Thursday, April 30, 2015

004 ይህ በ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry ሥር እየተዘጋጀ የሚቀርብላችሁ ትምህርት ነው የትምህርት ርዕስ ኢየሱስ ክርስቶስ የአብ ሊቀካህናት ነው የአብ ሊቀካህናት የሆነው እርሱ ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር አስታረቀ የተወደዳችሁ ወገኖች ሊቀካህናት ማለት ምን ማለት ነው ስንል ሊቀካህናት ማለት በአጭር ቃል አስታራቂ አማላጅ ማለት ነው ታድያ ኢየሱስ ክርስቶስ የአብ ሊቀካህናት መባሉ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር በማስታረቁ ነው ከእርሱ ውጪ ይህንን የማስታረቅን ሥራ የሰራ ማንም የለም ለዚህ ነው መጽሐፍቅዱሳችን ብቻ ሳይሆን አንጋፋው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሃይማኖተ አበው የተባለው መጽሐፍ እና የቤተክርስቲያኒቱም የእምነት መግለጫ አመክንዮ ዘሐዋርያት ወአረቀ ትዝምደ ሰብእ ምስለ እግዚአብሔር ሊቀካህናቲሁ ለአብ ትርጉም የአብ ሊቀካህናት እርሱ ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር አስታረቀ ሲሉ የጻፉልን ቤተክርስቲያኒቱም እንዲሁ ስትል አጽንታና ጸንታም ነው እስከ ዛሬ ድረስ በዚሁ በእምነት መግለጫዋ ላይ ያሰፈረችልን ይሁን እንጂ ይህንን መጽሐፍቅዱሳዊ የእውነት ቃል በእምነት መግለጫዋ ላይ ዘግባ ታድያ ለምን የኢየሱስን ብቸኛ አማላጅነትና አስታራቂነት መስበክ እንደቸገራት ለኛ ለሁላችንም ግልጽ ሊሆንልን አልቻለም ኢየሱስ የአብ ሊቀካህናት ሆኖ ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር አስታረቀ ብላ የምትሰብክና የምታስተምር ከሆነ ደግሞ በእርሱ ብቻ ታርቃ ወደ መንግሥቱ መግባቷን ታውጃለች እንጂ እንደገና ወደኋላ ተመልሳ የፍጡራንን አስታራቂነት አምና እና በእነርሱም ተማጽና በእነርሱ በኩል ወደ መንግሥቱ እገባለሁ ስትል ለዘጸውአ ስመኪ ወለዘገብረ ተዝካረኪ እምሕር ለኪ ለዘጸውአ ስመከ ወለዘገብረ ተዝካረከ እምሕር ለከ ትርጉም ስምሽን የጠራ ተዝካርሽን ያደረገ ስምህን የጠራ ተዝካርህን ያደረገ እምርልሻለሁ እምርልሃለሁ እያለች ሰዎች በጻድቁ ስም አሻሮ ቆልተውና ዳቦ ጋግረው ስላበሉ ገድሉን ስላነበቡና ጢስ ስለጤሰባቸው ወይም ሻማ ስለለኮሱ ጧፍ እጣን ስለቀረቡ ይጸድቃሉ ስትል አትናገርም አታውጅም ሰዎችንም ለዚህ ነገር አታነሳሳም በእርግጥ ነቢይን በነቢይ ስም መቀበል ጻድቅንም በጻድቅ ስም መቀበል ዋጋ እንዳለው መጽሐፍቅዱስ ቢነግረንም ዋጋው ግን የደኅንነት ዋጋና መንግሥተሰማያት የመግባት ዋጋ አይደለም ይህንን ዋጋ ከፍሎ በነጻ ያጸደቀንና በጸጋውም ያዳነን ኢየሱስ ብቻ ነው መዳን ከኢየሱስ ውጪ በሌላ በማንም የለምና የሐዋርያት ሥራ 4 ፥ 12 ነቢይንም ሆነ ጻድቅን ለመቀበልና ይህንኑ የጻድቁንም ሆነ የነቢዩን ዋጋ ለማግኘት ደግሞ በመጀመርያ በዚህ ጌታ አምኖ መዳን ያስፈልጋል አምኖ የዳነ ሰው ሲቀበል ነው ዋጋው የማይጠፋበት ማለት የሚድነው የዘላለም ሕይወት የሚያገኘው ማለቴ ሳይሆን ጻድቁንና ነቢዩን በመቀበሉ የሚሸለመው ማለቴ ነው መጽሐፉ የሚያስተምረን ይህንን እውነት ነው ታድያ ለዚህ ሁሉ እውነት ለመድረስና ለመብቃት የኢየሱስን ብቸኛ አዳኝነትና አማላጅነት በቅድሚያ መቀበል አማራጭ የሌለው ነገር ነው በመሆኑም ይህንን የኢየሱስክርስቶስን ብቸኛ የአብ ሊቀካህናትነትና አማላጅነት የአሁንዋ ኦርቶዶክስ ለመስበክ ቢዳዳትም የጥንቷ ሐዋርያዊት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናችን ግን በእምነት መግለጫዋ ላይ ሳይቀር ያሰፈረችው ነውና ሰብካዋለች አስተምራዋለች ስለዚህ አሁን ላይ የተነሳን እኛም አገልጋዮች ደግሞ ይህን የኢየሱስ ክርስቶስን ብቸኛ አማላጅነትና የአብ ሊቀካህናት መሆን ሳንሸፋፍን ግልጽልጽ አድርገን እንሰብከዋለን እናስተምረዋለን ወገኖቼ ትምህርቱ ሁለት ተከታታይ ክፍለ ጊዜያቶች የያዘ ቢሆንም በሁለት ክፍለጊዜያቶች የሚጠቀለል ብቻ ሳይሆን ወደፊትም በስፋት እየቀጠልን የምናስተምረው ስለሆነ በነዚህ አጫጭር ትምህርቶች ብቻ የምንቋጨው አይደለም ከዚህም ሌላ ይህንን የኢየሱስን አማላጅነት በተመለከተ በጽሑፍ ሳይቀር አስፍሬ የለቀቅሁዋቸው ትምህርቶች ስለሉ እነርሱን በብሎጎቼና በፌስ ቡክ እንዲሁም በጎግል ወስጥ በመግባት እና እየፈለጋችሁም በማንበብ ልትጠቀሙ የምትችሉ መሆናችሁን ከወዲሁ ላሳስብ እወዳለሁ አሁን ግን በጥቂቱ ያቀረብኳቸውን ሁለት ተከታታይ የኦድዮ ትምህርቶችን በሚገባ እንድትከታተሉአቸው በጌታ ፍቅር እጠይቃለሁ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን የJoshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry መሪና ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment