Monday, March 30, 2015

005 የተወደዳችሁ ወገኖች እነዚህን ማሳሰብያዎች በተራ ቁጥር ያቀረብናቸው ናቸውና እንደሚከተለው ተመልከቷቸው 1ኛ)በዚህ ትምህርት ውስጥ ከመጽሐፍቅዱሳችን ባሻገር ይህንኑ የእግዚአብሔር ቃል አስተምሕሮታችንን የሚደግፉ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የተጻፉ ልዩ ልዩ መጽሕፍትን ለማብራርያነት ተጠቅመናል ይህንን ያደረግንበት ምክንያት እነዚህ መጻሕፍት ከመጽሐፍቅዱሳችን ጋራ በእኩልነት እንዲታዩ ለማድረግ ብለን ሳይሆን በእግዚአብሔር ቃል መሠረት የምንሰጠው አስተምሕሮ በእነዚህ መጻሕፍቶችም ውስጥ ተጠቅሰው ስላሉ ሕዝባችንን ወደ ትክክለኛው የእግዚአብሔር ቃል እውነት ለማምጣት በር ስለሚከፍቱልንና መንገድ ስለሚሆኑን ነው 2ኛ)የጥንቷ ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊትና ዓለማቀፋዊቷ ቤተክርስቲያን ትክክለኛ የእግዚአብሔር ቃል እውነት የምትከተል ለመሆኗም በእነዚህ መጻሕፍት ውስጥ የሠፈሩት ጽሑፎች ይመሠክራሉ ታድያ እነዚህ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ፍጹም ሳይጋጩ ተስማምተው የተጻፉ ጽሑፎች ካሉ እነዚህን ጽሑፎች ከእግዚአብሔር ቃል ጋር አገናኝቶ ማስተማር ተገቢያችን ነው እንላለን እንዲህ በምናስተምርበት ጊዜ ደግሞ ሕዝባችን የእግዚአብሔር ቃል የማይደግፈውን እውነት ይዞ ከሆነ ከመጽሐፍቅዱሱ ሌላ በእነዚህ በኦርቶዶክስ መጽሕፍት ውስጥ ሠፍረው ያሉ ሃሳቦች ከመጽሐፍቅዱሱ ቃል ጋር የተስማሙ በመሆናቸው ለሕዝባችን እገዛ ሆነው ሕዝባችንን ወደ ትክክለኛ የእግዚአብሔር ቃል እውነት እንዲመጣ የእግዚአብሔርንም ቃል ብቻ እንዲከተል በእርግጠኝነት ይረዱታል ለዚህ ነው ይህንን የምናደርገው 3ኛ)መጽሐፍቅዱስ በእግዚአብሔር መንፈስ የተጻፈ ብቸኛ የእግዚአብሔር መጽሐፍ እንደሆነ እናምናለን የእግዚአብሔር መጽሐፍ የሆነውን 66ቱን መጽሐፍቅዱስ ብቻ እናስተምራለን ከዚህ ውጪ የምናምነውም የምናስተምረውም ሆነ የምንሰብከው ቃል የለም 4ኛ)በዚህ ትምህርት ውስጥ የሃይማኖተ አበው መጽሐፍንም ሆነ የውዳሴ ማርያምን የጸሎት መጽሐፍ ተጠቅመናል የተጠቀምነውም በእግዚአብሔር ቃል ላለ እውነት እንደ አስረጂና ማብራርያነት የሚያገለግሉን ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የማይጋጩ እውነቶች ስላገኘን ነው ይሁን እንጂ በሃይማኖተ አበው መጽሐፍም ሆነ በውዳሴ ማርያም የጸሎት መጽሐፍ ውስጥ ያለውን የጸሎት መጽሐፍ ተጠቀምን ማለት ሃይማኖተ አበውን እንደገናም የውዳሴ ማርያምን የጸሎት መጽሐፍ ተቀበልን ማለት አይደለም በተለይ የውዳሴ ማርያም የጸሎት መጽሐፍ የሚያሳየን ውዳሴሃ ለማርያም እያለ የማርያምን ውዳሴ ነው ነገር ግን ሊወደስም ሆነ ሊመሠገን የሚገባው እግዚአብሔር ብቻ ነውና ውዳሴ ለእግዚአብሔር ብቻ መሆኑን ነው የምናምነው ሮሜ 11 ፥ 36 ፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 8 ፥ 5 እና 6 ፤ 2 ቆሮንቶስ 13 ፥ 14 ፤ ዘጸአት 20 ፥ 3 _ 6 ፤ ዮሐንስ ወንጌል 2 ፥ 5 5ኛ )በዚህ ጉዳይ ላይ የአማኞች ቤተክርስቲያንንም ብንመለከት የክርስቶስ አማኞች የሆኑት ቅዱሳን የሚያምኑት 66ቱን ቅዱሳት መጻሕፍትን የያዘውን መጽሐፍቅዱስን ብቻ ነው ነገር ግን በተለያየ ክፍለ ዘመን የተለያዩ የእግዚአብሔር ባሮች የጻፉዋቸውን መጻሕፍት ብዙ አገልጋዮች ለትምህርታቸው በዋቢነት አስረጂ በማድረግ ከመጽሐፍቅዱስ ቃል ጋር እያጣቀሱ ሲያስተምሩበት አይቻለሁ እኔም ይህንኑ መንገድ ተጠቅሜ አውቃለሁ እስካሁንም ሲሰራበት ያለና እየተሰራበት ያለም ነገር ነው ማለቴ አዲስ ነገር አይደለም ለማለት ነው እንደምሳሌ እንውሰድ ብንል ዶክተር ዓለሙ ቢፍቱ የእግዚአብሔር ባርያ የጻፉትን የቃል ኪዳን ታቦት በማደርያው ድንኳን የሚለውን መጽሐፋቸውን ብዙዎች አጣቅሰው ከእግዚአብሔር ቃል ጋራ በማገናኘት ሲያስተምሩበት ይህ ብቻ አይደለም ራሱን መጽሐፉን ሳይቀር ሲማሩት አይቻለሁ እኔም ተጠቅሜያለሁ ታድያ መጽሐፉ ከእግዚአብሔር ቃል ጋራ እስካልተጋጨ ድረስ አጣቅሰን ብናስተምርበት እኛም በግላችን መጽሐፉን ብናነበው ብናጠናው ብንማረውም ክፋት የለበትም እንደገናም የነወንጌላዊ ዶክተር ገብሩ ወልዱ የመንፈስቅዱስ ስጦታዎችና አጠቃቀማቸው የሚለው መጽሐፍ ብዙዎችን የጠቀመ ለመንፈስቅዱስ ሙላትና አሰራር ያዘጋጀ ታላቅ መጽሐፍ ነው እኔና ጓደኞቼም በዘመናችን በብዙ ተጠቅመንበታል የእግዚአብሔርንም ትልልቅ እውነቶች አግኝተንበታል ከዚህ ከከበረው የእግዚአብሔር