Monday, November 30, 2015

መዝገብነ ዘኢይረክቦ ሠራቂ ሌባ የማያገኘው መዝገባችን ክፍል ሰባት

መዝገብነ ዘኢይረክቦ ሠራቂ ሌባ የማያገኘው መዝገባችን ክፍል ሰባት

THE MAGICIANS OF EGYPT  EXODUS 7 : 8 _ 25

 




መዝገብነ ዘኢይረክቦ ሠራቂ




ሌባ የማያገኘው መዝገባችን




ክፍል ሰባት




መዝገብነ ዘኢይረክቦ ሰራቂ ወኢያማስኖ ፃፄ ወቊንቊኔውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ

ትርጉም  ሌባ የማያገኘው ብል  ነቀዝ የማያበላሸውመዝገባችን ይህ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው


ምንጭ መጽሐፈ ሰዓታት )



መዝገብን በተመለከተ አሁንም ከእግዚአብሔር ቃልየምናየው እውነት አለ ሰዎች ሕይወታቸውን ለጌታለኢየሱስ በሚሰጡበት ጊዜ  የመጽሐፈ ሰዓታት ደራሲምእንደነገረን ብል ነቀዝ ሌባም ሊሰርቀው የማይችለውንመዝገባችን ኢየሱስንና በእርሱም መዝገብ ውስጥ ያለውንደኅንነት የኃጢአት ሥርየት ምሕረትና ይቅርታየዘለዓለምንም ሕይወት  ባገኙ ሰዎች ውስጥ ጌታየሚያስቀምጠው መዝገብ አለ በኦርቶዶክስ ወንጌልየገባቸው አባቶቻችን ይህንን ሁኔታ እንዲህ ሲሉያስቀምጡታል በሀብተ መንፈስቅዱስ የተገኘ ክህሎትይሉታል በመንፈስቅዱስ ሀብት የተገኘ ችሎታ ማለትንየሚያሳይ ነው በመሆኑም የእነዚህ አባቶች አባባልትክክልና መጽሐፍቅዱሳዊም ነው ስለዚህ ጉዳይመጽሐፍቅዱስን ከመሠረቱ ስንመለከት እንዲህ የሚልቃል እናገኛለን ነገር ግን የኃይሉ ታላቅነት ከእግዚአብሔርእንጂ ከእኛ እንዳይሆን ይህ መዝገብ በሸክላ ዕቃ ውስጥአለን በሁሉ እንገፋለን እንጂ አንጨነቅም፤ እናመነታለንእንጂ ተስፋ አንቆርጥም እንሰደዳለን እንጂ አንጣልም፤እንወድቃለን እንጂ አንጠፋም የኢየሱስ ሕይወት ደግሞበሥጋችን ይገለጥ ዘንድ ሁልጊዜ የኢየሱስን መሞትበሥጋችን ተሸክመን እንዞራለን 2 ቆሮንቶስ 4  7 _ 10 ይህ ቃል ታድያ እነዚህ ኦርቶዶክሳውያን አባቶችከተናገሩት ቃል ጋር የተያያዘ ነው እኛ ሸክላ ስንሆን ሽክላበሆነው በእኛ ውስጥ የተቀመጠው መዝገብ ግን በሀብተመንፈስቅዱስ የተገኘ ክህሎት ነው ስለዚህ ሰውየእግዚአብሔርን ቃል ያስተምርም ይስበክም ተአምራታዊኃይልና ፈውስ ያካሂድም ትንቢት ይናገር ይዘምርምመዝገቡ የጌታና በሀብተ መንፈስቅዱስ የተገኘ ክህሎትነው ሌላው ቀርቶ ሰዎች ምድራዊ ችሎታ ኖሮአቸውበተሰጣቸው ችሎታ የሚሰማሩት ያንን ችሎታውንእግዚአብሔር ስለሰጣቸው ነው ከእነርሱነታቸው የሆነግን ምንም ነገር የለም እነዚህ ኦርቶዶክሳውያን አባቶችበሀብተ መንፈስቅዱስ የሚመጣውን ክህሎት በሀብተመንፈስቅዱስ የሚመጣ በሰዎች ውስጥ ያለ ክህሎትወይንም በአማርኛው ችሎታ ነው ማለታቸው አንደኛውሊናገሩበት የፈለጉት ሃሳብ ከሰው ችሎታ ውጪ የሆነውንበሸክላ ዕቃ ውስጥ ያለውን መዝገብ  ሊጠቁሙን ፈልገው ሲሆን ሁለተኛው ሃሳብ ግን በ1ኛ ቆሮንቶስ 12 4 _ 11 በተጻፈው ቃል መሠረት ነገር ግን መንፈስቅዱስን መግለጥ ለእያንዳንዱ ለጥቅም ይሰጠዋል ለአንዱጥበብን መናገር በመንፈስ ይሰጠዋልና፥ ለአንዱምበዚያው መንፈስ እውቀትን መናገር ይሰጠዋል ለአንዱምበዚያው መንፈስ እምነት፥ ለአንዱም በአንዱ መንፈስየመፈወስ ስጦታ፥ ለአንዱም ተአምራትን ማድረግ፥ለአንዱም ትንቢትን መናገር፥ ለአንዱም መናፍስትንመለየት፥ ለአንዱም በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፥ለአንዱም በልሳኖች የተነገረውን መተርጎምይሰጠዋል፤ይህን ሁሉ ግን  አንዱ መንፈስ እንደሚፈቅድለእያንዳንዱ ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል አካልም አንድእንደ ሆነ ብዙም ብልቶች እንዳሉበት ነገር ግን የአካልብልቶች ሁሉ ብዙዎች ሳሉ አንድ አካል እንደ ሆኑ፥ክርስቶስ ደግሞ እንዲሁ ነው አይሁድ ብንሆን የግሪክሰዎችም ብንሆን ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆንእኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆንተጠምቀናልና ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናልይለናልና ይህንንም ሃሳብ ለመግለጽ ነው የጥንቷኦርቶዶክሳዊትና ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያንበመንፈስቅዱስ አሠራርም የምታምን ቤተክርስቲያን ናትናከዚህ የተነሳ በትርጓሜ ወንጌልዋ በሐዋርያት ሥራምዕራፍ 2 ላይ በሐዋርያት ላይ የመጣውን ርደተመንፈስቅዱስ ማለትም የመንፈስቅዱስን መውረድአስመልክቶ የተናገረችውን ለአብነት ያህል ጥቂቱንማቅረብ የፈለግሁት መጽአ ግብተ እምሰማይ ድምጽ ከመድምጸ አውሎ ነፋስ ከወደ ሰማይ እንደ አውሎ ነፋስ ያለድምጽ ነጉዶ ተሰማ አለ መንፈስቅዱስ ነው ነፋስ ረቂቅነው መንፈስቅዱስ ረቂቅ ነውና ነፋስ ኃያል ነውመንፈስቅዱስም ኃያል ነውና ነፋስ ፍሬውን ከገለባ ይለያልመንፈስቅዱስም ጻድቃንን ከኃጥአን ይለያልና ነፋስበምልዓት ሳለ አይታወቅም ባሕር ሲገስጽ ነፋስ ሲያናውጥነው እንጂ መንፈስቅዱስም በምልአት ሳለ አይታወቅምቋንቋ ሲያናግር ምሥጢር ሲያስተረጉም ነውና ነፋስመንቅሒ ነው መንፈስቅዱስም መንቅሒ ነው መንቅሒማለት የሚያነቃ ማለት ነው ነፋስ መዓዛ ያመጣልመንፈስቅዱስም መዓዛ ጸጋን ያመጣል ( የሐዋርያት ሥራምዕራፍ 2  2 ትርጓሜ ወንጌልን ይመልከቱ ) ታድያመንፈስቅዱስ የሚያነቃ ሆኖ መዓዛ ጸጋን ያመጣልምሥጢርን ያስተረጉማል ማለት በ1ኛ ቆሮንቶስ 12 ፥ 4_ 11 በተጠቀሰው ቃል መሠረት ለጥቅም የሚሰጠውንየመንፈስቅዱስን መግለጥ የሚያስታውሰን ነው ስለዚህክሂሎት እንግዲህ የሀብተ መንፈስቅዱስ ውጤት ስለሆነማለትም ችሎታ የመንፈስቅዱስ ሃብት ነውና የሚገኘውከመንፈስቅዱስ ብቻ ነው ነገር ግን አንዳንድ መድኃኒትቀማሚዎችና አዋቂ ነን ባዮች ክሂሎት ወይም ችሎታንእንሰጣለን  ትምህርት እንዲገባችሁ እናደርጋለን ንግዳችሁ  ሥራችሁ  ትዳራችሁ የሰመረ ይሆናል ከሰውበላይ ትሆናላች ማስፈራት በላያችሁ ይሆናል   ግርማሞገስንና የመሣሠሉትን እንሰጣለን  ዕድል ፈንታችሁንምበዚህ እንነግራለን እያሉ ክታብ ይጽፋሉ መድኃኒትቀምመው ይሰጣሉ ሲያስፈልግም ያጠጣሉ ያስጐነጫሉይህንን ግን የእግዚአብሔር ቃል አይደግፈውምመንፈስቅዱስም ይቃወመዋል ይህ የሰይጣን ሥራ ነውበመንፈስቅዱስ የምታምን ቤተክርስቲያን ክርስቶስንምበማመን ከእግዚአብሔር ዳግመኛ መወለድን  ያገኘችቤተክርስቲያን ይህንን ሰይጣናዊ አሠራር በጽኑትቃወማለች መጽሐፍ ሲናገር  ወንድ ልጁን ሴት ልጁን በእሳት የሚያሳልፍ፥ ምዋርተኛም፥ ሞራ ገላጭምአስማተኛም፥ መተተኛም፥ በድግምት የሚጠነቍልም፥መናፍስትንም የሚጠራ፥ ጠንቋይም፥ ሙታን ሳቢምበአንተ ዘንድ አይገኝ ይህንም የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነው፤ ስለዚህም ርኵሰት አምላክህ እግዚአብሔር ከፊትህ ያሳድዳቸዋል አንተ ግን በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ ፍጹም ሁን የምትወርሳቸው እነዚህ አሕዛብ ሞራ ገላጮችንና ምዋርተኞችን ያዳምጣሉ፤ አንተ ግን እንዲሁ ታደርግ ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር ከልክሎሃል ይላል ዘዳግም18  10 - 14 እንደገናም እርሱም፦ የሚጮኹትንናድምፃቸውን ዝቅ አድርገው የሚናገሩትን መናፍስትጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ጠይቁ ባሉአችሁ ጊዜ፥ ሕዝቡከአምላኩ መጠየቅ አይገባውምን ? ወይስ ለሕያዋን ሲሉሙታንን ይጠይቃሉን ? ወደ ሕግና ወደ ምስክር ሂዱእንዲህም ያለውን ቃል ባይናገሩ ንጋት አይበራላቸውምይለናል  ትንቢተ ኢሳይያስ 8  19 እስከ 21 በመሆኑምይህ ድርጊት የሙታን ሳቢና የጠንቋይ የመናፍስት ጠሪነትድርጊት ነው እኛ ክርስቲያኖች ጠይቁ ስንባል መጠየቅያለብን በተጻፈልን ቃል መሠረት አምላካችንን ነውእንደገናም ወደ ሕግና ወደ ምስክር ሂዱ እንዲህም ያለውንቃል ባይናገሩ ንጋት አይበራላቸውም ተብለናልና ሕጉናምስክሩ ደግሞ ንጋትን የሚያመጣልን ቃሉ ስለሆነ መሄድ የሚገባን ወደ ቃሉ ነው ወደነዚህ ሰዎች መሄድ ግን እንደ ንጉሥ ሳኦል ለጠላት ተላልፎ መሰጠት ነው ንጉሥ ሳኦል ወደመናፍስት ጠሪ ቤት በመሄዱ ለጠላት ተላልፎ የተሰጠ ነበረ  1 ሳሙኤል 28  8 _ 25  እንደ እግዚአብሔርቃል ያልሆነ  ቃሉም የሌለበትን ማንኛውንም ነገርመቀበል የለብንም መናፍስት ጠሪና ጠንቋይንእንድንጠይቅ ወደ እነርሱም እንድንሄድ መጽሐፍቅዱሳችንአይነግረንም እንደገናም ብርሃን ከጨለማ ጋር ክርስቶስከቤልሆር ጋር ኅብረትና መስማማት የለውም 2ቆሮንቶስ 6  14 _ 18 በመሆኑም እግዚአብሔርበሌለበትና በማይፈቅደው ነገር ውስጥ ገብተንና በሰይጣንውስጥ ተጥለን  የጠላት መጫወቻ ከምንሆን ክሂሎትወይም ችሎታ የመንፈስቅዱስ ሃብት ነውና ሕይወታችንንለጌታ ለኢየሱስ በመስጠት ደኅንነትን አግኝተንከመንፈስቅዱስ የሆነውን ክህሎት በየጊዜው ከራሱከባለቤቱ ከእግዚአብሔር በመቀበል በእግዚአብሔርምእርዳታ ሥር ተጠልሎ መኖር ለሁላችንም የተገባ ነገር ነውከጠንቋዮች ምክር ከሰይጣን እስራትና ትብታብ የሠራዊትጌታ እግዚአብሔር ሕዝባችንን ይፍታ ይጠብቅልን ለተጨማሪ ማስረጃ እነዚህን ጥቅሶች ያንብቡአቸውዘሌዋውያን 19  31  የማቴዎስ ወንጌል 8  16 እና17  የማቴዎስ ወንጌል 10  1  የማርቆስ ወንጌል 6  ራዕይ 18  2 የተወደዳችሁ ወገኖች  ትምህርቴንበዚህ እጠቀልላለሁ ሌባ የማይሰርቀው መዝገባችን በሚልአርዕስት ከክፍል አንድ እስከ ክፍል ሰባት የተዘጋጀውትምህርት በዚሁ ተጠቃሎአል እንግዲህ እነዚህን ከክፍልአንድ እስከ ክፍል ሰባት የተለቀቁትን ትምህርቶች በሚገባከተከታተላችኋቸው በኋላ ለሌሎችም ሊጠቀሙ ለሚችሉሁሉ ሼር እንድታደርጉ በጌታ ፍቅር ለማሳሰብ እወዳለሁጌታ ዘመናችሁን ይባርክ

የ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry

አገልጋይና ባለራዕይ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

 

No comments:

Post a Comment