Tuesday, September 29, 2015

ሁሉም ሰው በእርግጠኝነት ንስሐ መግባት አለበት ክፍል አምስት (ሐ) All must repent

ሁሉም ሰው በእርግጠኝነት ንስሐ መግባት አለበት


ክፍል አምስት ()



All must repent



የእግዚአብሔርን መሠረታዊ እውነት ከተማረ እያንዳንዱ ሰው ንስሐ መግባት አለበት ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል 2 ጴጥሮስ 3 9 There are no exceptions God wants everyone to repent  ታድያ ሰዎች ይህንን መረዳት አንድ ጊዜ እንዴት መቀበል ይችላሉ ? ለእግዚአብሔርስ እራሳቸውን ማስገዛትና ሕይወታቸውን መለወጥ እንዴት ይችላሉ ? ጳውሎስ ሐዋርያው ይህንን ገልጾታል እንግዲህ ያላመኑበትን እንዴት አድርገው ይጠሩታል ? ባልሰሙት እንዴት ያምናሉ ? ያለ ሰባኪስ እንዴት ይሰማሉ ? መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው ተብሎ እንደ ተጻፈ ካልተላኩ እንዴት ይሰብካሉ ? ሮሜ 10 14 እና 15 ጳውሎስ እንደተናገረው ከእግዚአብሔር በትክክል የተላከ በእርግጠኝነት መናገር አለበት የእርሱ ታማኝ አገልጋይ ለእግዚአብሔር ቃል ታማኝ ሆኖ ሕጉን ካላስተማረ ለእግዚአብሔር መታዘዝ ምን እንደሆነ ካልተናገረ ንስሐ የሚገባው ሰው ኃጢአትን አያቆምም የእግዚአብሔርንም ሕግ ይጥሳል ወይንም ይተላለፋል ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ ዓመጽን ደግሞ ያደርጋል ኃጢአትም ዓመጽ ነው 1 ዮሐንስ 3 4 ከዚሁ ጋር በማያያዝ በመጠራትና በመመረጥ መካከል ያለውን ልዩነት በጥቂቱም ቢሆን እንመለከታለንና ተከታተሉ እግዚአብሔር በመጀመርያ የመረጠን ለደኅንነት ነው ለዛ ጥሪ በእርግጠኝነት ምላሽ ስንሰጥ ግብዣ ለደኅንነት ይመርጠናል በ2ኛ ተሰሎንቄ 2 13 እና 14 ላይ እኛ ግን፥ በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ልናመሰግን ግድ አለብን፥ እግዚአብሔር በመንፈስ መቀደስ እውነትንም በማመን ለመዳን እንደ በኵራት መርጦአችኋልና ለዚህም የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር ለማግኘት በወንጌላችን ጠራችሁ ይለናል ስለዚህ የተመረጡ ማለት ደኅንነትን ለሚያስገኘው ለእግዚአብሔር ወንጌል በእርግጠኝነት ምላሽ የሰጡ ናቸው ወገኖቼ እኛንም እግዚአብሔር ለሚፈልገን የንስሐ ሕይወትም ሆነ የመጠራትና የመመረጥ ሕይወት እንደ ቃሉ የሆነ አፋጣኝ ምላሽ የምንሰጥ ያድርገን ተባረኩልኝ ለዘላለም


Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ
                                                                                          
ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ





No comments:

Post a Comment