መንፈስም ጋር በዚሁ መጽሐፍ በብዙ ተዋውቀናል ሌሎችም የእግዚአብሔር ባሮች እነ ፓስተር በቀለ ወልደ ኪዳን እነ ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን እነ ዶክተር መለሰ ወጉና የመሣሠሉት የጻፉዋቸው መጻሕፍት ለትውልድ የእውቀትን በር የከፈቱና ከዚሁ ከመጽሐፍቅዱሳችንም ጋር ትውልድን በብዙ ያስተዋዋቁ በመሆናቸው በዚህ አጋጣሚ እነዚህን የጠቀስኳቸው የእግዚአብሔር ባሮችና ሌሎችንም ያልጠቀስኳቸውን ጸሐፍት አገልጋዮቻችንን በብዙ ልባርካቸው ላመሰግናቸውም እውዳለሁ ደግሞም ዘመናቸው ሁሉ የተባረከ እንዲሆን እጸልይላቸዋለሁ ይህ በእንዲህ እንዳለ ታድያ ከመጽሐፍቅዱሳችን ሌላ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ አንዳንድ መጻሕፍትም በተመሣሣይ መልኩ ከመጽሐፍቅዱሱ ቃል ጋር በማይቃረን ሁኔታ ተጽፈው የሰፈሩልን እውነቶች አሉ በመሆኑም እነዚህን እውነቶች ሳንታክት በማንበብ እየፈለፈልን በምናገኝበት ጊዜ በዚህ ዘመን በአማኞች ቤተክርስቲያን ያሉትን አገልጋዮች ስም በጥቂቱም ቢሆን አንስቼ እንደባረኳቸው ዛሬም እንዲሁ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከመጽሐፍቅዱሱ ቃል ጋራ በልተጋጨ ወይም ባልተጣረሰ መልኩ የእግዚአብሔርን እውነት የጻፉልንን ባሮች በብዙ ልባርካቸው እወዳለሁ ይህን ያልኩት መጻሕፍቶቻቸውን ጊዜ ወስጄ አንብቤና አጥንቼ የእግዚአብሔርን እውነት ከማግኘቴ የተነሳ ነው ታድያ ካገኘናቸው ከእነዚህ የእግዚአብሔር ቃል እውነቶች የተነሳ ነው የዛሬዋን ኦርቶዶክስ ወደ ጥንተ መሠረትዋ ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነት ትመለስ የምንለው ምንም ነገር ሳናገኝ ያነበብነው ነገርም ሳይኖር እንዲሁ ይህንን አባባል ይዘን አልተነሳንም ከእኛ በፊት የነበሩት አባቶች በጽሑፋቸው ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የማይጋጨውን እውነት አስተምረውና ጽሑፋቸውንም ትተውልን ሄደውል ይህ የሠሩት መልካም ሥራም ሲዘከር ሲተረክና ሲነገር ይኖራል ስለዚህ ወገኖቼ ሃይማኖተ አበው መጽሐፍንና ሌሎችንም የኦርቶዶክስ መጽሐፍንም መጥቀስ ያስፈለገኝ ከዚህ የተነሣ ነውና እነዚህን አባቶች አሁንም እግዚአብሔር በብዙ ይባርካቸው እላለሁ ለትውልዱም የማስተላልፈው አንድና አንድ ነገር ነው ትውልድ ሆይ እምነት አለኝና በእምነቴ ጽንቼ እኖራለሁ የምትል ከሆነ መጻሕፍትን ጽፈህ ለትውልድ የማሻገር አቅም ወይም ደረጃ ላይ ባትደርስ እንኳ መጻሕፍትን ግን ሳትንቅና ሳትሳነፍ አንብብ ስል እመክራለሁ ምክንያቱም የእኛ ሕዝብ በአብዛኛው አንባቢ አይደለም ነገር ግን በብዙ አስተያየት የሚሰጥ ነው ማንበብ ሲታከልበት ግን አስተያየታችን ሙሉ ይሆናል የመንግሥቱም ሥራ እንደሚገባ ይራመዳል 6ኛ )ከዚህም ሌላ የወንጌሉን እውነትና የእግዚአብሔርንም ቃል ለሙስሊም ሕዝብ ለማድረስ እግዚአብሔር ያስነሳቸው ሰዎች ወንጌል ያልገባበት ቦታ የለምና ለሙስሊሙ ሕዝብ ወንጌሉን ከቁርዓን ጠቅሰው ነው የሚያሳዩት እኛም ለኦርቶዶክስ ሕዝብ የእግዚአብሔርን ቃል ከኦርቶዶክስ መጽሐፎች ጠቅሰን እንዲሁ እናስተምራለን 7ኛ)ሰባተኛውና የመጨረሻው መልዕክቴ ደግሞ በኦድዮ መልዕክታችንና ትምህርታችን ላይ የኦርቶዶክስ ዘማርያን መዝሙሮችን ከመዝሙሩም ጋር የተቀናጁትን ነገሮች ሁሉ አብረን ተጠቅመናል ነገር ግን አንድ እውነት የምናገረው ከዚህ በፊትም እንደተናገርኩት እነዚህን ዘማሪዎች በፍጹም አላውቃቸውም ግንኙነትም የለኝም ነገር ግን አሁንም መዝሙሮቻቸው በኢንተርኔት ላይ ሕዝብ እንዲጠቀምበትና እንዲባረክበት ተለቆ ያለ መዝሙር በመሆኑ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ሳይጋጭ በትክክል የተዘመረ መዝሙር ነውና እኔም ለትምህርቴ እንደ መግቢያና መነሻ መዝሙር አድርጌ ተጠቅሜዋለሁ ወደፊትም እጠቀምበታለሁ ይህ የእኛ ሚኒስትሪ ሰዎች የትም ቦታ ይሁኑ ፣ ከየትም ቦታ ሆነው ይዘምሩ የእግዚአብሔርን ቃል እስከዘመሩና እስካመሰገኑ ድረስ መዝሙሩንም ሆነ ቃሉን ይቀበላል አብሮም ይዘምራል ያመሰግናል ዓላማችን የእግዚአብሔርን ቃል ለሰዎች ማድረስ ነው እኛ የምንለው የእግዚአብሔር ቃል በትክክለኛውና በተጻፈው ሃሳቡ ይሰበክ ይዘመር ይመልክ ነው ሌላውን ደግሞ እንደ አስፈላጊነቱ ወደፊት የምንገልጸው ይሆናል እንግዲህ በዚህ ተከታታይ በሆነው በኦድዮ ትምህርት ተባረኩበት ተጠቀሙበት ወደፊትም ሊጠቀሙ ለሚፈልጉ ሰዎች አስተላልፉት እያልኩ እሰናበታችኋለሁ መልካም የበረከት ጊዜ ይሁንላችሁ አሜን

Sunday, March 29, 2015

003

My Slideshow

001 የተወደዳችሁ ወገኖች እነዚህን ማሳሰብያዎች በተራ ቁጥር ያቀረብናቸው ናቸውና እንደሚከተለው ተመልከቷቸው 1ኛ)በዚህ ትምህርት ውስጥ ከመጽሐፍቅዱሳችን ባሻገር ይህንኑ የእግዚአብሔር ቃል አስተምሕሮታችንን የሚደግፉ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የተጻፉ ልዩ ልዩ መጽሕፍትን ለማብራርያነት ተጠቅመናል ይህንን ያደረግንበት ምክንያት እነዚህ መጻሕፍት ከመጽሐፍቅዱሳችን ጋራ በእኩልነት እንዲታዩ ለማድረግ ብለን ሳይሆን በእግዚአብሔር ቃል መሠረት የምንሰጠው አስተምሕሮ በእነዚህ መጻሕፍቶችም ውስጥ ተጠቅሰው ስላሉ ሕዝባችንን ወደ ትክክለኛው የእግዚአብሔር ቃል እውነት ለማምጣት በር ስለሚከፍቱልንና መንገድ ስለሚሆኑን ነው 2ኛ)የጥንቷ ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊትና ዓለማቀፋዊቷ ቤተክርስቲያን ትክክለኛ የእግዚአብሔር ቃል እውነት የምትከተል ለመሆኗም በእነዚህ መጻሕፍት ውስጥ የሠፈሩት ጽሑፎች ይመሠክራሉ ታድያ እነዚህ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ፍጹም ሳይጋጩ ተስማምተው የተጻፉ ጽሑፎች ካሉ እነዚህን ጽሑፎች ከእግዚአብሔር ቃል ጋር አገናኝቶ ማስተማር ተገቢያችን ነው እንላለን እንዲህ በምናስተምርበት ጊዜ ደግሞ ሕዝባችን የእግዚአብሔር ቃል የማይደግፈውን እውነት ይዞ ከሆነ ከመጽሐፍቅዱሱ ሌላ በእነዚህ በኦርቶዶክስ መጽሕፍት ውስጥ ሠፍረው ያሉ ሃሳቦች ከመጽሐፍቅዱሱ ቃል ጋር የተስማሙ በመሆናቸው ለሕዝባችን እገዛ ሆነው ሕዝባችንን ወደ ትክክለኛ የእግዚአብሔር ቃል እውነት እንዲመጣ የእግዚአብሔርንም ቃል ብቻ እንዲከተል በእርግጠኝነት ይረዱታል ለዚህ ነው ይህንን የምናደርገው 3ኛ)መጽሐፍቅዱስ በእግዚአብሔር መንፈስ የተጻፈ ብቸኛ የእግዚአብሔር መጽሐፍ እንደሆነ እናምናለን የእግዚአብሔር መጽሐፍ የሆነውን 66ቱን መጽሐፍቅዱስ ብቻ እናስተምራለን ከዚህ ውጪ የምናምነውም የምናስተምረውም ሆነ የምንሰብከው ቃል የለም 4ኛ)በዚህ ትምህርት ውስጥ የሃይማኖተ አበው መጽሐፍንም ሆነ የውዳሴ ማርያምን የጸሎት መጽሐፍ ተጠቅመናል የተጠቀምነውም በእግዚአብሔር ቃል ላለ እውነት እንደ አስረጂና ማብራርያነት የሚያገለግሉን ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የማይጋጩ እውነቶች ስላገኘን ነው ይሁን እንጂ በሃይማኖተ አበው መጽሐፍም ሆነ በውዳሴ ማርያም የጸሎት መጽሐፍ ውስጥ ያለውን የጸሎት መጽሐፍ ተጠቀምን ማለት ሃይማኖተ አበውን እንደገናም የውዳሴ ማርያምን የጸሎት መጽሐፍ ተቀበልን ማለት አይደለም በተለይ የውዳሴ ማርያም የጸሎት መጽሐፍ የሚያሳየን ውዳሴሃ ለማርያም እያለ የማርያምን ውዳሴ ነው ነገር ግን ሊወደስም ሆነ ሊመሠገን የሚገባው እግዚአብሔር ብቻ ነውና ውዳሴ ለእግዚአብሔር ብቻ መሆኑን ነው የምናምነው ሮሜ 11 ፥ 36 ፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 8 ፥ 5 እና 6 ፤ 2 ቆሮንቶስ 13 ፥ 14 ፤ ዘጸአት 20 ፥ 3 _ 6 ፤ ዮሐንስ ወንጌል 2 ፥ 5 5ኛ )በዚህ ጉዳይ ላይ የአማኞች ቤተክርስቲያንንም ብንመለከት የክርስቶስ አማኞች የሆኑት ቅዱሳን የሚያምኑት 66ቱን ቅዱሳት መጻሕፍትን የያዘውን መጽሐፍቅዱስን ብቻ ነው ነገር ግን በተለያየ ክፍለ ዘመን የተለያዩ የእግዚአብሔር ባሮች የጻፉዋቸውን መጻሕፍት ብዙ አገልጋዮች ለትምህርታቸው በዋቢነት አስረጂ በማድረግ ከመጽሐፍቅዱስ ቃል ጋር እያጣቀሱ ሲያስተምሩበት አይቻለሁ እኔም ይህንኑ መንገድ ተጠቅሜ አውቃለሁ እስካሁንም ሲሰራበት ያለና እየተሰራበት ያለም ነገር ነው ማለቴ አዲስ ነገር አይደለም ለማለት ነው እንደምሳሌ እንውሰድ ብንል ዶክተር ዓለሙ ቢፍቱ የእግዚአብሔር ባርያ የጻፉትን የቃል ኪዳን ታቦት በማደርያው ድንኳን የሚለውን መጽሐፋቸውን ብዙዎች አጣቅሰው ከእግዚአብሔር ቃል ጋራ በማገናኘት ሲያስተምሩበት ይህ ብቻ አይደለም ራሱን መጽሐፉን ሳይቀር ሲማሩት አይቻለሁ እኔም ተጠቅሜያለሁ ታድያ መጽሐፉ ከእግዚአብሔር ቃል ጋራ እስካልተጋጨ ድረስ አጣቅሰን ብናስተምርበት እኛም በግላችን መጽሐፉን ብናነበው ብናጠናው ብንማረውም ክፋት የለበትም እንደገናም የነወንጌላዊ ዶክተር ገብሩ ወልዱ የመንፈስቅዱስ ስጦታዎችና አጠቃቀማቸው የሚለው መጽሐፍ ብዙዎችን የጠቀመ ለመንፈስቅዱስ ሙላትና አሰራር ያዘጋጀ ታላቅ መጽሐፍ ነው እኔና ጓደኞቼም በዘመናችን በብዙ ተጠቅመንበታል የእግዚአብሔርንም ትልልቅ እውነቶች አግኝተንበታል ከዚህ ከከበረው