Saturday, September 12, 2015

አደገኛ ማታለል Dangers of Deception ክፍል ሦስት

አደገኛ ማታለል
                             

Dangers of Deception




ክፍል ሦስት





ኢየሱስ እንደተናገረው ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ መንገዱም የቀጠነ ነውና የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው አለን የማቴዎስ ወንጌል 7 14 ይሁን እንጂ አብዛኛው ሕዝብ የኢየሱስን ቃል ቸል ብሎአል Ignore (ኢግኖር) አድርጎአል ከዚህም ቃል ጋር አልተስማማም ጌታ ኢየሱስ ለእውነተኛ ደቀመዛሙርቶቹ አስረግጦ በጠበበው ደጅ ግቡ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ መንገዱም ትልቅ ነውና ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው ይለናል የማቴዎስ ወንጌል 7 13 ሌላው ቀርቶ አንድ ጊዜ የጌታ ደቀመዛሙርት የሆኑትን እንኳ ሳይቀር ሰይጣን በስሕተት ትምህርቱ ወደኋላ ጠርጎ የመውሰድ ኃይል አሳይቶ ነበር ሕጉን በመፈጸም እግዚአብሔርን ለማስደሰት ለሚፈልግ ጻድቅ ክፉ የሆነ  የዚህ ዓለም አሳች እና አለቃ መንፈስ ነው ሐዋርያው በዚህ ጉዳይ ላይ ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምንአልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ የሚመጣውን ያልሰበክነውን ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክ ወይም ያላገኛችሁትን ልዩ መንፈስ ወይም ያልተቀበላችሁትን ልዩ ወንጌል ብታገኙ በመልካም ትታገሡታላችሁ ይለናል 2 ቆሮንቶስ 11 3 _ 4 አዲሱ የመጽሐፍቅዱስ ትርጉም ደግሞ ያልተቀበላችሁትን ልዩ ወንጌል ብታገኙ በመልካም ትታገሡታላችሁ የሚለውን አባባል ከተቀበላችሁት ወንጌል የተለየ ወንጌል ብትቀበሉ ነገሩን በዝምታ ታልፉታላችሁ በማለት ይገልጸዋል  ጳውሎስ በቀላሉ ከክርስቶስ ትምህርት ፊታቸውን የመለሱትንና ወደዚህ ወደ ስሕተት አሠራር የገቡትን ይደነቅባቸዋል በተታለለው መንፈሳቸውም ያፍርባቸዋል ሰይጣን የማታለል አዛዥ መሪና ጌታ ነው Satan is the master deceiver  አብዛኛው ሕዝባችን በቀላሉ ታድኖ የሚበላ ነው በእግዚአብሔር የእውነት ቃል ከተመለሰ በኋላ እንኳ   በሐሰተኛ አስተማሪዎች የሚሳብ እነርሱም ሊያባብሉት የሚሞክሩ ሊያሳምኑትም የሚችሉ ናቸው እነዚህ አስተማሪዎች ጭልፊቶች ትክክለኛ ያልሆኑና አስመሳይ የጽድቅ አገልጋዮች ናቸው 2 ቆሮንቶስ 11 13 _ 15 እነዚህ የሐሰት አስተማሪዎች ከጌታ ከኢየሱስ ስም ሥር የሚመጡ ለሃይማኖት ሰዎችም ስሙን እንደ ማስክ ለብሰው ነው የሚያገለግሉት በእግዚአብሔር ቃል የሆነ ትክክለኛ የእምነት መረዳት እና ዶክትሪን ያስገኛቸው አይደሉም ጌታ ስለዚህ ጉዳይ ሲናገር በዚያን ቀን ብዙዎች ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን ? በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን ? በስምህስ ብዙ ተአምራት አላደረግንምን ? ይሉኛል የዚያን ጊዜም ከቶ አላውቃችሁም እናንተ አመጸኞች ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ ይለናል የማቴዎስ ወንጌል 7 22 እና 23 ጌታ የምናነበውን ቃል እንድናስተውለውና እንድንጠቀምበት ይርዳን አሜን

 

Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና ባለ ራዕይ

ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ



 

 

 



No comments:

Post a Comment