Monday, March 9, 2015

ኢንትገዘር እንከ ከመ አይሁድ ነአምር ከመ መጽአ ዘይፌጽም ኦሪተ ወነቢያተ እንግዲህ እንደ አይሁድ አንገዘር አሪትና ነቢያትን የሚፈጽም እንደመጣ እናውቃለን ሃይማኖተ አበው አመክንዮ ዘሐዋርያት ሄሬኔዎስ ምዕራፍ ሰባት

ይህ Joshua Breakthrough Renewal Teaching and Preaching Ministry
ስር  እየተዘጋጀ የሚቀርብላችሁ ትምህርት ነው

ኢንትገዘር እንከ ከመ አይሁድ ነአምር ከመ መጽአ ዘይፌጽም ኦሪተ ወነቢያተ

እንግዲህ እንደ አይሁድ አንገዘር አሪትና ነቢያትን የሚፈጽም እንደመጣ እናውቃለን

ሃይማኖተ አበው

አመክንዮ ዘሐዋርያት

ሄሬኔዎስ

ምዕራፍ ሰባት

የተወደዳችሁ ቅዱሳን ባለፈው የኢየሱስ ክርስቶስን ሊቀካህንነት በተነጋገርንበት ሃሳብ ውስጥ ሃይማኖተ አበው የተባለው መጽሐፍና አመክንዮ ዘሐዋርያት የሚለው ምን እንደሆነ ባጭሩ ተመልክተነዋል በተለይ ይህ አመክንዮ ዘሐዋርያት የእናት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የእምነት መግለጫ ነው በዚህ የእምነት መግለጫዋ አሁንም እንግዲህ እንደ አይሁድ አንገዘር አሪትና ነቢያትን የሚፈጽም እንደመጣ እናውቃለን በማለት በክፍሉ ተጽፎ እናገኛለን  ይህ ሃሳብ የሚያስተምረን ኦሪትና ነቢያትን በመፈጸም በጸጋው መዳንን ያመጣልን የእግዚአብሔር ልጅ ስላለን እንግዲህ ወደ ኋላ ተመልሰን እንደ አይሁድ ግዝረትን አንለቅም እያልን እኛም ስንገረዝ እንዳንገኝ የሚጠቁመን ነው የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ኦሪትና ነቢያትን ሊፈጽማቸው የመጣው እኛን በጸጋው ለማዳን ነው ምክንያቱም በኤፌሶን 2 8 ላይ ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም ይለናል ቃሉ በሥራ መዳን ቢሆን ኖሮ ጸጋ የሚባለው ነገር በፍጹም ሳያስፈልገን ሕግን በመጠበቅ ብቻ እንድን ነበር ማለት ነው ሕግን በመጠበቅ ደግሞ የምንድን ከሆነ በእግዚአብሔር ቃልም ሆነ በአመክንዮ ዘሐዋርያት  ላይ ተጽፎ እንደምናገኘው ኢየሱስ ክርስቶስ  ሕግንና ነቢያትን ሊፈጽማቸው አይመጣም ነበር ጌታችን ኢየሱስ እንደውም ያለው ኢይምሰልክሙ ዘመጻእኩ እስዓሮሙ ለኦሪት ወለነቢያት ዘእንበለ ዳዕሙ ከመ እፈጽሞሙ ነው ትርጉም እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም በማለት ነው የተናገረው የማቴዎስ ወንጌል 5 17 ለዚህም ነው ይህንን ቃል ተንተርሶ የእናት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የእምነት መግለጫ ሕግን የምንጠብቅ በመምሰል እንደ አይሁድ አንገዘር ኦሪትና ነቢያትን የሚፈጽማቸው እንደመጣ እናውቃለን በማለት በግልጽ የነገረን ታድያ ይሄ እውነት እንደ እግዚአብሔር ቃል እናት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በእምነት መግለጫዋ ላይ እምነቴና የሃይማኖቴም አንቀጽ በመሆኑ አስተምረዋለሁ እሰብከዋለሁ ብላ በጽሑፍዋ  ላይ ሳይቀር አስፍራልን ሳለ እኛ ግን ይሄ እንደ እግዚአብሔር ቃል የተጻፈው እውነትና የእምነቱም መግለጫ አልታይ ብሎን እንደገናም እምቢ  አሻፈረኝ ብለን እንደ አይሁድ ግዝረትን በመቀበልና በመገረዝ ሕግንና ነቢያትን ልንፈጽም እንደገና የኋሊት መመለስ አላዋቂነታችንን ከሚያሳይ ባሻገር በቃሉም የተጻፈልን ስለሆነ ፍጹም ስሕተት ነው ከዚህም ሌላ እንግዲህ እንደ አይሁድ አንገዘር አሪትና ነቢያትን የሚፈጽም እንደመጣ እናውቃለን የሚለው ቃል  በአመክንዮ ዘሐዋርያት ላይ የሠፈረና የእናት ኦርቶዶክስ የእምነት መግለጫ የሚያመለክት ስለሆነ ይህንኑ እውነታ መካድና ክርስቶስም ሕግንና ነቢያትን ሊፈጽማቸው አልመጣም ማለትን የሚያመለክትብን ስለሆነ ትልቅ ሥህተት ላይ ይጥለናል ደግሞም ይህ አለመረዳት ብዙዎችን ሥህተት ላይ ጥሏቸዋል እየጣላቸውም ይገኛል እንዲየው እንበልና መጽሐፍቅዱሱን እንኳ ሽምጥጥ አድርገን ብንክድ በእናት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በገዛ የእምነት መግለጫዋ ላይ ቁልጭ ብሎ በሚገባ የተጻፈልን ስለሆነ የተጻፈው  ራሱ የእምነት መግለጫ በግልጽ ይመሰክርብናልና የትም ልናመልጥ አንችልም የእምነት መግለጫውም የተጻፈው ራሱ ከቃሉ የተነሳ ስለሆነ ቃሉ ደግሞ እንደሚገባ የማያፈናፍነን አድርጎ ይመሰክርብናል ስለዚህ በማያዛልቀን የግዝረት ሰፈር  ኦሪትንና ነቢያትን እኔም በማንነቴ ለመዳኔ ስል እፈጽማቸዋለሁ በሚል የጀብደኝነትና  የወነኝነት መንደር ውስጥ ተመካኝተን እንደገናም ተመቻምቸን በከንቱ አንቅር ይልቁንም ሕግንና ነቢያትን የሚፈጽማቸው እንደመጣ የታወቀ ሆኗልና ሕግን ፈጽሞልን በጸጋው ወዳዳነን ጌታ አምነን ለመዳኔ ልፈጽም ያልቻልኩትን ሕግን ፈጽመህ በጸጋህ አዳንከኝ ስንል ተሸንፈን ለዚህ ለሚያድነንም ጸጋ ራሳችንን አሳልፈን ልንሰጥ ወደዚህ ጌታ እንምጣ ለመዳናችን የሚያዛልቀን ይኸው ጌታና የሚያድነንም ጸጋው ነው ነገር ግን በመገረዜና ሕግን በመፈጸሜ እድናለሁ የሚለው ትምክህት  እንኳን ለእኛ ሕግን በመጀመርያ በሙሴ በኩል ተቀብለው ሊፈጽሙ ለሚፈልጉና ሊድኑም ለሚናፍቁ በየጊዜውም ለሚገረዙ ለአይሁድም አልጠቀመም የተረፋቸው የቀረላቸውም ነገር ትምክህታቸው ብቻ ነው መጽሐፍቅዱሳችን በገላትያ 5 4 ላይ በሕግ ልትጸድቁ የምትፈልጉ ከክርስቶስ ተለይታችሁ ከጸጋው ወድቃችኋል ይለናል ስለዚህ ከክርስቶስ ተለይተን ከጸጋው በታች ከምንወድቅ በሕግ ልንጸድቅ መፈለጋችንን ማቆም ይሻለናል ደግሞም ማቆም አለብን አለበለዚያ ከክርስቶስ የምንለይበት መለየት ከጸጋው በታች የሚጥለን በመሆኑ ውድቀታችንን የከፋ ያደርገዋል  ለራት የታሰበ ለቁርስ እንደሚሆን እኛ ሕግን ጠብቀንና ተገርዘን መንግሥተ ሰማያት እንገባለን ብለን ስንኳትት ዲያብሎስ በአቋራጭ ገብቶ የገሃነመ እሳት ራት ያደርገናል ከዚህ ይልቅ የመዳን ቀን አሁን ስለሆነ ዛሬ በዚህ ኦሪትንና ነቢያትን በፈጸመልን ጌታ በጸጋው መዳን ይሁንልን 2 ቆሮንቶስ 6 2 መጽሐፉ እንደሚነግረን የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሳያውቁ የራሳቸውንም ጽድቅ ሊያቆሙ ሲፈልጉ፥ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና በማለት በግልጽነት የቃሉን አብርሆት የሰጠን ስለሆነ ሮሜ 10 3 እና 4 እንድናለን ስንል የራሳችንን ጽድቅ ካቆምንበት ስፍራ ወጥተን አምነን ወደምንጸድቅበት ክርስቶስም ወደ ፈጸመልን የሕግ ፍጻሜና የጸጋ መዳን እንምጣ ይህ ክርስቶስ የፈጸመው ሕግ ሰዎች የዳኑበት፣ የሚድኑበትና ሊድኑም ያሉበት የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው የምናነበውን ቃል እንድናስተውለው እንድንጠቀምበትም እግዚአብሔር ይርዳን
እስመ በኢየሱስ ክርስቶስ ተገዝሮሂ ኢይበቊዕ ወኢተገዝሮሂ ኢያሰልጥ ዘእንበለ ሐዳስ ፍጥረት

በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት መሆን ይጠቅማል እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና

                       ገላትያ 6 15


ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን




ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ  

No comments:

Post a Comment