Thursday, September 24, 2015

ሁሉም ሰው በእርግጠኝነት ንስሐ መግባት አለበት All must repent ክፍል አምስት ( ለ )

ሁሉም ሰው በእርግጠኝነት ንስሐ መግባት አለበት



All must repent



ክፍል አምስት ( )



እግዚአብሔር ንስሐ በሚገባ ሕይወት እንደሚደሰት ሁሉ ንስሐ በማይገባ ሕይወት ደግሞ ያዝናል በማርቆስ ወንጌል 8 22 _ 26 ላይ ወደ ቤተ ሳይዳም መጡ ዕውርም አመጡለት፥ እንዲዳስሰውም ለመኑት ዕውሩንም እጁን ይዞ ከመንደር ውጭ አወጣው፥ በዓይኑም ተፍቶበት እጁንም ጭኖበት አንዳች ታያለህን ? ብሎ ጠየቀው አሻቅቦም፦ ሰዎች እንደ ዛፍ ሲመላለሱ አያለሁ አለ ከዚህም በኋላ ደግሞ እጁን በዓይኑ ላይ ጫነበት አጥርቶም አየና ዳነም ከሩቅም ሳይቀር ሁሉን ተመለከተ ወደ ቤቱም ሰደደውና፦ ወደ መንደሩ አትግባ በመንደሩም ለማንም አንዳች አትናገር አለው ይለናል የተወደዳችሁ ወገኖች እንግዲህ ይህንን ዓይነ ሥውር ከመንደሩ ውጪ አውጥቶ ለምን ዓይኑን ሊፈውሰው ቻለ ? እንደገናም ጌታችን ኢየሱስ አጥርቶ እንዲያይ ካደረገው በኋላ ወደ መንደሩ አትግባ በመንደሩም ለማንም አንዳች አትናገር ለምን ሊለው ወደደ ? መንደሩ ጋር ያለው ችግር ምንድርነው ? ማለት የቤተ ሳይዳው ችግር ምንድነው ? ስንል በሉቃስ ወንጌል 10 13 ላይ ወዮልሽ ኮራዚን፥ ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ፤ በእናንተ የተደረገው ተአምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርጎ ቢሆን፥ ማቅ ለብሰው በአመድም ተቀምጠው ከብዙ ጊዜ በፊት ንስሐ በገቡ ነበር የሚል ቃል ተጽፎ እናገኛለን ከዚህ የተነሳ ቤተ ሳይዳ ወደ እግዚአብሔር ምሕረት እንድትመጣ በተደረገው ተአምራት የሰጠችው ምላሽ አልነበረም ማለትም የንስሐ ምላሽ መስጠት ሲገባት ለእግዚአብሔር ተአምራት ቦታ ባለመስጠቷ ምክንያት ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ በእናንተ የተደረገው ተአምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርጎ ቢሆን፥ ማቅ ለብሰው በአመድም ተቀምጠው ከብዙ ጊዜ በፊት ንስሐ በገቡ ነበር የሚል ቃል ተጽፎላታል ከእርሷ ይልቅ ይህ ተአምራት በጢሮስና በሲዶና ቢደረግ ማቅ ለብሰው በአመድም ተቀምጠው ከብዙ ጊዜ በፊት ንስሐ በገቡ ነበር ሲል ጌታ ተናገረ ስለዚህ ቤተ ሳይዳ ጌታ ለሚያደርጋቸው ተአምራቶች ምንም ዓይነት የንስሐ ምላሽ የማትሰጥና መስጠትም የማትፈልግ በመሆንዋ ኢየሱስ ዕውሩን እጁን ይዞ ከመንደር ውጪ አወጣው ከፈወሰውም በኋላ ወደ መንደሩ አትግባ በመንደሩም ለማንም አንዳች አትናገር አለው በማለት የእግዚአብሔር ቃል ይነግረናል ንስሐ ለመንፈሳዊ ጉብኝት ፣ ለመንፈሳዊ ባርኮትና ለመንፈሳዊ ዕድገትም ጭምር ዓይነተኛ ምክንያት ነው ንስሐ በሚገባ ሰው ጌታችን በብዙ ይደሰታልና እነዚህን ነገሮች ሁሉ ያለ አንዳች መከልከል ያደርጋል እንግዲህ የጥንቷን ቤተ ሳይዳ በዚህ መልኩ አንስተን የምንተው ብቻ አንሆንም የዛሬዋም ቤተክርስቲያንና የቅዱሳን ኅብረት ቤተ ሳይዳ እየሆነች ነው ከዚህ የተነሳ ጌታም ተአምራቱንና ጉብኝቱን በቅዱሳን መካከል ለማድረግ ተቸግሮ ያለበት ጊዜ ላይ ደርሰናል የእግዚአብሔር ነገር ኖርማል እየሆነብን እና እየቀለለብን ብዙ ነገር እያለፈን ነው ከዚህ የተነሳ በጢሮስና በሲዶና ብቻ ሳይሆን ዛሬም በእኛ የተደረገው ነገር በብዙዎች ተደርጎ ቢሆን አሁን ላይ ብቻ ሳይሆን ከብዙ ጊዜ ጀምሮ ብዙዎች ንስሐ በገቡ ነበር ታድያ ይህ ሁኔታችን የእግዚአብሔርን የተአምራት ጉብኝት የከለከለ ሆነ ከዚህም ሌላ ብዙዎች ንስሐ ገብተው እንዳይድኑ የብዙዎችን ሕይወት አቁሮ ያዘ ለዚህም ነው ሰዎች ወንጌል ሲመሰከርላቸው አምነው በንስሐ ይቀበላሉ ተብለው ሲጠበቁ ለእናንተ ያልሆነ ወንጌል እንዴት ለእኛ ይሆናል ?ሲሉ የሚስተዋሉት   በመሆኑም እኛን የፈወሰ ወንጌል ነው ሌሎችን ሊፈውስ የሚችለው አሁንም ለእኛ ያልሆነ ወንጌል ለሌሎች ሊሆን አይችልም ወገኖቼ ሆይ ታድያ ወንጌል ለእኛ ሳይሆን ቀርቶ አይደለም እኛ እንደ ቤተ ሳይዳ ግዴለሾች ስለሆንንና አንገራጋሪ ሕይወት  ስለያዝን  ንስሐ የሚገባ ልብ የለንም ከዚህ የተነሳ  ጌታ ዛሬም መፈወስ ሲፈልግ ሥራውን ያላቆመ ማቆምም የማይፈልግ አምላክ በመሆኑ  ሰዎችን ካለንበት መንደር አውጥቶ በደጅ በአፍ አና በውጪ ይፈውሳል ወደ መንደሩም አትግባ ለማንምም አንዳች አትናገር ይላል ምስክርነት ከዚህም ሌላ ጌታም እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረገልን የሚነገረው የንስሐ ልብ ኖሮአቸው ለሚጠቀሙ ሰዎች ነው ከዛ ውጪ ግን እንቁን በእሪያ ፊት መጣል ይሆንብናልና አይነገርም የማቴዎስ ወንጌል 7 6 ወገኖቼ ጌታ እግዚአብሔር የንስሐ ዕድል የሚሰጠን በሕይወት ሊያኖረን ነው ለዚህም ነው በራዕይ 3 20 ላይ እንግዲህ ቅና ንስሐም ግባ በማለት  የጻፈልን ስለዚህ ባለንበት ሁኔታ ተመቻችተንና ሀገር ሰላም ነው ብለን ከመቀመጥ ይልቅ ንስሐ ለመግባት ብንቀና ከለብታና ከበራድ ሕይወት እንወጣለን በብዙም ልናፈራ የተዘጋጀን እንሆናለን ንስሐ ለመግባት መቅናት ማለት ደግሞ አዲሱ የመጽሐፍቅዱስ ትርጉም እንደሚነግረን ንስሐ ለመግባት መትጋት የሚለውን ትርጉም በመስጠት  ነው ንስሐ ለመግባት ስንተጋ ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ እንደተባለችው መንደር አንሆንም ጌታም በመንደራችን በውስጠኛው ክፍል ሆኖ ይፈውሳል እንጂ ከከተማችን በደጅ ሆኖ እና የተፈወሰውንም ሰው ወደዚህ ከተማም ሆነ መንደር አትግባ ለማንም አንዳች አትንገር ሲል ትዕዛዝ ሰጥቶ አይሄድም ወገኖቼ የጌታ ፈውስ ለሰፈራችንም ሆነ ላለንበት መንደር እጅግ በጣም የራቀ ከመሆኑ የተነሳ መስማታችን ሳይቀር በሕይወታችን እውን አይደለምና አሉታዊ  ነው በመሆኑም እንስማ ብንል እንኳ የምንሰማው የስማ በለው ያክል ነው ይህ ደግሞ በሕይወታችን ላይ አሳዛኝ ክስተት እያመጣ ያለ  በመሆኑ እጅግ አስከፊ እየሆነ የመጣ ጉዳይ ሆኗል የሉቃስ ወንጌል 13 1 _ 5 ስለዚህ እግዚአብሔር ከዚህ ሕይወት ያውጣን ይመልሰን ክፍል አምስት ( ሐ ) ከዚህ ትምህርት በኋላ የሚቀጥል ይሆናል ተባረኩልኝ ለዘላለም

Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ
                                                                                          
ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ



No comments:

Post a Comment