የእግዚአብሔር መንፈስም ጋር በዚሁ መጽሐፍ በብዙ ተዋውቀናል ሌሎችም የእግዚአብሔር ባሮች እነ ፓስተር በቀለ ወልደ ኪዳን እነ ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን እነ ዶክተር መለሰ ወጉና የመሣሠሉት የጻፉዋቸው መጻሕፍት ለትውልድ የእውቀትን በር የከፈቱና ከዚሁ ከመጽሐፍቅዱሳችንም ጋር ትውልድን በብዙ ያስተዋዋቁ በመሆናቸው በዚህ አጋጣሚ እነዚህን የጠቀስኳቸው የእግዚአብሔር ባሮችና ሌሎችንም ያልጠቀስኳቸውን ጸሐፍት አገልጋዮቻችንን በብዙ ልባርካቸው ላመሰግናቸውም እውዳለሁ ደግሞም ዘመናቸው ሁሉ የተባረከ እንዲሆን እጸልይላቸዋለሁ ይህ በእንዲህ እንዳለ ታድያ ከመጽሐፍቅዱሳችን ሌላ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ አንዳንድ መጻሕፍትም በተመሣሣይ መልኩ ከመጽሐፍቅዱሱ ቃል ጋር በማይቃረን ሁኔታ ተጽፈው የሰፈሩልን እውነቶች አሉ በመሆኑም እነዚህን እውነቶች ሳንታክት በማንበብ እየፈለፈልን በምናገኝበት ጊዜ በዚህ ዘመን በአማኞች ቤተክርስቲያን ያሉትን አገልጋዮች ስም በጥቂቱም ቢሆን አንስቼ እንደባረኳቸው ዛሬም እንዲሁ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከመጽሐፍቅዱሱ ቃል ጋራ በልተጋጨ ወይም ባልተጣረሰ መልኩ የእግዚአብሔርን እውነት የጻፉልንን ባሮች በብዙ ልባርካቸው እወዳለሁ ይህን ያልኩት መጻሕፍቶቻቸውን ጊዜ ወስጄ አንብቤና አጥንቼ የእግዚአብሔርን እውነት ከማግኘቴ የተነሳ ነው ታድያ ካገኘናቸው ከእነዚህ የእግዚአብሔር ቃል እውነቶች የተነሳ ነው የዛሬዋን ኦርቶዶክስ ወደ ጥንተ መሠረትዋ ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነት ትመለስ የምንለው ምንም ነገር ሳናገኝ ያነበብነው ነገርም ሳይኖር እንዲሁ ይህንን አባባል ይዘን አልተነሳንም ከእኛ በፊት የነበሩት አባቶች በጽሑፋቸው ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የማይጋጨውን እውነት አስተምረውና ጽሑፋቸውንም ትተውልን ሄደውል ይህ የሠሩት መልካም ሥራም ሲዘከር ሲተረክና ሲነገር ይኖራል ስለዚህ ወገኖቼ ሃይማኖተ አበው መጽሐፍንና ሌሎችንም የኦርቶዶክስ መጽሐፍንም መጥቀስ ያስፈለገኝ ከዚህ የተነሣ ነውና እነዚህን አባቶች አሁንም እግዚአብሔር በብዙ ይባርካቸው እላለሁ ለትውልዱም የማስተላልፈው አንድና አንድ ነገር ነው ትውልድ ሆይ እምነት አለኝና በእምነቴ ጽንቼ እኖራለሁ የምትል ከሆነ መጻሕፍትን ጽፈህ ለትውልድ የማሻገር አቅም ወይም ደረጃ ላይ ባትደርስ እንኳ መጻሕፍትን ግን ሳትንቅና ሳትሳነፍ አንብብ ስል እመክራለሁ ምክንያቱም የእኛ ሕዝብ በአብዛኛው አንባቢ አይደለም ነገር ግን በብዙ አስተያየት የሚሰጥ ነው ማንበብ ሲታከልበት ግን አስተያየታችን ሙሉ ይሆናል የመንግሥቱም ሥራ እንደሚገባ ይራመዳል 6ኛ )ከዚህም ሌላ የወንጌሉን እውነትና የእግዚአብሔርንም ቃል ለሙስሊም ሕዝብ ለማድረስ እግዚአብሔር ያስነሳቸው ሰዎች ወንጌል ያልገባበት ቦታ የለምና ለሙስሊሙ ሕዝብ ወንጌሉን ከቁርዓን ጠቅሰው ነው የሚያሳዩት እኛም ለኦርቶዶክስ ሕዝብ የእግዚአብሔርን ቃል ከኦርቶዶክስ መጽሐፎች ጠቅሰን እንዲሁ እናስተምራለን 7ኛ)ሰባተኛውና የመጨረሻው መልዕክቴ ደግሞ በኦድዮ መልዕክታችንና ትምህርታችን ላይ የኦርቶዶክስ ዘማርያን መዝሙሮችን ከመዝሙሩም ጋር የተቀናጁትን ነገሮች ሁሉ አብረን ተጠቅመናል ነገር ግን አንድ እውነት የምናገረው ከዚህ በፊትም እንደተናገርኩት እነዚህን ዘማሪዎች በፍጹም አላውቃቸውም ግንኙነትም የለኝም ነገር ግን አሁንም መዝሙሮቻቸው በኢንተርኔት ላይ ሕዝብ እንዲጠቀምበትና እንዲባረክበት ተለቆ ያለ መዝሙር በመሆኑ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ሳይጋጭ በትክክል የተዘመረ መዝሙር ነውና እኔም ለትምህርቴ እንደ መግቢያና መነሻ መዝሙር አድርጌ ተጠቅሜዋለሁ ወደፊትም እጠቀምበታለሁ ይህ የእኛ ሚኒስትሪ ሰዎች የትም ቦታ ይሁኑ ፣ ከየትም ቦታ ሆነው ይዘምሩ የእግዚአብሔርን ቃል እስከዘመሩና እስካመሰገኑ ድረስ መዝሙሩንም ሆነ ቃሉን ይቀበላል አብሮም ይዘምራል ያመሰግናል ዓላማችን የእግዚአብሔርን ቃል ለሰዎች ማድረስ ነው እኛ የምንለው የእግዚአብሔር ቃል በትክክለኛውና በተጻፈው ሃሳቡ ይሰበክ ይዘመር ይመልክ ነው ሌላውን ደግሞ እንደ አስፈላጊነቱ ወደፊት የምንገልጸው ይሆናል እንግዲህ በዚህ ተከታታይ በሆነው በኦድዮ ትምህርት ተባረኩበት ተጠቀሙበት ወደፊትም ሊጠቀሙ ለሚፈልጉ ሰዎች አስተላልፉት እያልኩ እሰናበታችኋለሁ መልካም የበረከት ጊዜ ይሁንላችሁ አሜን

