Friday, March 13, 2015

የሐዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን የተጀመረችው ወይም የተመሠረተችው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማይ ከወጣ ወይም ካረገ በኋላ በአሥረኛው ዕለት በጴንጤቆስጤ ቀን ነው

ቤተክርስቲያን

ክፍል አንድ


የሐዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን የተጀመረችው ወይም የተመሠረተችው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማይ ከወጣ ወይም ካረገ በኋላ በአሥረኛው ዕለት በጴንጤቆስጤ ቀን ነው እግዚአብሔር መንፈሱን የጌታችንን ትዕዛዝ ለመታዘዝና የታዘዙትንም ለመፈጸም በኢየሩሳሌም በቀሩት ደቀመዛሙርት ላይ በዚሁ በጴንጤቆስጤ ቀን በአንድ ላይ ተሰብስበው ሳሉ አፈሰሰባቸው ለዚህ ነው በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 24 ቁጥር 49 ላይ ጌታችን ኢየሱስ እነሆም አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ ሲል የተናገረው ጌታችንም በተናገረው መሠረት መንፈስቅዱስ በዚሁ በጴንጤቆስጤ ቀን መጣ የሐዋርያት ሥራ 2 ፥ 1  _ 4 በዚያን ቀን በሐዋርያው ጴጥሮስ አገልግሎት ልባቸው የተነካና ቃሉንም የተቀበሉ ሦስት ሺህ የሚያህል ነፍስ ወደ ጌታ መንግሥት ተጨመሩ በሐዋርያት ትምህርትና በኅብረት እንጀራውንም በመቁረስ በየጸሎቱም ይተጉ ነበር በማለት የእግዚአብሔር ቃል ይነግረናል የሐዋርያት ሥራ 2 37 _ 42 ከዚህም በኋላ ይህንኑ ሁኔታ  ሐዋርያት ተንተርሰው በዚህ ስም እንዳታስተምሩ አጥብቀን አላዘዝናችሁምን ?  እነሆ ኢየሩሳሌምን በትምሕርታችሁ ሞልታችኋል የዚያን ሰው ደም በእኛ ታመጡብን ዘንድ ታስባላችሁን ? ብሎ ለጠየቃቸው ሊቀካህንና አምጥተውም በሸንጎ ፊት ላቆሙአቸው ሰዎች ሁሉ እጅግ አስደናቂና ማራኪም የሆነ መልስ ሰጥተዋቸው ነበር እነዚሁ ደቀመዛሙርት የመጀመርያውን መልስ ሲሰጡ ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል አሉ በመቀጠልም ኢየሱስ ክርስቶስ ንስሐንና የኃጢአትን  ሥርየት ለመስጠት ራስና መድኃኒት ሆኖ ከፍ ከፍ ማለቱን በግልጽነት ከተናገሩ በኋላ እኛም ለዚህ ነገር ምስክሮች ነን ደግሞም እግዚአብሔር ለሚታዘዙት የሰጠው መንፈስቅዱስ ምስክር ነው በማለት የመንፈስቅዱስን የሥራ ድርሻና  ምስክርነት እነርሱም ለቃሉ በመታዘዛቸው ምክንያት ከመንፈስቅዱስ የተነሳ ምስክሮች መሆናቸውን በግልጽነት ተናገሩ መሰከሩ  የሐዋርያት ሥራ 5 27 _ 32 እነዚሁ ሐዋርያት ትክክለኛ የቃሉ ምስክሮች በመሆናቸው የእግዚአብሔር ቃል እንደሚነግረን እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ በሕዝብ ሁሉ ፊት  ሞገስ ነበራቸው ጌታም የሚድኑትን ዕለት ዕለት በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር ይለናል የሐዋርያት ሥራ 2 47 የቃሉ ምስክሮች ስንሆን የሰዎች ልብ ተነክቶ ሦስት ሺህ የሚያህል ነፍስ ብቻ ወደ ጌታ መንግሥት የሚጨመሩ አይሆኑም ጌታም የሚድኑትን ሳይቀር ዕለት ዕለት በእኛ ላይ ይጨምራል ሐዋርያት ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል ማለታቸውም  የቃሉ ምስክሮች በመሆናቸው ነው ሐዋርያት ጉዳያቸው ሕዝብ ማብዛት የአባል ቁጥር መጨመር አይደለም የቃሉ ምስክር መሆን ነው ከዚህ የተነሳ ይህንኑ የማዳን ቃል የተሸከሙ በመሆናቸው በስብከት ሞኝነት ብቻ ሳይሆን ገና ሳይሰብኩም በምሥጋና ውስጥ ሆነው ጌታ የሚድኑትን ዕለት ዕለት በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር እኛንም እግዚአብሔር እንደነዚሁ እንደ ሐዋርያት ቃሉን ያሸክመን የቃሉ ምስክሮች ያድርገን በዚህን ጊዜ እኛ ተናግረንና መስክረን ብቻ ሳይሆን ቃሉን የያዝን በመሆናችን ሳንመሰክርም የሚድኑትን ሰዎች በእኛ ላይ ይጨምራል ዛሬ ግን በአንጻሩ የቃሉ ምስክሮች ከምንሆን ይልቅ አባል አፍርተንና ሕዝብ አብዝተን ትልቅ ሜጋ ቸርች የማቋቋም አላማና ከተቻለም እኛን መሰል ሌሎች የወንጌላውያን አብያተክርስቲያናትን አገልጋዮቻቸውንም ሳይቀር በስራችን የማድረግ ተልኮ ያለን በመሆናችን ሥራችን ውጤታማ ሳይሆን ቀርቶ ሕልማችንም እንዲሁ የሕልም እንጀራ ሆኖ ይቀራል ሕዝብ ማብዛቱ ትልቅ ሜጋ ቸርች ማቋቋሙና መደራጀቱ መልካም ሆኖ እግዚአብሔርም ሳይቀር  የሚወደው ቢሆንም ቲቶ የራስን የበላይነት ለማረጋገጥና ሌሎች መሰል  የወንጌላውያን አብያተክርስቲያናትንና አገልጋዮችን በሥር ለማድረግ ለመጠቅለልም የሆነውን አደራረግና አሰራር ግን እግዚአብሔር ፍጹም ይቃወመዋል እግዚአብሔር እኛን የሚያውቀንና ሊያውቀንም የሚፈልገው በአንድ በተደራጀ ትልቅ ኢንካም ባለውና ሜጋ ቸርች በሆነ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሳይሆን በክርስቶስ ውስጥ ነው በክርስቶስ መሆናችንን ሳናረጋግጥና በክርስቶስም ሳንሆን አያችሁ ? የተደራጀውና ትልቁ ሜጋ ቸርች የሆነው ቸርቼ  ይሄ ነው ብንል ድርጅታችንን ወይንም ቸርቻችንን የምንሰብክ ከምንሆን በስተቀር እንደ ሐዋርያት የቃሉ ምስክሮች አይደለንም ከዚህ የተነሳ ብዙ ሰዎች በዚህ መረዳት ውስጥ ስላሉ የቸርቻቸው ፍቅር ነው ያላቸው እንጂ የቃሉ ፍቅር የላቸውም የቸርች ነገርም ሲነሳ ከእነርሱ ውጪ ሌላው ቸርች ቸርች አይመስላቸውም ሰው ሁሉ ወደ እነርሱ መጥቶ ቢጠቀለል እነርሱንም ቢመስል ከእነርሱም ጋር ቢሆን ይወዳሉ በአጠቃላይ ቃሉን ሳይሆን ቸርቻቸውን ያመልካሉ ይህ ግን ፍጹም ስሕተት ነው እኛ ቃሉን ልናመልክ እንጂ አጥቢያ ቸርቾቻችንን ልናመልክ አልተጠራንም እንደገናም ብዙውን ጊዜ የቅዱሳን ሕይወትም የማያድገው በዚህ የተሳሳተ መረዳት ውስጥ ከመሆን የተነሳ ነው ቸርች ሄዶ መምጣቱ መመላለሱ ያለ ቃሉ ዋጋ የለውም ቸርች የምንሄደው በወገኖች ሕብረት ባለ በረከት ውስጥ ሆነን የእግዚአብሔርን ቃል ልንሰማ በቃሉም ተኮትኩተን ልናድግና እግዚአብሔርን ልናመልክ ነው እንጂ ቸርች መሄድ ስላለብን ብቻ አይደለም በእርግጥ ዳዊት ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ ብሏል ዳዊት ይህንን ያለው በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ያለውን በረከትና መንፈሳዊ የሆነውንም ስጦታ ተመልክቶ ነው እንደገናም ዛሬ ተደራጅተን ተቋቁመንና የምናመልክበትንም አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን  ገዝተን ጌታም ረድቶን በአንድነት ያለምንም ችግር  ልናመልክ እንችላለን ይህ ሁኔታ ግን በነገው እድል እንደፈለግነው ሆኖ እንደዚህ ላይቀጥል ይችላል የነገው ጊዜ የፈተና ጊዜ ይሆንና መበተን ሊያጋጥም ቢችል  መጽሐፍ ቅዱሳችን የተበተኑትም ቃሉን እየሰበኩ ዞሩ ፊልጶስም ወደ ሰማርያ ከተማ ወርዶ ክርስቶስን ሰበከላቸው ስለሚለን የሐዋርያት ሥራ 8 1 _ 6 ከምንምና ከማንም በላይ በቃሉ ላይ ትኩረት ልናደርግ ይገባል እነዚህ ቅዱሳን ከመከራው ብዛት የተነሳ ቢበተኑም ለሕይወታቸው የቀረላቸው ትልቁ ነገር በተደራጁበት ነገር ያፈሩት ኃብት ሳይሆን ቃሉ ነበር በሕብረት ሆነው ሳሉ ያፈሩት ሃብት ንብረት ገንዘብና የመሳሰሉት ነገሮች ከእነርሱ ጋር ባይሆንም በዓመታት ውስጥ ያከማቹት የሰነቁትና ያጠራቀሙት ቃል ግን ከእነርሱ ጋር ነበር ስለዚህ በስደት ምክንያት የደረሰባቸው መበተን ቃሉን እየሰበኩ እንዲዞሩ አደረጋቸው እንጂ ተበትነው እንዲቀሩ ከዓላማቸውም እንዲደናቀፉ አላደረጋቸውም በዚህም ምክንያት ነው እንግዲህ የሰማርያ ሰዎች ቃሉን የመቀበል ዕድል ያጋጠማቸው በኢየሩሳሌምም የነበሩት ሐዋርያት የሰማርያ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል እንደተቀበሉ ሰምተው ጴጥሮስንና ዮሐንስን ሰደዱላቸው የሚለን ወገኖች የዚህ ተከታይ ክፍል ሁለት ትምህርትና ቀጣይ የሆኑ ተከታታይ ሃሳቦች ስላሉ በማስተዋል ሆናችሁ እንድትከታተሉአቸው በጌታ በሆነው ወንድማዊ ፍቅር ላሳስባችሁ እወዳለሁ ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ አሜን


በጌታ ወንድማችሁ የሆንኩ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ነኝ

No comments:

Post a Comment