Wednesday, September 16, 2015

መጠራትና መመረጥ Called and Chosen ክፍል አራት

 መጠራትና መመረጥ




Called and Chosen  


ክፍል አራት



የመጠራትንና የመመረጥን ሃሳብ በእርግጠኝነት ያስገኘው ኢየሱስ ራሱ ነው ለደቀመዛሙርቱም ሲነግራቸው የተጠሩ ብዙዎች የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና ነበር ያላቸው የማቴዎስ ወንጌል 22  14 መጠራትና መመረጥ የተባሉት ሁለቱም ሃሳቦች መጽሐፍቅዱሳዊ ናቸው በእንግሊዘኛው Many are called but few are chosen ይለናል ወደ አማርኛው ስንተረጉመው  የተጠሩ ብዙዎች የተመረጡ ግን ጥቂቶች ማለትን የሚያመለክተን ነው የተጠሩ ብዙዎች የተመረጡ ግን ጥቂቶች  ሲል ምን ማለት ነው ? ስንል  የእግዚአብሔር ጥብቅ የሆነ ፍላጎቱ ለሰው ልጆች ሁሉ ደኅንነት እና የዘላለምን ሕይወት መስጠት ነው በዮሐንስ ወንጌል 3  17 ላይ ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና ይለናል በዚህ በተጻፈው ቃል መሠረት ቊልፍ ቃሉ ይህንን ቢሰጠንም ነገር  ግን ሁሉም የዳነ አይደለም በዚህ ሰዓትና በዚህ ጊዜ በሮሜ 11  7-  ላይ  እንግዲህ ምንድር ነው ? እስራኤል የሚፈልጉትን አላገኙትም፤ የተመረጡት ግን አገኙት ሌሎቹም ደነዘዙ፤ እንዲሁም፦ ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስን እስከ ዛሬ ድረስ ሰጣቸው ተብሎ ተጽፎአል ይለናል   በሮ  11  25 እና 26 ላይ ደግሞ ወንድሞች ሆይ፥ ልባሞች የሆናችሁ እንዳይመስላችሁ ይህን ምሥጢር ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፤ የአሕዛብ ሙላት እስኪገባ ድረስ ድንዛዜ በእስራኤል በአንዳንድ በኩል ሆነባቸው እንደዚሁም እስራኤል ሁሉ ይድናል፤ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፦ መድኃኒት ከጽዮን ይወጣል ከያዕቆብም ኃጢአተኛነትን ያስወግዳል ይለናል ይሁን እንጂ ታድያ በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው ሃሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነውና  ይህንን ሃሳቡን እግዚአብሔር በየትኛውም መንገድ ቢሆን  ይፈጽማል ኤፌሶን 1  7 እግዚአብሔር ሰውን የመረጠው የዘላለምን ሕይወት እንዲቀበል እውነትን የተማረና የተቀበለ እንደገናም በእምነት ንስሐ ገብቶ ሲጠመቅ ብቻ ነው ነገር ግን እንዴት እውነትን ከስሕተት ለይቶ ማወቅ ይችላል ? ስንል በዮሐንስ ወንጌል 17  17 ላይ በእውነትህ ቀድሳቸው ቃልህ እውነት ነው ይለናል በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ሁሉም በእርግጠኝነት የእግዚአብሔር ቃል የእውነት ምንጭ መሆኑን ማወቅና መቀበል አለበት መጽሐፍቅዱሳችን አሁንም እንዲህ ይለናል እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው ይለናል 1 ጢሞቴዎስ 2  1- 4 በመሆኑም አምላካችን የሚመኘው ከልብም የሚፈልገው ሰው ሁሉ ወደ እውነተኛው የእግዚአብሔር እውቀት እንዲመጣና እንዲድን ነው








ጌታ እግዚአብሔር በዚህ ቃል ይጥቀመን ይርዳን ይገናኘን አሜን

Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ


ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ








No comments:

Post a Comment