Friday, April 3, 2015

የሚመራ መፈለግ Seeking guidance ክፍል ሁለት ለእግዚአብሔር ሕግ መታዘዝ አንዱና ዋናው የቤተክርስቲያን ጠባይ ነው

የሚመራ መፈለግ


Seeking guidance


ክፍል ሁለት



ለእግዚአብሔር ሕግ መታዘዝ አንዱና ዋናው የቤተክርስቲያን ጠባይ ነው



የተወደዳችሁ ወገኖች በቃሉ አገልጋዮችም ይሁን በቤተክርስቲያን አገልግሎት ወደ ቃሉ ስንመራና የእግዚአብሔርን ቃል ስናውቅ የእግዚአብሔርን ቃል ለመታዘዝ እንነሳለን ሐዋርያው ጳውሎስ ለእግዚአብሐር ሕግ በመታዘዝ ምክንያት የሚገኘውን ጥቅም እንዲህ ሲል ይገልጸዋል ነገር ግን አስቀድማችሁ የኃጢአት ባሪያዎች ከሆናችሁ፥ ለተሰጣችሁለት ለትምህርት ዓይነት ከልባችሁ ስለ ታዘዛችሁ፥ ከኃጢአትም አርነት ወጥታችሁ ለጽድቅ ስለ ተገዛችሁ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ሮሜ 6 17 እና 18 የሮሜ ክርስቲያኖች ከኃጢአት ነጻነት ወጥተው የጽድቅ ባርያዎች ሆነዋል ታድያ እንዲህ እንዲሆኑ ያስቻላቸው ነገር ምንድርነው ? ስንል ከዚህ በፊት የኃጢአት ባሮች ነበሩ ነገር ግን ለተሰጡለት ትምህርት በሙሉ ልብ የታዘዙ በመሆናቸው ሐዋርያው ጳውሎስ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን በማለት ሳይደመድም የሮሜ ክርስቲያኖችን የመታዘዝ ውጤት ነገረን ከኃጢአት ነጻ ወጥታችሁ የጽድቅ ባርያዎች ሆናችኋል ሲላቸው እንመለከታለን ለእግዚአብሔር ሕግ መታዘዝ ሌላ የተለየ መታዘዝን ብቻ የሚያስከትል ሳይሆን ለተለየ ውጤትም የሚያበቃ ነው ለእግዚአብሔር ሕግ ከልብና ሙሉ የሆነ መታዘዝን በምናደርግበት ጊዜ ከኃጢአት ነጻነት ወጥተን የጽድቅ ባርያዎች መሆን እንጀምራለን ወገኖቼ የጽድቅ ባርያ ብቻ ሳይሆን  ከኃጢአት ነጻ መውጣት በራሱ የሚቻለው ለእግዚአብሔር ሕግ ከመታዘዝ የተነሳ ነው ለዚህ ነው መጽሐፍቅዱሳችን በገላትያ 5 13 ላይ ወንድሞች ሆይ፥ እናንተ ለአርነት ተጠርታችኋልና፤ ብቻ አርነታችሁ ለሥጋ ምክንያትን አይስጥ፥ ነገር ግን በፍቅር እርስ በርሳችሁ እንደ ባሪያዎች ሁኑ የሚለን በመሆኑም እርስ በእርስ በፍቅር ባርያዎች ወደምንሆንበት ሕይወት ውስጥ የምንገባው በቅድሚያ ወደ ተጠራንበት አርነት ስንመጣና በዚሁ በቃሉ  አርነት ስንወጣ ነው አለበለዚያ ግን ባርነቱ የፍቅር መሆኑ ይቀርና የሌላ ይሆናል ይህ በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ የሰጠንን ነጻነት ሳይቀር የሚጋፋ ይሆንና እንደገና ወደ ከፋ ባርነት ውስጥ ይከተናል ለዚህ ነው ሐዋርያው አሁንም ጸንታችሁ ቁሙ እንደገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ ሲል የመከረን ይህን ማለቱ ግን አርነታችሁ ለሥጋ ምክንያት ይስጥ ማለቱ እንዳልሆነ ለሁላችንም ግልጽ ሊሆን ይገባል ስለዚህ አንዳንዴም አስተውለን ብቻ ሳይሆን ባለማስተዋልና የቃሉን እውነትም እንደሚገባ ባለመረዳት በባርነት ቀንበር መያዝ አለ ገላትያ 5 1 ለአርነት የተጠራ ሰው ተቀዳሚና መጀመርያ የሆነውን አርነቱን የሚያገኘው በእግዚአብሔር ቃል ነው በዮሐንስ ወንጌል 8 31 _ 37 ላይ ሄደን ስንመለከት ኢየሱስም ያመኑትን አይሁድ እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው እነርሱም መልሰው የአብርሃም ዘር ነን ለአንድም ስንኳ ከቶ ባሪያዎች አልሆንም፤ አንተ አርነት ትወጣላችሁ እንዴት ትላለህ ? አሉት ኢየሱስ መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ኃጢአት የሚያደርግ ሁሉ የኃጢአት ባርያ ነው ባርያም ለዘላለም በቤት አይኖርም፤ ልጁ ለዘላለም ይኖራል እንግዲህ ልጁ አርነት ቢያወጣችሁ በእውነት አርነት ትወጣላችሁ የአብርሃም ዘር መሆናችሁንስ አውቃለሁ ነገር ግን ቃሌ በእናንተ አይኖርምና ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ እንግዲህ አርነት መውጣት የሚቻለው አንድና አንድ በሆነው በእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው የእነ እገሌ ዘር ነኝ የእነርሱ ደቀመዝሙር ነበርኩ በእነርሱ ሥር ነው ተኮትኩቼ ያደኩት ከልጅነቴ ዘመን ጀምሮ እንዲህና እንዲያ ነኝ በማለት አርነት አይመጣም የታወቁ ስመጥር አገልጋዮችና የተቀቡ የእግዚአብሔር ሰዎች ሌላም ሌላም ልንል እንችላለን እሰየው መልካም ነው አርነት ግን የሚገኘው የእግዚአብሔርን ቃል በማመንና በማወቅ ብሎም ያመነውንና ያወቅነውን ቃል በመታዘዝ ነው ከዚህ ውጪ ግን ሥራችን ይመሠክርብናልና አርነት የለም ቃሉ በሌለበት ሰው ውስጥ ያለው የአብርሃም ዘር ነን ለአንድም ስንኳ ባሮች አልሆንም ባሉት በአይሁድ ውስጥ እንደነበረው ዓይነት  ቅናት ጥል ክርክር ዛቻ ግድያና የመሣሠሉት ነገር ነው ያለው ከዚህ በመቀጠል በራዕይ መጽሐፍ ላይ የእግዚአብሔር ሕዝብ ሥዕል ምን እንደሚመስል እንመለከታለን በራዕይ 14 12 ላይ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁት ኢየሱስንም በማመን የሚጸኑት ቅዱሳን ትዕግሥታቸው በዚህ ነው ይለናል መጽሐፍቅዱሳችንን አውጥተን ስንመለከት ደግሞ ቤተክርስቲያን ታዋቂ ድርጅትና ትልቅ ዲኖሚኔሽን አይደለችም ክርስቶስ ስለዚችው ቤተክርስቲያን ሲናገር አንተ ታናሽ መንጋ መንግሥትን ሊሰጣችሁ የአባታችሁ በጎ ፈቃድ ነውና አትፍሩ ነው ያለው የሉቃስ ወንጌል 12 32 እንደገናም በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነውና፥ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው አለን የማቴዎስ ወንጌል 7 13 እና 14 እንመልከት በያዕቆብ መጽሐፍ ላይ ደግሞ አመንዝሮች ሆይ ዓለምን መውደድ ለእግዚአብሔር ጥል እንዲሆን አታውቁምን ? እንግዲህ የዓለም ወዳጅ ሊሆን የሚፈቅድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል ይለናል ያዕቆብ 4 4 በውጤቱም ይህንን ዓለም የሚከተሉ ሰዎች በትክክለኛው በሰይጣን ዓለም ውስጥ ናቸውና ለእነርሱም የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን ሃሳብ አሳወረ በማለት ተናገረን 2 ቆሮንቶስ 4 4 እንደገናም ከእግዚአብሔር እንደሆንን ዓለምም በክፉ እንደተያዘ እናውቃለን ይለናል 1 ዮሐንስ መልዕክት 5 19 ጌታ እግዚአብሔር በምናነበው ቃል ያሳድገን ሕይወታችንንም  ይለውጥልን


የቃሉ አገልጋይ ቄስ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment