Monday, April 20, 2015

ለ - እያንዳንዱ መረዳቱንና መታዘዙን ማጠንከር Understanding and obedience reinforce each other ክፍል አምስት

Seeking guidance


የሚመራ መፈለግ



- እያንዳንዱ መረዳቱንና መታዘዙን ማጠንከር

Understanding and obedience reinforce each other


ክፍል አምስት



ትክክለኛ ባሕርይ የሚመራው ሕጉን እንድንታዘዝ ነው ይህም የሚሆነው ብዙ የመጽሐፍቅዱስ መሠረት ሲኖረን ነው  በመዝሙር 119 34 ላይ እንዳስተውል አድርገኝ ሕግህንም እፈልጋለሁ በፍጹም ልቤም እጠብቀዋለሁ ይለናል መዝሙሮቹ አስተማሪዎች ስለሆኑ ብዙ ጊዜ የወንድማችንን ዘማሪ ፓስተር ተስፋዬ ጋቢሶን መዝሙር መጥቀስ ደስ ይለኛል መዝሙሩም ከብዙ በጥቂቱ እንዲህ የሚል ነው እንግዲህ ጌታ ሆይ እንዳስተውል አርገኝ በቀረልኝ ዘመኔ ፈቃድህን እንዳደርግ አስተምረኝ አስተምረኝ ፈቃድህን አውቆ መታዘዙ ጠቅሞኝ ከኃጢአትም መራቅ ማስተዋል ሆኖልኝ መልካም ሥርዓትህን ተምሬ ተምሬ በእንግድነት ሀገር ዘምራለሁ ዛሬ ዘምራለሁ ዛሬ ሲል ዘምሮልናል እግዚአብሔር ለእኛ የገለጠልንን መረዳት ከጣልን ወይም ካልያዝን ካቃለልን በሆሴዕ መጽሐፍ ላይ ሕዝቤ እውቀት ከማጣት የተነሳ ጠፍቶአል አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆን እጠላሃለሁ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ ይለናል ሆሴዕ 4 6 የእግዚአብሔርን ቃል ለመረዳት የእግዚአብሔርን ሕግ መማርና ማክበር አለብን የእግዚአብሔርን ሕግ ስናከብር ያኔ ነው እንግዲህ ዘማሪ ተስፋዬ እንደዘመረልን ፈቃዱን አውቀን የመታዘዝ ጥቅሙ የሚገባን እንደገናም ይህ ብቻ አይደለም ከኃጢአትም መራቅ ማስተዋል መሆኑን በብዙ እንረዳለን ዛሬ ግን በዘመናችን በተለይ የሕጉን መጽሐፍ ከማንበብና ከመስበክ ያለፈ ነገር ስለሌለ ብዙውን ጊዜ የመታዘዝ ጥቅሙ ምን እንደሆነ ከብዙ በጥቂቱ ቢገባንም  ከኃጢአት መራቅ ማስተዋል መሆኑን ግን በፍጹም አንረዳምና በምግባራችን በብዙ ስንስት እና ሰዎችንም ስናስት እንገኛለን የጥበብ መጀመርያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ለሚያደርጓትም ደህና ማስተዋል አላቸው ምስጋናውም ለዘላለም ይኖራል በማለት መዝሙረኛው ይነግረናል መዝሙር 111 10 በእርግጥም በትክክለኛ ሁኔታ ወደ ተሻለ የመጽሐፍቅዱስ መረዳት ለመምጣት ከፈለግን ምን እንደተረዳንና ምን እንደተከተልን ማስተዋል አለብን ብዙ በተማርነው ቃል ልክ መንገዳችንንም መለወጥ አለብን በእግዚአብሔር ፊት ሕግን የሚያደርጉት ይጸድቃሉ እንጂ ሕግን የሚሰሙ ጻድቃን አይደሉምና ሮሜ 2 13 ሰዎች ብዙ ጊዜ ለመናገር ለመስበክ ለማስተማርና ብሎም ለመዘመር ሳይቀር ይሰማሉ መጽሐፍቅዱሱንም ያጠናሉ በተለይ በአሁን ዘመን በአብዛኛው ሰዎች መጽሐፍቅዱሳቸውን የሚያጠኑት የተናገረውን ለመስማት ነው ነገር ግን ያዘዘውን ለማድረግ አይደለም ይህ እግዚአብሔርን አያስደስተውም ጌታ በማቴዎስ ወንጌል 5 17 _ 18 ላይ እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም፥ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ እንግዲህ ከነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ ታናሽ ይባላል፤ የሚያደርግ ግን የሚያስተምርም ማንም ቢሆን እርሱ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ ይባላል ይለናል የማቴዎስ ወንጌል 5 17 _ 19 እንደገናም በማቴዎስ ወንጌል 7 21 _ 23 ላይ በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም በዚያ ቀን ብዙዎች ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን ? በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን ? በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን ? ይሉኛል የዚያን ጊዜም ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ በማለት ይነግረናል ስለዚህ አጋንንትን ማውጣትም ሆነ ትንቢት መናገር ለመንግሥተ ሰማያት መግቢያ እንደ ዋስትና የሚሆነን አይደለም በሰማያት ያለውን የአብን ፈቃድ እስካላደረግን ድረስ አጋንንት በማውጣታችንና ትንቢት በመናገራችን ብቻ እግዚአብሔር የሚያውቀን አይሆንም እንደውም የሚለን ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ነው በዮሐንስ ወንጌል 15 10 ላይ እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ጠበቅሁ በፍቅሩም እንደምኖር፥ ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ ይለናል ጌታ ያስተማረን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ እንድንጠብቅ ነው ከእርሱም መራቅ የለብንም በሐዋርያት ሥራ 5 32 ላይ ደግሞ እኛም ለዚህ ነገር ምስክሮች ነን፥ ደግሞም እግዚአብሔር ለሚታዘዙት የሰጠው መንፈስ ቅዱስ ምስክር ነው ይለናል ስለዚህ የተገለጠውን መንፈሳዊ እውነት መረዳት ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔርን ሕግና መመርያ ማለት በቅዱስ መጽሐፉ ያየነውን ቁልፍ ሃሳብ በጥሩ ሁኔታና በመታመን እንድንታዘዘው የሚጠይቅ ነው ስለዚህ መንፈሳዊ መረዳታችን እንዲቀጥል መታዘዛችን አስፈላጊ ነው ይህን በተመለከተ ያዕቆብም እንዲህ ሲል ገልጦታል አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን ? እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደ ነበረ፥ በሥራም እምነት እንደ ተፈጸመ ትመለከታለህን ? ሲል ተናግሮናል የምናነበውን ቃል እንድናስተውለው እግዚአብሔር ይርዳን አሜን



ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment