Friday, March 13, 2015

በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው እንግዲህ የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት አላቸው

ቤተክርስቲያን

ክፍል ዘጠኝ


 በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው
እንግዲህ የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት አላቸው
   
           የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 9 ቁጥር 37 እና 38


ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማንንም ሰው ተነስቶ ወይንም ከዚህ በፊት የሚያውቁትን የሰሙትን ትምህርቱንም የተካፈሉትን ሰዎች መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው እንግዲህ የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት አላላቸውም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  ያለው ደቀመዛሙርቱን ነው ደቀመዛሙርቱ የሚላኩ ሠራተኞች እነማንና ምን ዓይነት እንደሆኑ ጌታም ሠራተኞችን እንዲልክ እንዴት ባለ ሁኔታ የመከሩን ጌታ እንደሚለምኑ   እንደገናም ስለመከሩ ብዛትና ስለመከሩ ከኢየሱስ ጋር  በጥቂቱም ቢሆን ቆይታ አድርገው ደቀመዛሙርት የተባሉ ናቸውና እውቀት አላቸው ለመከሩ ሥራ ስለሚላኩ ሠራተኞችም  ሆነ ስለ መከሩ መለመን የሚችል  ቢያንስ ሃላፊነት ተሰምቶትና ሥራዬ ብሎም ሊተጋ የሚችል የደቀመዛሙርቱ ዓይነት ሕይወትና መረዳት ያለው ሊሆን ይገባል ለዚህ ነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሌላ ስፍራ ላይ በመከሩ ሥራ ላይ መዘናጋት ላጋጠማቸው ደቀመዛሙርት እናንተ ገና አራት ወር ቀርቶአል መከርም ይመጣል ትሉ የለምን ? እነሆ እላችኋለሁ፥ ዓይናችሁን አንሡ አዝመራውም አሁን እንደ ነጣ እርሻውን ተመልከቱ የሚያጭድ ደመወዝን ይቀበላል፥ የሚዘራና የሚያጭድም አብረው ደስ እንዲላቸው ለዘላለም ሕይወት ፍሬን ይሰበስባል አንዱ ይዘራል አንዱም ያጭዳል የሚለው ቃል በዚህ እውነት ሆኖአልና  እኔም እናንተ ያልደከማችሁበትን ታጭዱ ዘንድ ሰደድኋችሁ፤ ሌሎች
ደከሙ እናንተም በድካማቸው ገባችሁ በማለት የተናገራቸው ዮሐንስ ወንጌል 4 35 _ 38 አዝማራው እንዲሁ ከሜዳ ተነስቶ አዝመራ የሆነ ሳይሆን ብዙ ድካምን የጠየቀ ስለዚህ ጉዳይ መንፈሳዊ እውቀትና መረዳት ያላቸው ከደቀመዛሙርቱ በፊት የነበሩ ሌሎች የደከሙበት ነው አዝመራው ከዘር ከቡቃያና ከዛላ ተነስቶ አዝመራ ሆኖ እንዲደርስ እነዚሁ ሰዎች በብዙ ደክመዋል ደቀመዛሙርቱ ግን በእነዚሁ ሰዎች ድካም ውስጥ ገብተው እንዲያጭዱ ደሞዛቸውንም እንዲቀበሉ ጌታችን ኢየሱስ እናንተ ገና አራት ወር ቀርቶአል መከርም ይመጣል ትሉ የለምን ? እነሆ እላችኋለሁ፥ ዓይናችሁን አንሡ አዝመራውም አሁን እንደ ነጣ እርሻውን ተመልከቱ የሚያጭድ ደመወዝን ይቀበላል፥ የሚዘራና የሚያጭድም አብረው ደስ እንዲላቸው ለዘላለም ሕይወት ፍሬን ይሰበስባል አንዱ ይዘራል አንዱም ያጭዳል የሚለው ቃል በዚህ እውነት ሆኖአልና አላቸው ስለዚህ መከርን የሚያውቅ ሰው ለመከሩም ሠራተኛ ሊሆን የቀረበ የመከሩ ሠራተኞች እንዲጨመሩ የመከሩን ጌታ የሚለምን በሥራው የተዘናጋ ካልሆነ ወደነጣው ለመታጨድና ወደ ጎተራም ሊከተት ወደ ደረሰው አዝመራ ይደርሳል በመሆኑም ዛሬ በእኛ ዘመን እኛ ምን እያደረግን ይሆን ? ቅዱሳን ልመናችንስ ምን ይሆን ? መከሩና የመከሩ ሥራ የሠራተኞች መጨመር ? ወይስ ሌላ የግል አጀንዳ ? መጽሐፍቅዱስ በሮሜ 8 23 ላይ እርሱም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን የመንፈስ በኵራት ያለን ራሳችን ደግሞ የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን ልጅነት እየተጠባበቅን ራሳችን በውስጣችን እንቃትታለን ይለናል ስለሆነም ለመከሩና ለመከሩ ሥራ ሠራተኞችን የሚለምኑ እንደገናም የነጣውን አዝመራ አይተው በማጨድ ወደ ጎተራ የሚያስገቡ የተቻላቸውና የተፈቀደላቸው ሰዎች ሳይሆኑ ሐዋርያው አሁንም በዚሁ በሮሜ 8 23 ላይ እንደተናገረው የመንፈስ በኩራት ያላቸው ራሳቸው ደግሞ የሰውነታቸውን ቤዛ የሆነውን ልጅነት እየተጠባበቁ ራሳቸው በውስጣቸው የሚቃትቱት ናቸው ወገኖቼ እንግዲህ ቃሉ እንዳስተማረን የእግዚአብሔር ሥራ የሚሠራው በአዕምሮ ብልሃትና በብዙ ዘዴዎች ሳይሆን በመንፈስ መቃተት ነው ይሄ የተወለድንበት መንፈስ እኛው ለእኛ ብቻ የሚጮኸ  ሳይሆን ብዙዎች ከእግዚአብሔር የመንፈስ መወለድን  እንዲያገኙ ተወልደውም በቡቃያና በዛላ ገና በእንጭጩ እንዳይቀሩ ወደ መከሩና ወደ ሰብል ወደነጣውም አዝመራ ደርሰው ለእግዚአብሔር ጎተራ እንዲበቁ የሚቃትት ነው ይህንን ለማድረግ ደግሞ በሥጋ ያሉቱ እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉምና ስለሚለን ቃሉ የእግዚአብሔርን ሥራ በተመለከተ   በሥጋ ማሰብን ማቆም ይኖርብናል ሮሜ 8 7 እና 8 በሥጋ የእግዚአብሔርን ሥራ እንስራ ብንል ብዙ ድካምና መላላጥ ከሚሆንብን ውጪ አንገፋውም ከዚህም ሌላ ብቻችንን እንቀራለን እንጂ ሰሚ አናገኝም በመንፈስ በምንሆንበት ጊዜ የእግዚአብሔር ሥራ መዘናጋት የሌለበትና ቸል የማይባል ይሆናል እንደገናም በሕይወታችን የማይቆምና የሚቀጥል ሆኖ ይታያል ሐዋርያት ለመከሩ ሥራ የተዘናጉት በሥጋ አስተሳሰብ ውስጥ ገብተው ነው ጌታችንን መምህር ሆይ ብላ ብለው በለመኑት ጊዜ እርሱ ግን እናንተ የማታውቁት ሌላ መብል አለኝ አላቸው በዚህን ጊዜ ነበር የሚበላው አንዳች ሰው አምጥቶለት ይሆንን ? የተባባሉት ከዚያ በኋላ  ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ የእኔስ መብል የላከኝን ፈቃድ አደርግ ዘንድ ሥራውንም እፈጽም ዘንድ ነው አለ የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 4 31 _ 35 መብላችን ሁልጊዜ እንጀራና ዳቦ አይደለም የአባታችንን ፈቃድ ማድረግ ሥራውንም መፈጸም ነው  ለምን ? ስንል  በጢሞቴዎስ መጽሐፍ ላይ ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው  በማለት ይነግረናል 1 ጢሞቴዎስ 2 3 እና 4 በመሆኑም እግዚአብሔር ስለወደደ የሰማርያ ሰዎች ዳኑ እውነቱንም ወደማወቅ ደረሱ ሳምራዊቷ ሴትም እንስራዋን ትታ ወደ ከተማ ሄደች ለሰዎችም ያደረግሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ኑና እዩ እንጃ እርሱ ክርስቶስ ይሆንን ? አለች እነርሱም ከከተማ ወጥተው ወደ እርሱ ይመጡ ነበር ይለናል ዮሐንስ ወንጌል 4 26 _ 30  ሰዎች ምንም እንኳ ለእግዚአብሔር ነገር የማይመቹ ሆነው የእግዚአብሔርን ሥራ የተቃወሙ ቢሆኑም ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው ስለሚለን ቃሉ ሁልጊዜ ደህንነት ለእነርሱ ይሆናል የሰማርያ ሰዎች እንደዚያ ነበሩ የእግዚአብሔርን ሥራ የሚቃወሙ ነበሩ ከዚህም የተነሳ የዘብዴዎስ ልጆች የኤልያስ እሳት ወርዳ እንድትበላቸው የኤልያስን እሳት ለምነውባቸዋል ጌታ ኢየሱስ ግን ወደ እነርሱ ዘወር ብሎ ገሠጻቸውና ምን ዓይነት መንፈስ እንደ ሆነላችሁ አታውቁም የሰው ልጅ የሰውን ነፍስ ሊያድን እንጂ ሊያጠፋ አልመጣም አለ ይለናል የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 9 51 _ 56 ስለዚህ እኛም ዛሬ በዘመናችን ሰዎች እንዲህና እንዲያ አደረጉ ስለዚህ የመዳን ተስፋ የላቸውምና ይህ ይምጣባቸው ይህም ያግኛቸው ልንል አንችልም አይገባምም  የሰዎቹ ነገር በእኛ ያበቃ ቢመስልም እንኳ በእግዚአብሔር ግን ገና ያልተቆረጠ በመሆኑ እኛ ባልጠበቅነው መንገድ ደህንነት ለእነርሱ ይሆናል ሐዋርያው ጴጥሮስ ሲናገር  ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል ነው የሚለን 2 ጴጥሮስ 3 9  ጌታም ለዚህ ነው የዘብዴዎስ ልጆች እንደ ቃሉ የሆነን እርምጃ ስላልተራመዱ ገሠጻቸውና ምን ዓይነት መንፈስ እንደሆነላችሁ አታውቁም ያላቸው እኛም ሰዎች ይድኑና እውነቱን ወደማወቅ እንዲደርሱ እንታገስ ከቁጣችንም እንመለስ እንደቃሉ የሆነውን መንፈሳችንንም እንጠብቅ በመጨረሻም አንድ ልናየው የምፈልገው ነገር በመከሩ ላይ እንዲጨመሩ የምንለምነው ሠራተኞች የክርስቶስን ዓይነት ሥራ የሚሠሩ ሠራተኞች ሊሆኑ ይገባል ክርስቶስ ምን ሠራ ? ስንል በምኩራቦቻቸው እያስተማረ፥ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ፥ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ፥ በከተማዎችና በመንደሮች ሁሉ ይዞር ነበር ብዙ ሕዝብም ባየ ጊዜ፥ እረኛ እንደ ሌላቸው በጎች ተጨንቀው ተጥለውም ነበርና አዘነላቸው ይለናል የማቴዎስ ወንጌል 9 35 እና 36 እንደገና በማቴዎስ ወንጌል 8 16 እና  ፲፯ ላይ በመሸም ጊዜ አጋንንት ያደረባቸውን ብዙዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ በነቢዩ በኢሳይያስ  እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ደዌያችንንም ተሸከመ የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ መናፍስትን በቃሉ አወጣ፥ የታመሙትንም ሁሉ ፈወሰ ስለሚል ለመከሩ ሥራ ለምነን የምናገኛቸው ሠራተኞች እንደ ኢየሱስ ተጨንቀውና ተጥለው  የነበሩትን ሕዝቦች ማየት የሚችሉ አይተውም የሚራሩላቸው የሚያዝኑላቸው ሊሆኑ ይገባል ከዚያ በኋላ ነው በከተማዎችና በመንደሮች ደዌንና ሕማምን እየፈወሱ መዞር የሚመጣው መሸ ነጋ ጨለመ ሳይሉም እንደ ኢየሱስ ችግረኛንና ደካማን ሕዝብ ወዶ የብዙዎችን ድካምና ደዌ መሸከም  ልዩ ልዩ እስራቶቻቸውን በቃሉ መፍታት መፈወስ የሚቻለው አሁንም ማየትና አይቶም መራራት ሲቻል ነው ይሁን እንጂ ዛሬ እንደዚህ ዓይነቱን ነገር አይተን ከምንራራ ተገቢውንም መንፈሳዊ አገልግሎት ጌታ በሰጠን ጸጋ ሁሉ ከምንሰጥ ይልቅ በዓይኖቻችን ለእኛ ይጠቅማሉ የምንላቸውን ነገሮች ብናይ በነዛም ነገሮች ላይ ጊዜ ብናጠፋና የእኛም ቢሆኑልን እንወዳለን ለዚህ ነው በሕዝኤል 34 ከቁጥር 2  ጀምሮ የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር፥ በእስራኤል እረኞች ላይ ትንቢት ተናገር፥ እረኞችንም እንዲህ በላቸው። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ራሳቸውን ለሚያሰማሩ ለእስራኤል እረኞች ወዮላቸው፦ እረኞች በጎችን ያሰማሩ ዘንድ አይገባቸውምን ? ጮማውን ትበላላችሁ ጠጕሩንም ትለብሳላችሁ፥ የወፈሩትን ታርዳላችሁ በጎቹን ግን አታሰማሩም የደከመውን አላጸናችሁትም የታመመውንም አላከማችሁትም የተሰበረውንም አልጠገናችሁትም የባዘነውንም አልመለሳችሁትም የጠፋውንም አልፈለጋችሁትም በኃይልና በጭቈናም ገዛችኋቸው እረኛንም በማጣት ተበተኑ፥ ለምድርም አራዊት ሁሉ መብል ሆኑ፥ ተበተኑም በጎቼ በተራሮች ሁሉና በረዘሙ ኮረብቶች ሁሉ ላይ ተቅበዝብዘዋል፥ በጎቼም በምድር ፊት ሁሉ ላይ ተበትነዋል የሚሻም የሚፈልግም አልነበረም ስለዚህ፥ እረኞች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና እረኛ ስለሌለ እረኞቼም በጎቼን ስላልፈለጉ እረኞችም ራሳቸውን እንጂ በጎቼን ስላላሰማሩ፥ በጎቼ ንጥቂያ ሆነዋልና፥ በጎቼም ለምድር አራዊት ሁሉ መብል ሆነዋልና ስለዚህ፥ እረኞች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በእረኞች ላይ ነኝ፥ በጎቼንም ከእጃቸው እፈልጋለሁ፥ በጎቼንም ከማሰማራት አስተዋቸዋለሁ ከዚያም ወዲያ እረኞች ራሳቸውን አያሰማሩም በጎቼንም ከአፋቸው አድናለሁ፥ መብልም አይሆኑላቸውም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና እነሆ፥ እኔ ራሴ በጎቼን እሻለሁ እፈልግማለሁ  እረኛ በተበተኑት በጎች መካከል ባለ ጊዜ መንጋውን እንደሚፈልግ፥ እንዲሁ በጎቼን እፈልጋለሁ በደመናና በጨለማ ቀን ከተበተኑት ስፍራ ሁሉ አድናቸዋለሁ እያለ  የምዕራፉ ሙሉ ሃሳብ የሚነግረን እኛ ሸክሙ ኖሮን ሃላፊነቱም ግድ ብሎን የባዘነውን ባንፈልግ የወደቀውን ባናነሳ እረኛችን ግን በጎቹን ከተበተኑበት ሥፍራ ፈልጎ ያገኛቸዋል ያድናቸውማል ስለዚህ ወገኖቼ ሆይ የመከሩ ሠራተኞች ሆነን ጌታ እግዚአብሔር የሚጠብቅብንን ነገር እንድናደርግ እርሱ ይርዳን




ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment