Thursday, April 2, 2015

የሚመራ መፈለግ Seeking guidance ክፍል አንድ

የሚመራ መፈለግ


Seeking guidance


ክፍል አንድ


ይህ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry ሥር እየተዘጋጀ የሚቀርብላችሁ ትምህርት ነው

ፊልጶስም ሮጦ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ሲያነብ ሰማና በውኑ የምታነበውን ታስተውለዋለህን ? አለው
እርሱም፦ የሚመራኝ ሳይኖር ይህ እንዴት ይቻለኛል ? አለው

የሐዋርያት ሥራ  8 30 እና 31


ወጥቶም ከእርሱ ጋር ይቀመጥ ዘንድ ፊልጶስን ለመነው ያነበውም የነበረ የመጽሐፉ ክፍል ይህ ነበረ፤ እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፥ የበግ ጠቦትም
በሸላቹ ፊት ዝም እንደሚል፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም በውርደቱ ፍርዱ ተወገደ፤ ሕይወቱ ከምድር ተወግዳለችና ትውልዱንስ ማን ይናገራል ?
ጃንደረባውም ለፊልጶስ መልሶ፦ እባክህ፥ ነቢዩ ይህን ስለ ማን ይናገራል ? ስለ ራሱ ነውን ? ወይስ ስለ ሌላ ? አለው ፊልጶስም አፉን ከፈተ፥ ከዚህም
መጽሐፍ ጀምሮ ስለ ኢየሱስ ወንጌልን ሰበከለት በመንገድም ሲሄዱ ወደ ውኃ ደረሱ፤ ጃንደረባውም  እነሆ ውኃ፤ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ
ምንድር ነው ? አለው ፊልጶስም  በፍጹም ልብህ ብታምን፥ ተፈቅዶአል አለው መልሶም ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ አምናለሁ
አለ ሰረገላውም ይቆም ዘንድ አዘዘ፥ ፊልጶስና ጃንደረባው ሁለቱም ወደ ውኃ ወረዱ፥ አጠመቀውም ከውኃውም ከወጡ በኋላ የጌታ መንፈስ ፊልጶስን
ነጠቀው፤ ጃንደረባውም ሁለተኛ አላየውም፥ ደስ ብሎት መንገዱን ይሄድ ነበርና

      
የሐዋርያት ሥራ  8 32 _ 39


በግልጽነት  ከእግዚአብሔር አገልጋይ እርዳታን መፈለግ ዋነኛውን የእግዚአብሔርን ቃል ለመረዳት ይጠቅማል ስለዚህ ጉዳይ ጳውሎስ የተናገረው ነገር አለ  እንግዲህ ያላመኑበትን እንዴት አድርገው ይጠሩታል ? ባልሰሙትስ እንዴት ያምናሉ ?  ያለ ሰባኪስ እንዴት ይሰማሉ ?  መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው ተብሎ እንደ ተጻፈ ካልተላኩ እንዴት ይሰብካሉ ? ይለናል ሮሜ 10 14 _ 15 እንደገናም ጴጥሮስን እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም አለው የማቴዎስ ወንጌል 16 28 ደቀመዛሙርቱን በአንድ ላይ ደግሞ እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ በማለት መመርያ ሰጣቸው የማቴዎስ ወንጌል 28 ፥ 19 እና 20 ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ቃል እውነትን ለማስተማር ሃላፊነት አለባት እያንዳንዱ በግሉ ደግሞ ቤተክርስቲያን የምታስተምረውን ሊሰማ ሃላፊነት አለበት ቤተክርስቲያን ሕንጻ አይደለችም ወይም የምትታይ ድርጅትም አይደለችም ነገር ግን እንደ ሕዝብ በእግዚአብሔር መንፈስ የምትመራ ናት የሕዝቦች ሕብረት የሚረዳው ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን መንፈሳዊ እውነት ለመማር ነው በዚህ ውስጥ ግን ጌታ ሁሉን ፈትኑ መልካሙን ያዙ ብሎናል 1 ተሰሎንቄ 5 23 ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ሐዋርያው ጳውሎስ ቲቶን እንዲህ ሲል ይናገረዋል ስለዚህ ምክንያት የቀረውን እንድታደራጅ በየከተማውም፥ እኔ አንተን እንዳዘዝሁ፥ ሽማግሌዎችን እንድትሾም በቀርጤስ ተውሁህ የማይነቀፍና የአንዲት ሚስት ባል የሚሆን፥ የሚያምኑም ልጆች ያሉት፥ ስለ መዳራትም ወይም ስለ አለመታዘዝ የማይከሰስ ማንም ቢኖር፥ ሹመው ኤጲስ ቆጶስ፥ እንደ እግዚአብሔር መጋቢ፥ የማይነቀፍ ሊሆን ይገባዋልና፤ የማይኮራ፥ የማይቆጣ፥ የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ፥ ነውረኛ ረብ የማይወድ ነገር ግን እንግዳ ተቀባይ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚወድ፥ ጠንቃቃ፥ ጻድቅ፥ ቅዱስ፥ ራሱን የሚገዛ ይሁን ሕይወት በሚገኝበት ትምህርት ደግሞ ሊመክር ተቃዋሚዎቹንም ሊወቅስ ይችል ዘንድ፥ እንደተማረው በታመነ ቃል ይጽና የማይታዘዙና ከንቱ የሚናገሩ የሚያታልሉ ይልቁንም ከተገረዙት ወገን የሚሆኑ ብዙ ናቸውና ቲቶ 1 5 _ 9 ስለ ሐሰተኛ ነቢያትም የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ይናገራል የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን ? ይለናል እንደገናም በዚያ ቀን ብዙዎች ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን ?  ይሉኛል የዚያን ጊዜም ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ ይለናል የማቴዎስ ወንጌል 7 15 _ 16 22 _ 23 እንመልከት ስለዚህ የነቢያትን ቃል የምንፈትንበት የእግዚአብሔር ቃል አለን መጽሐፉ ሲናገር እንዲህ ይላል የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ ተፈትናለች እርሱ ለሚታመኑት ጋሻ ነው እንዳይዘልፍህ፥ ሐሰተኛም እንዳትሆን በቃሉ አንዳች አትጨምር ይለናል እንደገናም ወደ ሕግና ወደ ምስክር ሂዱ፦ እንዲህም ያለውን ቃል ባይናገሩ ንጋት አይበራላቸውም ምሣሌ 30 5 - 6 ኢሳይያስ 8 20 እግዚአብሔር አምላክ በምናነበው ቃል ብዙ የሆነ መረዳቱን ይስጠን የክፍል ሁለት ትምህርት ይቀጥላል ተባረኩልኝ





ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ነኝ

No comments:

Post a Comment