Sunday, March 22, 2015

የተወደዳችሁ ቅዱሳን ወገኖች ይህ በሥዕል የተደገፈና በኦድዮ የተላለፈ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ኦርቶዶክስን ወደ ጥንተ መሠረቷ ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነትና ወደ ወንጌሉ ቃል እንድትመለስ የተላለፈ ወደፊትም በዚህ መልኩ የሚተላለፍ መልዕክትና ትምህርትም ያለበት አገልግሎት ነው እናንተም ይህንን ቃል እየሰማችሁ ለሌሎች እንድታሰሙ ይሁን ልንላችሁ እንወዳለን ይህን የመሠሉ ሌሎችንም ትምህርቶች መከታተል ከወደዳችሁ በዚህ ዌብሳይት ገብታችሁ መከታተል የምትችሉ መሆናችሁን ከወዲሁ ላሳስብ እወዳለሁ የዌብሳይቴ አድራሻ http//www.joshua.yonasgetaneh.com የክፍል ሦስት ተከታይ ክፍል አራት ክላሲካል መዝሙር ነው ይህንን መዝሙር በማዳመጥ የእግዚአብሔርን በረከት ይካፈሉ https://youtu.be/rGbct9EZc3Y http://www.facebook.com/yonas.aseaw.39 yonasgetaneh@ymail.com

የተወደዳችሁ ቅዱሳን ወገኖች ይህ በሥዕል የተደገፈና በኦድዮ የተላለፈ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ኦርቶዶክስን ወደ ጥንተ መሠረቷ ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነትና ወደ ወንጌሉ ቃል እንድትመለስ የተላለፈ ወደፊትም በዚህ መልኩ የሚተላለፍ መልዕክትና ትምህርትም ያለበት አገልግሎት ነው እናንተም ይህንን ቃል እየሰማችሁ ለሌሎች እንድታሰሙ ይሁን ልንላችሁ እንወዳለን ይህን የመሠሉ ሌሎችንም ትምህርቶች መከታተል ከወደዳችሁ በዚህ ዌብሳይት ገብታችሁ መከታተል የምትችሉ መሆናችሁን ከወዲሁ ላሳስብ እወዳለሁ የዌብሳይቴ አድራሻ http//www.joshua.yonasgetaneh.com የክፍል ሦስት ተከታይ ክፍል አራት ክላሲካል መዝሙር ነው ይህንን መዝሙር በማዳመጥ የእግዚአብሔርን በረከት ይካፈሉ ትምህርት https://youtu.be/rGbct9EZc3Y http://www.facebook.com/yonas.aseaw.39 yonasgetaneh@ymail.com

Saturday, March 21, 2015

yemel'kt res haymanotekie ahywetekie 6የተወደዳችሁ ቅዱሳን ወገኖች ይህ በሥዕል የተደገፈና በኦድዮ የተላለፈ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ኦርቶዶክስን ወደ ጥንተ መሠረቷ ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነትና ወደ ወንጌሉ ቃል እንድትመለስ የተላለፈ ወደፊትም በዚህ መልኩ የሚተላለፍ መልዕክትና ትምህርትም ያለበት አገልግሎት ነው እናንተም ይህንን ቃል እየሰማችሁ ለሌሎች እንድታሰሙ ይሁን ልንላችሁ እንወዳለን ይህን የመሠሉ ሌሎችንም ትምህርቶች መከታተል ከወደዳችሁ በዚህ ዌብሳይት ገብታችሁ መከታተል የምትችሉ መሆናችሁን ከወዲሁ ላሳስብ እወዳለሁ የዌብሳይቴ አድራሻ http//www.joshua.yonasgetaneh.com የክፍል ሁለት ተከታይ ክፍል ሦስት ትምህርት

የተወደዳችሁ ቅዱሳን ወገኖች ይህ በሥዕል የተደገፈና በኦድዮ የተላለፈ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ኦርቶዶክስን ወደ ጥንተ መሠረቷ ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነትና ወደ ወንጌሉ ቃል እንድትመለስ የተላለፈ ወደፊትም በዚህ መልኩ የሚተላለፍ መልዕክትና ትምህርትም ያለበት አገልግሎት ነው እናንተም ይህንን ቃል እየሰማችሁ ለሌሎች እንድታሰሙ ይሁን ልንላችሁ እንወዳለን ይህን የመሠሉ ሌሎችንም ትምህርቶች መከታተል ከወደዳችሁ በዚህ ዌብሳይት ገብታችሁ መከታተል የምትችሉ መሆናችሁን ከወዲሁ ላሳስብ እወዳለሁ የዌብሳይቴ አድራሻ http//www.joshua.yonasgetaneh.com የክፍል አንድ ተከታይ ክፍል ሁለት ትምህርት

የተወደዳችሁ ቅዱሳን ወገኖች ይህ በሥዕል የተደገፈና በኦድዮ የተላለፈ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ኦርቶዶክስን ወደ ጥንተ መሠረቷ ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነትና ወደ ወንጌሉ ቃል እንድትመለስ የተላለፈ ወደፊትም በዚህ መልኩ የሚተላለፍ መልዕክትና ትምህርትም ያለበት አገልግሎት ነው እናንተም ይህንን ቃል እየሰማችሁ ለሌሎች እንድታሰሙ ይሁን ልንላችሁ እንወዳለን ይህን የመሠሉ ሌሎችንም ትምህርቶች መከታተል ከወደዳችሁ በዚህ ዌብሳይት ገብታችሁ መከታተል የምትችሉ መሆናችሁን ከወዲሁ ላሳስብ እወዳለሁ የዌብሳይቴ አድራሻ http//www.joshua.yonasgetaneh.com

Wednesday, March 18, 2015

በር መሠማርያ የሕይወት መገኛ የሚያድን ምግባችን የሚፈርድልን መጠጣችን ነው ሃይማኖተ አበው እልመስጦግያ ምዕራፍ 3

ይህ   Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry  ሥር እየተዘጋጀ የሚቀርብላችሁ ትምህርት ነው


ክፍል ሁለት


ጥንተ አንቀጽ መካነ ሕይወት ፈውስነ ሲሳይነ ስቴነ መኮንንነ


ትርጉም በር መሠማርያ የሕይወት መገኛ የሚያድን ምግባችን
            የሚፈርድልን መጠጣችን ነው

               ሃይማኖተ አበው

             
               እልመስጦግያ

               ምዕራፍ 3





ኢየሱስም ደግሞ አላቸው እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እኔ የበጎች በር ነኝ
ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦችና ወንበዴዎች ናቸው፤ ዳሩ ግን በጎቹ አልሰሙአቸውም
በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማርያም ያገኛል
         
           
         የዮሐንስ ወንጌል 10 1 _ 15 7 _ 10





ይህ የክፍል ሁለት መልዕክት ነው በክፍል አንድ ትምህርታችን ላይ ኢየሱስ የበጎች በር በመሆኑ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማርያም ያገኛል በማለት ነግሮናል በመሆኑም እርሱ መንገድና እውነት ሕይወትም ስለሆነ  የዮሐንስ ወንጌል 14 6 እርሱ ሕይወት መሆኑን አውቆ በእርሱ መንገድ ላይ የመጣ ሁሉ እርሱ ወደ እውነትና ወደ ሕይወት የሚወስድ መንገድ ብቻ ሳይሆን የበጎችም በር ነውና በዚህ በር በሆነው በእርሱ በኩል ይገባል ገብቶም አይቀርም ይድናል ይወጣልም መሠማርያም ያገኛል ስንል ዛሬም ይህን የቃሉን እውነት አምኖ በዚህ መንገድ ላይ የመጣ መጥቶም ሳይቀር በዚህ የበጎች በር በኩል ገብቶ በበሩ የገባ መዳኛና መሰማርያም የማግኘት ዕድሉም ለእርሱ እንደሆነ በሰፊው በቃሉ ተማምረናል ክርስቶስ ኢየሱስ የበጎች በር መሆኑን አውቆ በበሩ የገባ የሚድን ነውና የሃይማኖተ አበው መጽሐፍ እንደነገረን እርሱ የሕይወት መገኛ ነው ከዚህ ጌታ ጋር በበሩ በኩል ገብቶ ላልተገናኘ ግን ሕይወት የሚገኝ አይሆንም መዳንም የለም እንግዲህ የሃይማኖተ አበው ጸሐፊ እንዳለው ክርስቶስ ኢየሱስ የበጎች በር መሠማርያ የሚያድን ብቻ ሳይሆን ምግባችን የሚፈርድልን መጠጣችን መሆኑን ይነግረናል ታድያ ወደ ጌታ መጥተን በበሩ ስንገባ የሕይወት መገኛችን ሆኖ የሚያድነን መሠማርያም የሚሰጠን ብቻ ሳይሆን ምግባችን የሚሰጠን እንደ አስፈላጊነቱም የሚፈርድልን ጌታ ነው ስለዚህ ወደ ክርስቶስ የመጣ ክርስቶስ ኢየሱስ ለእርሱ ሁሉ በሁሉ ነው ወደ ጌታ መጥተን እርሱ በር ነውና በበሩ ገብተን ድነንና መሠማርያ አግኝተን የምንቀር ብቻ አይደለንም እንድናድግ የሚያስችለንን መንፈሳዊ መብልንና መንፈሳዊ መጠጥን ከዚሁ ጌታ እናገኛለን በዮሐንስ ወንጌል 6 54 _ 58 ላይ ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ ሕያው አብ እንደ ላከኝ እኔም ከአብ የተነሣ ሕያው እንደምሆን፥ እንዲሁ የሚበላኝ ደግሞ ከእኔ የተነሣ ሕያው ይሆናል ከሰማይ የወረደ እንጀራ ይህ ነው፤ አባቶቻችሁ መና በልተው እንደ ሞቱ አይደለም፤ ይህን እንጀራ የሚበላ ለዘላለም ይኖራል ጌታችን ኢየሱስ እዚህ ጋር  ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ ሕያው አብ እንደ ላከኝ እኔም ከአብ የተነሣ ሕያው እንደምሆን፥ እንዲሁ የሚበላኝ ደግሞ ከእኔ የተነሣ ሕያው ይሆናል ብሎ ሲናገር በመንፈሳዊ ቃል ሊገልጸው የፈለገው ነገር አለ እርሱም በዚሁ በዮሐንስ ወንጌል 6 63 ላይ ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው በማለት የሕይወት እንጀራ መንፈስ ያለበት ቃሉ እንደሆነ ይናገረናል ቃሉን ስንበላ እርሱ ሕያው እንደሆነ ሁሉ እኛም ከእርሱ የተነሳ ሕያዋን እንሆናለን ሕያውነት ሁልጊዜ ቃሉን ከመብላት የተነሳ የሚመጣ ነው ኢየሱስ ከሰማይ የወረደ  የሕይወት እንጀራ ሆኖ ቃሉን ሰጥቶናል ራሱንም ሰጥቶናል ስለዚህ ሕያውነታችን እርሱን በመብላትና እርሱን በመጠጣት የበዛ ይሆናል ቃሉን ዕለት ዕለት በግላችን በምናጠናው የመጽሐፍቅዱስ ጥናት በቤተክርስቲያን ባሉን አገልጋዮቻችን በሕብረት ባላ የእርስ በእርስ የመጽሐፍቅዱስ ጥናት እና በመሳሰሉት እንመገባለን ሕያዋንም እንሆናለን ከዚህም ባሻገር በ1ኛ ቆሮንቶስ 11 23 _ 31 በተጻፈው ቃል መሠረት የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ሕብረት ያለው አይደለምን ? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን ? አንድ እንጀራ ስለሆነ እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና እያለ ይናገራል ይህ የሚያመለክተን የጌታን እራት በምንወስድ ጊዜ የሚሆነውን አንድነትና የበረከት መካፈል ነው የምንባርከው የበረከት ጽዋና የምንቆርሰው እንጀራ ከክርስቶስ ጋር ኅብረትን የሚሰጠን ነው እንደገናም እርስ በእርሳችን ሳይቀር ኅብረታችንንና አንድ ሥጋ መሆናችንን ሳይቀር የሚያሳይ ነው ነገር ግን በዚህ ውስጥ የጌታን ጽዋና የአጋንንትን ጽዋ በአንድ ላይ ልናስኬድ አንችልምና ለይተን ልናውቅ እኛም ከጌታ ጋር ብቻ መሆናችንን በማወቅ ኅብረታችንን የጌታን ጽዋና እንጀራውንም በመቁረስ በጽኑ ከእርሱ ጋር ልናረጋግጥ ይገባል ስለዚህ ቃሉን መብላታችን የጌታን ጽዋና እንጀራውንም መቁረሳችን እርሱ አንድ ነውና አንዱን ጽዋ ስንጠጣ አንዱንም እንጀራ ስንቆርስ ከአንዱ ጌታ ጋር ኅብረት ማድረጋችንንና አንድነታችንንም ጭምር የሚገልጽ ሲሆን የእርስ በእርስ አንድነታችንንም ይህ የምንካፈለው ነገር የሚጠብቅልንና የሚያሳየን ነው ምስጢሩ እንግዲህ በአጭሩ ይህንን ሲመስል የቆላስያስ መጽሐፍ ደግሞ ይህንን እውነት ይበልጥ ያጐላዋል ቆላስያስ 2 16 _ 20 ላይ እንግዲህ በመብል ወይም በመጠጥ ወይም ስለ በዓል ወይም ስለ ወር መባቻ ወይም ስለ ሰንበት ማንም አይፍረድባችሁ እነዚህ ሊመጡ ያሉት ነገሮች ጥላ ናቸውና፥ አካሉ ግን የክርስቶስ ነው ትሕትናንና የመላእክትን አምልኮ እየወደደ፥ ባላየውም ያለ ፈቃድ እየገባ፥ በሥጋዊም አእምሮ በከንቱ እየታበየ ማንም አይፍረድባችሁ እንደዚህ ያለ ሰው ራስ ወደሚሆነው አይጠጋም፥ ከእርሱም አካል ሁሉ በጅማትና በማሰሪያ ምግብን እየተቀበለ እየተጋጠመም እግዚአብሔር በሚሰጠው ማደግ ያድጋል ይለናል መንፈሳዊ ዕድገትን የሚሰጥም ሆነ የሚያሳድግ እግዚአብሔር ብቻ ነው በበሩ ገብተን መሠማርያ ስናገኝ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ከእግዚአብሔር ይሰጡናል መንገድ እና በር ሆኖን በበሩ ያስገባን ኢየሱስ ያዳነን የሚያወጣን የሚያገባን የሚያሰማራን ብቻ ሳይሆን የሕይወት እንጀራ ነውና ቃሉን ሰጥቶ ሕያውነታችንን የሚያበዛ የአካሉ ብልት አድርጎም እርሱ በሚሰጠን ዕድገት የሚያሳድገንም ነው ሐዋርያው ጳውሎስ ስለዚህ ጉዳይ ሲናገር እኔ ተከልሁ አጵሎስም አጠጣ ነገር ግን እግዚአብሔር ያሳድግ ነበር እንግዲያስ የሚያሳድግ እግዚአብሔር እንጂ የሚተክል ቢሆን ወይም የሚያጠጣ ቢሆን አንዳች አይደለም አለን 1 ቆሮንቶስ 3 6 እና 7 በመሆኑም መንገድና እውነት ሕይወትም ኢየሱስ ነውና የዮሐንስ ወንጌል 14 6 መንገዱን አውቀን የበጐች በር በሆነው በኢየሱስ በኩል በበሩ ስንገባ መሠማራቱ ሕያውነታችንን ማብዛቱ የአካሉ ብልት ሆነንና ተገጥመን እግዚአብሔር በሚሰጠን ዕድገት ማደጉ ሁሉ እኛን የሚጠብቅ ነገር ይሆናል ማለት ነው በመሆኑም እነዚህ ነገሮች በሕይወታችን እንዲጠናቀቁና እኛም ሙሉ ሰው እንድንሆን ኤፌሶን 4 12 እና 13 መንገድ እውነትና ሕይወት በሆነልን በኢየሱስ በኩል እንመጣ በበሩም በኩል እንግባ ያን ጊዜ የዘረዘርኳቸው እነዚህ  ነገሮች በሙሉ በሕይወታችን ይሆናሉ አለበለዚያ ግን መንገድና እውነት ሕይወትም የሆነን እንደገናም ወደ መንግሥቱ መግቢያ በር ሆኖን የሚያድነን የሚያወጣንና የሚያገባን መሠማርያም የሚሆነን የሕይወት እንጀራ የሆነውን ቃሉ አብልቶ ሕያውነታችንን የሚያበዛ አካሉና የአካሉ ብልትም አድርጎ እርሱ በሚሰጠን ማደግ የሚያሳድገን ኢየሱስ እያለልን እንደገና ኢየሱስ ለእኛ እንዳልመጣልን አድርገን እና ጥላ ወደሆነው አገልግሎት ተመልሰን በሰንበት  በወር መባቻ በበዓላት ሕይወትና አክብሮት ተይዘን ስንፈርድ  ስንፈራረድ በኢየሱስ የተሰጠን አሁን ላይ ያለው የመዳን ቀን ያመልጠናል  ሕይወትም   ይጨልምብናል ማለት በሚያድነው ጌታ በኢየሱስ ሳንድን እናንቀላፋለን የሥጋን ሞት እንሞታለን ኢየሱስ የሌለው ሰው ደግሞ ሞትን በሥጋ ሞት ብቻ የሚገላገለው ሳይሆን ከሥጋ ሞት ባሻገር ዘላለማዊ ሞት አለና በዚያም ለዘላለም የሚሰቃይበት ነው ስለዚህ ማምለጫው የመዳን ቀን አሁን ስለሆነ 2 ቆሮንቶስ 6 2 ቶሎ ብለን ቀን ሳንሰጥ አሁን ላይ ባለው ሕይወታችን ኢየሱስን መቀበል ነው ኢየሱስ ሆይ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ስትሆን ጌታዬና አዳኜ ነህ እቀበልሃለሁ ሕይወቴንም ላንተ እሰጣለሁ ስንል መወሰንና መቀበል አለብን ያን ጊዜ ከሞት ወደ ሕይወት እንሻገራለን ከሰይጣን መንግሥት እናመልጣለን የእግዚአብሔርም  ልጆች እንሆናለን   ስማችንም በሕይወት መዝገብ ይጻፋል እግዚአብሔር በምናነበው ቃል ወደዚህ ሕይወት እንድንመጣ ይርዳን ይባርከንም

ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን



ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