Saturday, April 25, 2015

163 የትምህርት ርዕስ የእግዚአብሔር ወገን የሆነ ሁሉ ወደ እኔ ይምጣ ሙሴ ወግኖ የለየለት ሰው ስለሆነ የእግዚአብሔር ወገን የሆነ ሁሉ ወደኔ ይምጣ አለ ወግነን የተለየን በምንሆንበት ጊዜ በአገልግሎት አናመቻምችም በሕይወት በኖሮ እና በመሣሠሉት መንፈሳዊ ነገሮቻችን አናመቻምችም በአጠቃላይ የተመቻመቸ ሕይወት የለንም የእስራኤል መሪዎች ሙሴም ሆነ ከሙሴ በኋላ የተነሳው ኢያሱ ወግነው የለየላቸው ባይሆኑ እስራኤልን ዳር ማድረስ አይችሉም ነበር የእስራኤል ሕይወት በምድረበዳ የሚያስቀር ሕይወት ነው ምክንያቱም መጽሐፍቅዱሳችን ከእነርሱ በሚበዙቱ ደስ አላለውም በምድረበዳ ቀርተዋልና ይለናል ወግኖ ለመለየት ከእግዚአብሔር ጋር በሕይወት ማንነትና የግንኙነት መስመር መተዋወቅ ያስፈልጋል ያን ጊዜ እግዚአብሔር አገልግሎታችንን ሕይወታችንን ያጸናል ወግነን ስንለይ በቀላሉ አንንበረከክም ሁሉን እንመረምራለን ሁሉን ፈትኑ መልካሙን ያዙ ተብሎ ተጽፎልናልና ወግነን ስንለይ የእግዚአብሔር ክብር ይገለጥብናል ኢያሱ ጸሐይ እንዳቆመ ገስግሶ ጠላቶችንም እንደመታ ለእኛም እንዲሁ ይሆናል ከዚህም ሌላ ኢያሱ ወደ ሠፈረበት ሕዝቡ መጥቶ ይሰፍር ነበር ይለናል እንደገናም እንዲህ በምንሆንበት ጊዜ የራስ ጸጉራችን ሳይቀር የተቆጠረ ስለሆነ የምንሆነው ነገር የለም እና በፍጹም ልንፈራ አይገባም ጌታ በጆሮ ያሰማንን በሰገነት ልናሰማ በጨለማ የነገረንን በብርሃን ልንናገር ጊዜው ስለሆነ የተዘጋጀን ልንሆን ይገባል በኢያሱ ዘመን ማንም በእስራኤል ላይ ምላሱን ማንቀሳቀስ አልቻለም ነበር ወግነን ስንለይ እግዚአብሔር የሐሜት የአሉባልታ የአድማና የስድብ ምላሶችን ይቆልፋል ክፋቱንና ቅናቱንና ተንኮሉንም ጭምር ያኔ በእኛ ላይ የሚያንቀሳቅስብን አይኖርም ኢያሱ ወግኖ የተለየ ስለሆነ ይህም ሳይበቃው በአምልኮ ሳይቀር እኔና ቤቴ እግዚአብሔርን እናመልካለን እናንተ ግን የምታመልኩትን ምረጡ አለ ለዚህ ነው እንግዲህ አምልኮው በእርሱ ሳይቋረጥ በቀጣይነት ወደ ትውልድ የተሻገረው ወገኖቼ የትምህርቱ ሃሳቦች እነዚህንና የመሳሰሉትን ጠቅልሎ የያዘ ነው በመሆኑም ትምህርቱ በተከታታይ ከክፍል አንድ እስከ ክፍል ስድስት ድረስ የቀረበ በመሆኑ እየገባችሁ እንድትከታተሉ በጌታ ፍቅር ላሳስብ እወዳለሁ ጌታ ይባርካችሁ የ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry አገልጋይና መሪ ባለ ራዕይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment