስሐ ሁሉም ሰው በእርግጠኝነት መግባት አለበት


All must repent  



ክፍል አምስት ()

ንስሐ እግዚአብሔር ከሰው ልጆች ሁሉ የሚፈልገው የእግዚአብሔር መሠረታዊ ዓላማ ያለበት ጉዳይ ነው ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር ሰዎች ሁሉ የበደለኝነት ስሜት ተሰምቶአቸው ሳለ እጃቸውን አጣጥፈው ዝም ብለው እንዲቀመጡ አያዝም በኃጢአታቸው ተናዘው በክርስቶስ ደም ታጥበው እንዲነጹ ይፈልጋል ለዚህም ነው ኃጢአቱን የሚሰውር አይለማም፤ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል ያለው ምሣሌ 28 13 እንደገናም በ1ኛ ዮሐንስ 1 8 _ 10 ላይ ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው ኃጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም ሲል የነገረን እኛም እግዚአብሔር የወደደውን ነገር ወደን ለአንዴ ብቻ ሳይሆን ለሁል ጊዜም ቢሆን የንስሐ ሕይወት ልንይዝና ሊኖረንም ይገባል ታድያ  በሉቃስ ወንጌል 15 7 እና 10 ላይም እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል በመሆኑም ንስሐ በእግዚአብሔርም ሆነ በእግዚአብሔር መላዕክቱ ፊት እጅግ የተወደደ ነገር እንደሆነ መጽሐፉ በግልጽነት ይነግረናል ንስሐ ያጠፋ ሰው ብቻ ወደ እግዚአብሔር ቀርቦ የሚናዘዝበትና ይቅርታም የሚጠይቅበት ሕይወት አይደለም ንስሐ ሰው ባይበድልም እራሱን ማለትም ሕይወቱን ለእግዚአብሔር የሚያስመረምርበት  ነው ለዚህም ነው መዝሙረኛው ዳዊት  በመዝሙር (139 ) 1 _ 5 ላይ አቤቱ፥ መረመርኸኝ፥ አወቅኸኝም አንተ መቀመጤንና መነሣቴን አወቕህ፤ አሳቤን ሁሉ ከሩቅ አስተዋልህ ፍለጋዬንና ዕረፍቴን አንተ መረመርህ፤ መንገዶቼን ሁሉ  ቀድመህ አወቕህ የዓመፃ ቃል በአንደበቴ እንደሌለ አቤቱ፥ አንተ እነሆ የቀድሞውንና የኋላውን አወቕህ፤ አንተ ፈጠርኸኝ፥ እጅህንም በላዬ አደረግህ  በማለት የተናገረው የዓመፃ ቃል በአንደበቱ እንደሌለ ያወቀው ራሱ ራሱን መርምሮ ሳይሆን በእግዚአብሔር ተመርምሮ ነው እኛ እኛን ከምናውቀው በላይ እግዚአብሔር እኛን በሚገባ ያውቀናል ስለዚህ ለራሳችን እራሳችን መልስ ከምንሰጥ ይልቅ ለሚያውቀን ለእግዚአብሔር በንስሐ እራስን መስጠት የተሻለ ነገር ነው ለዚህም ነው ዳዊት  በመዝሙሩ አሁንም ስሕተትን ማን ያስተውላታል፧ ከተሰወረ ኃጢአት አንጻኝ ሲል የተናዘዘው መዝሙር 19 12 መዝሙረኛው ዳዊት አቤቱ መረመርኸኝ አወቅኸኝም እና የመሣሠሉትን ያለ ብቻ ሳይሆን አቤቱ መርምረኝ ልቤንም እወቅ ፍተነኝ መንገዴንም እወቅ በደልንም በእኔ ውስጥ ብታገኝ እይ የዘላለምንም መንገድ መንገድ ምራኝ አለ መዝሙር ( 139 ) 9 ዳዊት አንዴ መረመርኸኝ አወቅኸኝም ብሎ ያቆመ ብቻ አይደለም የየዕለት ሕይወቱን ለእግዚአብሔር እየሰጠ በዘላለም መንገድ በእግዚአብሔር ለመመራት  አቤቱ መርምረኝ ልቤንም እወቅ ፍተነኝ መንገዴንም እወቅ በደልንም በእኔ ውስጥ ብታገኝ እይ የዘላለምንም መንገድ መንገድ ምራኝ ሲል ራሱን ለእግዚአብሔር የሰጠ ነው ኃጢአት ከእኛ ሊሠወር ቢችልም ከእግዚአብሔር ግን አይሠወርም ስለዚህም ዳዊት ይህንን ሁኔታ በሚገባ ጠንቅቆ የተረዳ በመሆኑ በራሱ ጉዳይ ላይ ኃጢአት የለብኝም ወይም እኔ እኮ ንጹሕ ነኝ ሲል ያንገራገረ ወይንም ለራሱ ፍርድ የሰጠ አልሆነም ያለው ነገር አንድና አንድ ነው ስሕተትን ማን ያስተውላታል፧ ከተሰወረ ኃጢአት አንጻኝ አለ መዝሙረኛው ዳዊት አሁንም ኃጢአት ከእርሱ ጋር ቢቆይ የሚያመጣበትን መዘዝ የሚያስከፍለውንም ዋጋ በትክክል ጠንቅቆ ያወቀም በመሆኑ ኃጢአቴን ለአንተ አስታወቅሁ፥ በደሌንም አልሸፈንሁም፤ ለእግዚአብሔር መተላለፌን እነግራለሁ አልሁ፤ አንተም የልቤን ኃጢአት ተውህልኝ በማለት በመናዘዝ ውስጥ የእግዚአብሔር የልብን ኃጢአት ሳይቀር የመተውን ነገር ይፋ አደረገ መዝሙር 32 5 እግዚአብሔር አምላካችን እንደዚህ ዓይነት መሐሪ አምላክ ነው የልብን ኃጢአት ሳይቀር ይቅር የሚልና የሚተው ክብር ለስሙ ይሁንለት የልብ ኃጢአት በአጋጣሚ የሚመጣ ድንገተኛም በሆነ የስሕተት ሁኔታ የሚከሰት ብቻ ሳይሆን ታስቦበትና ታቅዶ ሆን ተብሎም በዓላማ ጭምር ሳይቀር የሚደረግ ነው የሚገርመውና የሚደንቀው ነገር ግን ጌታ እግዚአብሔር ይህንን ኃጢአት ሁሉ ይቅር ይላል አሁንም ኃጢአትን መናዘዝ ያጠፉ ወይንም የበደሉ ሰዎች ተግባር ራሳቸውንም ለእግዚአብሔር እንደ ዳዊት ማስመርመር የሚፈልጉ ሰዎች ከዚህም ሌላ ስሕተትንና የተሰወረ ኃጢአትን ያላስተዋሉ ሰዎች ኑዛዜና የንስሐ ሕይወት ብቻ አይደለም በኢዮብ መጽሐፍ ምዕራፍ  1 5 የግብዣውም ቀኖች ባለፉ ጊዜ ኢዮብ፦ ምናልባት ልጆቼ በድለው፥ እግዚአብሔርንም በልባቸው ሰድበው ይሆናል ብሎ ይልክና ይቀድሳቸው ነበር፤ ኢዮብም ማልዶ ተነሣ፥ እንደ ቍጥራቸውም ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ እንዲሁ ኢዮብ ሁልጊዜ ያደርግ ነበር  ይለናልና የገባቸው ሰዎች ከኃጢአት የራቀ ነጻ ሕይወት እንዳላቸው የሚሰማቸው እንኳ ቢሆኑ ከራሳቸው ባሻገር ላለ የቤተሰበ ሕይወትም ይሁን የማኅበረ ሰብ የቤተክርስቲያንና የሀገር ጉዳይ ሳይቀር ግድ ብሎአቸው ስለብዙዎች ቅድስና እንደ ኢዮብ በእግዚአብሔር ፊት  ይወድቃሉ ይህንንም አሁንም እንደ ኢዮብ  ለሁልጊዜ የሚያደርጉ ይሆናሉ  ይህ ታድያ ከፍተኛ የሆነ የሕይወት ጤናማነት ነው ስለሆነም ንስሐ እኔ ደህና ነኝ ስንል ለሌሎች የምንተወውና ሌሎችም እንዲያደርጉት የምንወተውተው ወይም ለሌሎች በአደራ የምንሰጠው ሳይሆን እኛው እራሳችን ከሌሎች ጋር ሆነን አብረንና ተባብረን በአንድነት የምንገባበት የእግዚአብሔርንም ፊት የምንፈልግበት ሕይወት ነው እነ ነህምያ እነ እዝራ እነ ዳንኤል እራሳቸውን ከሕዝብ ሳይለዩ ወይም ሳያወጡ አብረው ንስሐ የገቡት በእንዲህ ዓይነት መንገድ ነው ዕዝራ 9 13 _ 15 ነህምያ 1 1 _ 7 ትንቢተ ዳንኤል 9 4 እና 5 የተወደዳችሁ ወገኖች የንስሐ ትምህርት በዚህ የተቋጨ አይደለም ቀጣይነትና ተከታታይነት ያለው ስለሆነ ተከታዩን ክፍል በሚቀጥለው እናቀርባለን እስከዚያው ተባረኩልኝ በማለት የምሰናበታችሁ

Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ
                                                                                          
ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ



No comments:

Post a Comment